ለኦነግና ኦነጋዊያን – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እንደሚታወቀው በተማሪዎች የተጀመረው ተቃውሞ ሌላው የኅብረተሰብ ክፍልም ተቀላቅሎት ሲደረግ የቆየው ሕዝባዊ ተቃውሞ እነሆ ሁለት ወራት እየሆነው ነው፡፡ እያየነው እንዳለነው እስከአሁን ተቃውሞው ያመጣው ውጤት ወይም ለውጥ የለም፡፡ ወደፊትም ሕዝቡ በዓመፁ የመቀጠል ብርታት የሚኖረው ከሆነ “በእኔ ግምት ይኖረዋል ብየ ስላልገመትኩ ነው ምክንያቶች አሉኝ” እንዲያው ከሆነ ግን ወያኔ ሁሉንም ለቃቅሞ እስኪፈጅ ድረስ ሳይሰለች መፍጀቱን ይቀጥላል እንጅ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት “እሽ! ተሳስቻለሁ ይቅርታ! ካሳም እከፍላለሁ! ያላቹህት ሁሉ ይሁን!” ብሎ እጅ የሚሰጥበት ሁኔታ ይፈጠራል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው፡፡

ይህ መሆኑን የሚወድ ዜጋ ይኖራል ብየ ለመገመት ይቸግረኛል፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ኦነግና ኦነጋዊያን ውጤቱ እንዲህ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡ እንዴት? ቢባል ሁለት ዐበይት ምክንያቶች አሉ፡፡

  1. ጥያቄውና ችግሩ የመላው ኢትዮጵያውያን ሆኖ እያለ የኦሮሞ ብቻ እንደሆነ በመወሰዱ፣ እንዲያ ተደርጎ እንዲታሰብ ጥረት በመደረጉና ተቃውሞው በምክንያቱ ወይም በመንስኤው ላይ ሳይሆን በውጤቱ ላይ ያተኮረ በመሆኑ፡፡
  2. ይሄንን ተቋውሞ የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብም እንዲቀላቀለው እንዲዋሐደው እንዲተባበረው ኦነግና ኦነጋዊያን መሥራት ያለባቸውን የቤት ሥራ ሥላልሠሩና መሥራትም ስላልፈለጉ ነው፡፡

እያንዳንዳቸውን በዝርዝር ዕንይ፡-

በአንደኛ ተራ ቁጥር ላይ በተጠቀሰው ጉዳይ ላይ እንደሚታወቀው የመሬት መፈናቀልና የመሬት ባለቤትበት ዋስትና የማጣት ችግር የኦሮምኛ ተናጋሪ ተቃውሞ አድራጊዎቹ እየገለጹት እንዳሉት በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ገበሬዎች ችግር ፈተና ብቻ ሳይሆን በመላ ኢትዮጵያ ያሉ ገበሬዎችና የከተማ ነዋሪዎችንም ጭምር ነው፡፡ በከተማ መስፋትና መሬታቸው ለባለሀብቶች በመሸጡ ምክንያት እየተፈናቀሉና እንዳይሆኑ ሆነው እየቀሩ ያሉ ዜጎች በመላ ሀገሪቱ ያሉ ዜጎች ሁሉ እንጅ አዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ገበሬዎች ብቻ አይደሉም፡፡

ምሳሌ፡- ባሕር ዳር ብንሔድ ተመሳሳይ ችግር በከተማው መስፋትና ከገበሬዎች እየተነጠቀ ለባለሀብቶች በሚሰጠው መሬት ምክንያት ከገበሬዎች ጋር በተፈተረ አለመግባባትና ችግር ምክንያት ገበሬዎች ለጅምላ እስር ተዳርገዋል፣ የተገደሉ አሉ፣ አማራጭ አጥተውና ተገደው የካሳ ገንዘብ ተቀብለው መሬታቸውን ለመልቀቅ የተስማሙትም የማትረባ የካሳ ገንዘብ ተሰጥቷቸው ይህቺ ገንዘብ ከወራት ላለፈ ጊዜ የማታቆይ በመሆኗ ለከተማ ኩሊነት የተዳረጉ ገበሬዎች በርካቶች ናቸው፡፡

በመሆኑም ባለፈው ጊዜም ለማስገንዘብ እንደሞከርኩት መቃወም ካለብን መቃወም ያለብን በጎጥና በዘር ሳንወሰን ሕዝቡን የሀገሩና የመብቱ ባለቤትና ተጠቃሚ እንዳይሆን ያደረገውን፤ ወያኔን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገውን የወያኔን ሸፍጠኛ የመሬት አሥተዳደር ሥርዓት ነው እንጅ የከተማ መስፋት አቅድን መሆን የለበትም፡፡ ምክንያቱም ችግራችን የከተማው መስፋት ላይ ከሆነ አንደኛ አስተሳሰቡ ካለው ተፈጥሯዊና ነባራዊ እውነታ ጋር የሚጋጭ የማይስማማ የደነቆረ አስተሳሰብ በመሆኑ፡፡ ሁለተኛ ይህ አስተሳሰብ ወያኔ ሲወድቅና ወደፊት ሌሎች መንግሥታት ሲመጡም ከነሱም ጋር የማያስማማ የደነቆረ የጥፋት አስተሳሰብ በመሆኑ፡፡ ይሄንን ተቃውሞ አመክንዮዊ የማያደርገው ሌላው ምክንያት ደግሞ ወያኔ እንደሚለው አዲስ አበባ ራሷ ባለቤትነቷ ኦሮሚያ ብሎ የሚጠራው ክልል ነው ይላልና ነው፡፡

እንዲህ ዓይነት በአመክንዮ ያልተደገፈ ተቃውሞን ይዞ መነሣት ተቃውሞውን ጽናትንና በዘላቂነቱ ላይም ወያኔን እስከማስወገድ ሊደርስ የሚያስችለውን አቅም ያሳጣዋል፡፡ ተቃውሞ አድራጊዎቹ እንደሚሉት የተቃውሞ ምክንያታቸው የአዲስ አበባ የማስፋፊያ አቅድ ብቻ ከሆነ በእርግጥም ይሄ ተቃውሞ ብስለትና ትክክለኛነት የጎደለው የትም የማይደርስ ማረሻውን ወስደውበት እያለ ለመርፌው የሚያለቅስ የጅል ለቅሶ ከመሆን የዘለለ አይደለም፡፡

ምን ማለቴ ነው፡- ወያኔን እንቃወም ካልን ልንቃወመው የሚገባን ሕዝብ ይሁንታ ያልሰጠው ያልመረጠውና በኃይል ሥልጣንን ይዞ ረግጦ የሚገዛ ጨካኝ አንባገነን አገዛዝ በመሆኑ፣ በሀገርና በሕዝብ ህልውና ላይ የሚቆምር ወራዳ፣ ነውረኛ፣ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባይ የሀገርና የሕዝብ ጠላት በመሆኑ ነው እንጅ በዚህ አልነበረም፡፡

ተቃውሞ አድራጊዎችን መጠየቅ የምፈልገው ጉዳይ ቢኖር፡- እሽ ወያኔ ሸፍጠኛ የመሬት አስተዳደር መመሪያው እንዳለ ሆኖ እየጠየቃቹህት እንዳለው የአዲስ አበባን የማስፋፊያ አቅድ የምሩን “ትቻለው ሰርዣለሁ!” ብሎ ቢል በቃ ተቋውሟቹህን ታቆማላቹህ ማለት ነው?

ዕያየነው እንዳለው ወያኔ ተቋውሞውን ለማብረድ ሲል የማስፋፊያ አቅዱን እንደሰረዘ መግለጹንና “የማስፋፊያ አቅዱን ከሰረዝኩ ሌላ ምን ችግር አለባቹህ? ለምንድን ነው አሁንም ተቋውሞ የምታደርጉት?” ብሎ ሲጠይቅ ተቋውሞ አድራጊው ጥያቄው ያደረገው “የታሰሩት ይፈቱ! ለሞቱት ካሳ ይሰጥ!” የሚል ሆኖ ነው የተገኘው፡፡ ይሄ ማለትም ወያኔ ይሄንን ቢያደርግ ሌላ ችግር የለብንም ማለታቸው ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ይህ ተቋውሞ የተከፈለለትን ዋጋና የተገኘውን ሐሰተኛና ጊዜያዊ ውጤት ተመጣጣኝ እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡ ይህ ከተፈለገው ውጤት እጅግ የበዛ መሥዋዕትነት ዋጋ የመክፈል ችግር ወይም ኪሳራ ሊፈጠር የቻለውም አመራር ለመስጠት እየሞከሩ ካሉት ኦነግና ኦነጋዊያን የአመራር ብቃትና ብስለት አለመኖር ችግር የመነጨ ነው፡፡ በእውነት ነው የምላቹህ በሰው ደም ይቀልዳሉ ምን እንደሚፈልጉና ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ አይደሉም፡፡ ለዚህ ነው ከላይ ተልካሻ ምክንያት አንግቦ መነሣት ተቃውሞው ከአስፈላጊው ግብ እንዳይደርስ ሕዝቡም ጽናት እንዲያጣ ያደርጋል ያልኩት፡፡

ስለሆነም ይሄንን ተቃውሞ እያስከፈለ ካለው መሥዋዕትነት በተመጣጣኝ ለሀገርና ለሕዝብ ጠቃሚ በመሆነ መልኩ ማስኬድ ከተፈለገና ውጤት እንዲያስመዘግብ ከተፈለገ የተቃውሞውን ምክንያት ከተልካሻነቱና ከኢአመክንዮአዊነቱ ወደ በሳልና አመክንዮአዊነት ደረጃ ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

እንዴት ነው ወደዚህ ደረጃ ከፍ ማድረግ የሚቻለው? ከተባለ ተቋውሞው በመጀመሪያ ደረጃ ወያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይፈልገው፣ ሳይፈቅደው፣ ሳይመርጠው በኃይል ተጭኖን በኃይል እየገዛ ያለ አንባገነን አገዛዝ መሆኑን አበክረን በማንሣት ሥልጣንን ለሕዝብ እንዲያስረክብ በመጠየቅ ነው ጥያቄያችንን ተቋውሟችንን ወደ ተገቢው ደረጃ ከፍ ማድረግ የምንችለው፡፡ ይሄንን ጥያቄ ካነሣን ወያኔን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ሥልጣኑን መብቱን ነጥቆ የወያኔ አሽከር የሚያደርገውን ሸፍጠኛ የመሬት አሥተዳደር ሕግና ሥርዓቱን እንዲያነሣ እንዲቀይር መጠየቁ የግድ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፡፡

ይህንን ማድረግ ባይቻልና ችግሩ ሀገር አቀፍ ሆኖ እያለ ልክ በአዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ ላይ እንደተፈጸመ በማስመሰል ትልቁን ጥያቄ አኮስሶ ቆንጽሎ የጎጥና የዘር ችግር እንዲሆን እንደተደረገ ቢቀጥልና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን የዚህ መሬት ጉዳይ የማይመለከታቸው ጭራሽም እንደ ባዕድ እንደ ወራሪ ተቆጥረው “ባሕላችንን ቋንቋችንን… ሊያጠፉብን!” ምንትስ እየተባለ ኢትዮጵያዊያንን ባይተዋር እንዳደረገ፣ የተቀረው ኢትዮጵያዊ ነገሬ ጉዳየ ብሎ እንዳያስበውና እንዳይተባበር እንዳደረገ ከቀጠለ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኘ ልነግራቹህ የምችለው ይህ ተቋውሞ የትም አይደርስም!

በሁለተኛው ነጥብ ላይ የተነሣውን ስናይ፡-

ሁሉም ባይሆኑም የተቃውሞ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉ ወገኖች በተለያየ መንገድ እየገለጹት ካለው መፈክራቸው እስከ ግባቸው ድረስ ከሚናገሩት ተነሥተን ስንናገር ፍላጎታቸው ኦነግ ዓላማው አድርጎ ሲሰብከው የኖረው ጉዳይ እንዲፈጸም ነው፡፡ በብዙኃን መገናኛዎች ይሄንን ተቋውሞ ለመምራት ጥረት እያደረጉ ያሉ እራሳቸውን እንደ ኦሮሞ የሚቆጥሩ ድቃይ ኦሮሞ ልኂቃን ኦነግ መሆናቸውን በግልጽ ባይነግሩንም ኦነጋዊያን መሆናቸውን ግን በተለያየ ጊዜ ይፋ ካደረጉልን ዓላማና ግባቸው በመነሣት አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል፡፡

ኦነግና እነዚህ ወገኖች ብልህና አስተዋይ ባለመሆናቸው የአመራር ብቃት የሌላቸው በመሆናቸው ምክንያት ይሄንን ቀርቃማ አጋጣሚ ከንቱ ሊያስቀሩት እንደሆነ እያየን ነው፡፡ እነዚህ የተማርን ነን የሚሉ ግለሰቦች “ችግሮችን እንዴት እንፍታ?” በሚለው ነጥብ ዙሪያ ከአንድ ካልተማረ ደንቆሮ ደጋፊያቸው የተሻለና የተለየ ሐሳብ ማመንጨት የማይችሉ እጅግ በሚገርምና ግራ በሚያጋባ ሁኔታ መማራቸው ምንም ያልፈየደላቸው ሰዎች ናቸው፡፡

ዋነኛው ምክንያትም እነኝህ ግለሰቦች በግልም ይሁን በቡድን በተለያየ መንገድ ሲገልጹልን በደም ፍላትም ሲዝቱብን እንደኖሩት አቋም ዓላማ ግባቸው ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ፀረ ወዘተረፈ. እንደሆነ ሲያረጋግጡልን መቆየታቸው ነው፡፡ አስቀድሞ በሽግግሩ ወቅትም በተለያዩ ቦታዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸም እጃቸው በደም የተጨማለቀ መሆናቸውን እስከ አሁንም ድረስ ለዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀላቸው ይቅርታ አለመጠየቃቸውንና መጠየቅም የማይፈልጉ መሆናቸውን እናውቃለን፡፡

ይህ ሁሉ ነገር እያለ እነሱም ብልጥ ሆኑና ምን ሲያደርጉ ምን እያሉም ሲዝቱብን እንደኖሩ ጨርሶ እረስተውት ተቋውሟቸውን እንድንቀላቀልና ተባብረን ወያኔን እንድንከላ እንድናስወግድ አበክረው በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡ ያለ ትብብር የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ግንባር ሳይፈጥር አንድ ዓላማ ሳያነግብ ወያኔን ማስወገድ መንቀል አለመቻሉን መረዳታቸው መልካም ነገር ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ዓለማ አንግቦ አንድ ግንባር ፈጥሮ በወያኔ ላይ እንዲያነጣጥር የሚያደርገውን የቤት ሥራ ሳይሠሩና ይሄንን የቤት ሥራም ለመሥራት ጨርሶ ፍላጎቱ ሳይኖራቸው ይሄንን ትብብር መጠየቃቸው ግን የቂል ቂል ያሰኛቸው እንደሆነ ነው እንጅ ብልጥ የሚያሰኛቸው አይመስለኝም፡፡

እነሱ ማለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ያልተለዩ የጥፋት ኃይሎች መሆናቸውን ነጋሪ መፈለጋቸው እጅግ ያስገረመኝ ጉዳይ ነው፡፡ እነኝህን ወገኖች መጠየቅ የምፈልገው ጉዳይ ቢኖር እስኪ እንዲያው በሞቴ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ እናንተን ከወያኔ የተለያቹህ የሚያደርጋቹህ ምንድን ነው? ከወያኔ ጋር የአንድ ሳንቲም ገጽታ ሆናቹህ እያለ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዲተባበራቹህ ለመጠየቅ ምን የሞራል (የቅስም) ብቃት አላቹህ? ወያኔ በቆመበት የጥፋት ጎራ ከወያኔ ጋር ቆማቹህ አብሯቹህ የቆመውን ወያኔን ለመውጋት ለማጥፋት የኢትዮጵያን ሕዝብ ትብብር መጠየቅ ይቻላል ወይ? የትኛው አመክንዮ የትኛው የሞራል (የቅስም) ሕግ ነው ይሄንን የሚለው?

እውነት ይሄንን ሕዝባዊ ተቋውሞ የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብም ተቀላቅሎት የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ የምትፈልጉ ከሆነ ማድረግ የሚገባቹህ ጉዳይ መሥራት የሚገባቹህ የቤት ሥራ ከወያኔ ጋር አንድ የሚያደርጋቹህን የጥፋት ዓላማና ተግባር የተቀረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አታላቹህ ግባቹህን ለማሳካት ከመፈለግ ከመቋመጥ ሳይሆን ለናንተም ለሁላችንም የማይጠቅም ከንቱ የጥፋት ዓላማ መሆኑን በሚገባ በመረዳት ጣል እርግፍ አድርጋቹህ በመተው የአንድነቱን ኃይል ፈጥናቹህ ተቀላቀሉ፡፡ ይሄኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ በእናንተ ላይ ያለበትን ከፍተኛ የጥርጣሬ መንፈስ ይገፍና እርስ በእርስ መፈራራቱን መጠላላቱን ትቶ መተማመንን ይፈጥርና ፊቱን በአንድ ወደ ወያኔ እንዲያዞርና ወያኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅሎ ለመቅበር እንዲችል ያደርገዋል፡፡

ይሄንን ወሳኝ እርምጃ ሳትወስዱና መውሰድም ሳትፈልጉ ሰይጣናዊ ዓላማቹህን በልባቹህ እንደቋጠራቹህ “የኢትዮጵያ ሕዝብ! የኢትዮጵያ ሕዝብ!” እያላቹህ ብታላዝኑ ግን ከንቱ ማላዘን በመሆኑ የሚሰማቹህ አይኖርምና በከንቱ አትድከሙ ማለትን እወዳለሁ፡፡ ሕዝብን በከንቱ በማስጨረሳቹህም እጅግ አዝናለሁ፡፡

እራሳቹህን በዚህ መልኩ አርማቹህ አስተካክላቹህ ተከታዮቻቹህን በተገቢው መንገድ መምራት ሳትችሉ ቀርታቹህ በጠባብነት ገመድ አንቃቹህ በእርስ በእርስ ጥላቻ ወጥራቹህ እንቅስቃሴው ምንም ስኬት ሳያስመዘግብ በወያኔ ተደፍጥጦ ቢቀር ነገ ይህች ሀገርና ሕዝቧ በከንቱ እንዲያልቁ፣ እንዲቆስሉ፣ እንዲታሰሩ፣ እንዲንገላቱ፣ ግፍ ሰቆቃ እንዲፈጸምባቸው ላረጋቹሀቸው ወገኖች ከወያኔ እኩል ተጠያቂ ያደርጓቹሀል፡፡

ይሄንን ወሳኝና ጠቃሚ እርምጃ መውሰድ ባለመቻላቹህ ሕዝባችን በወያኔ ላይ ሊወስደው የሚገባውንና የሚችለውን እርምጃ በመውሰድ ወያኔን በአፍ ጢሙ ደፍቶ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመቅበር እራሱን ነፃ እንዳያወጣ፤ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለዘለዓለማዊ ቂም በቀል ዳርጎ የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥልን የብሔር ወይም የእርስ በእርስ ግጭትንና እልቂትን በመፍራት ወያኔ የሚያደርስበትን ልክ የሌለው ግፍ በጸጋ እየተቀበለ እንዲኖር በወያኔ ላይ እንዳይነሣ አድርጎ አስሮና ኮድኩዶ ይዞታልና የእርስ በእርስ ግጭትን ወይም እልቂትን በመፍራት በዝምታ የወያኔን ግፍ እየተቀበለ ላለው ግፍ ሁሉ ተጠያቂዎች ናቹህ፡፡

ሕዝባችን እስከዛሬም ይሄንን የወያኔን ትቢያ ቡድን መንቀል መደምሰስ ማጥፋት ተስኖት አልነበረም ይሄንን አደጋ በመፍራት እንጅ፡፡ ወያኔም ያለውን ደካማ አቅም ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው እንደእናንተ ያሉትን የጥፋት ኃይሎች በመጠቀም ይሄንን የእርስ በእርስ እልቂት አደጋን በመጋረጥ ሕዝባችንን እርስ በእርሱ አነካክሶ እንዲፈራራ በማድረግ ዕድሜው እንዲራዘም ሲያደርግ የቆየውና አሁንም ያለው፡፡

እናንተ ይሄንን መውሰድ ያለባቹህን እርምጃ አለመውሰዳቹህ ወያኔ ይሄንን ሕዝባዊ ተቋውሞ አቅጣጫ በማሳትና እሱ ተጠቃሚ ወደሚሆንበት አደገኛ ሁኔታ ለመውሰድ እንዲቀለው አድርጋቹህታል፡፡ እውነት ይሄንን የወያኔን ሰይጣናዊ ሸፍጥ የምትጠሉና እንዲሆንም የማትፈልጉ ከሆናቹህ እባካቹህ ስለ እግዚአብሔር ብለን እንለምናቹህ ፈጥናቹህ ሳትዘገዩ ከወያኔ ጋር አንድ የሚያደርጋቹህን የጥፋት ዓላማ ጥላቹህ የአንድነት ኃይሉን ተቀላቀሉና የወያኔን ሰይጣናዊ ሸርና ሸፍጥ እናክሽፈው ነቅለን ለመጣልም እንቻል???

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

[email protected]

 

 

45 Comments on “ለኦነግና ኦነጋዊያን – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው”

  1. ለወገናችን መድረሥ አቅቶናል የታል ሀገር አድኑ ወያኔን ለማሥወገድ እየተከፈለ ያለው መሥዋእትነት የኦሮሞውና የጎንደር ህዝብ ብቻ ነው እንዴ ሀገር እንዳትሸጥ ከአባቶቹ አደራን የተቀበለው ወይሥ እንደ ትግራይ ወያኔ እና ሻብያ የሀገር ባንዳ ሄንን የታል…..

    ኦህዴድ ሆይ ትጥቅህን ፈተህ ልጆችህን አድን አፈሙዙን አዙረው ቁላው ወያኔን።

  2. የብሄር ፖለቲካ ጉድ አፍልቷል በአንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ተማሪዎችን ሆን ተብሎ እርሥ በርሡ ማን የማን ጎሣ እንደሆነ እንዲተያይ ያረገ በባህል በብሄር ሥም የሥነ ትምህርት አላማው ጎሣ መር አድርጓል ።

    እንዲሁም በዩኒቨርሥቲ ምደባው ብሄር ተኮር አደረጃጀትን በተከተለ ከየብሄሩ በማጣረዝ ቡድም እንዲመሠረት እና የተማሪ የብሄር ካድሬዎች እና መምህራንን በማሠማራት ትውልዱን ለ10 አመት በበለጠ ከፍተኛ ችግር ውሥጥ ገብተናል ይህም ትውልዱ እንደሀገር ሣይሆን እንደብሄር አሥቦ በክልሉ ብቻ መኖር መሥራት እንደሚችል በሚያረጋግጡ አደረጃጀት ተተብትቦ ይህን የመሠለ ሥንቃር ውሥጥ ሀገራችን ገብታለች አሁንም ቢሆን ይህ ትግል የኦሮሞው ብቻ ችግር ሣይሆን የሁሉም ክልል ችግር ነው በጋራ በልማት ሥም እየተዘረፈና እየተሸጠ ያለውን መሬት ባለቤቶቹ እኛ ሥለሆን በየክልሉ ያለውን የዝርፊያ እሥትራቴጂ ልናሥቆም ሁሉም ኢትዬጵያዊ ሊረባረብ ይገባል የሀገራችንን መራት አልሚዎቹ ባለቤቶቹ እኛው ነን ማንም ከጫካ መጥቶ እኔ ነኝ የማውቅልህ ተነሥ ልጅህን እኔ አረብ አገር ልላክልህ በሚል የባርነት ድለላ ውየላና ውየናው ገብቶህ ግንባርህን ለጥይት ደምህን ለሀገርህ እየከፈለ ያለው አርሶ አደር ያበላን እጁ በሬውን የገረፈበት እጁ ይፋረደናልና ሁላችንም የወገን እንባን እናብሥ።

    ሞት ለወያኔ ወያኔም ይወገዳል

  3. Amsalu or whatever your name is (don’t need to put your BS ot self-appointed title similar to the title of your “Professor” ):

    You are nothing but a Wolf in sheep’s clothing as an idiom of fable used in Biblical metaphor. It is used of those playing a role contrary to their real character, with whom contact is dangerous.

    You are choreographing your deep-seated fear and hate of the Oromo people. Sooner or later Oromos will look at the contempt of the likes of you in a rear-view mirror.

    My guess is that you are scared of loosing the 500 squre meter Oromo-land the Woyanes or Tigre thugs or your masters have promised you – Just go away – Oromos are better off without the patronizing and ignorant comments and attitude. I bait you are prepared to suck up to your Tigre (TPLF) masters at the expense of the blood and treasure of the Oromo – Just get lost!

  4. Alem betelym yetebaberut
    megstat ye tgrai woyanie
    ethiopiawiyann eskichersachew
    new zm blo yemiyay ?
    Be aTeqalay be yebotaw ye tgrai
    woyanie be ethiopiawiyan lay
    quami Tornet awajo be agazi Toru
    eychefechefe ye sudan darfur ena
    ye libiya (gadafi) aynet chfchefa
    be ethiopia hzb eyederes new.
    Yhn eyaye zm maletu lemn yhon.?
    MasTenqeqiya mesTet alebet.
    Eyederese yalewn elqit lemasqom
    bewetaderawi hayl Talqa
    lemegbat zgjt madreg
    ena masTenqeqiya mesTet alebet.
    Gobez ebakachuh beqrbt
    hunachuh asasbut, wetwtut,
    temaTenut.

    Mot le tgrai woyanie.

  5. Thank you, Amsalu,those OLF leaders are some of them ignorance, and all of them narrow mind.Look at Juhar Mohamed he wants kill none Muslim people by menccha.TPLF and OLF what is different? .

  6. This man is the one who dance on Woyane television so Called Ethiopian Television on Balehageru Idol if you want to check google it.He is the customer of them.thus why he cries the day of his master numbered.

  7. Mr Amsalu,
    I found your comments on the current Oromo students’ movement to be silly and immature. Rosa Park didn’t declare war overnight on white supremacy in the United States. It all started with a simple act: Montgomery bus boycott eventually engulfing the whole nation. Ghandi’s civil rights disobedience kicked off with the so-called salt march, providing a turning point in the history of India’s movement to independence. Mandel’s fight for the freedom of black South Africans didn’t involve many people at the beginning. It started underground with a handful of acquaintances. As soon as Mr Mandela became public, he faced brutal and dehumanizing treatment and three decades of imprisonment. Yet, South Africa became free.

    The Oromo students have done their first homework by taking their struggle to the streets and forcing Woyane to temporarily reverse it’s policy on the master plan. While this is the most persistent challenge put on Woyane sofar, i have no doubt that they will gradually become more organized and slowly start to involve other Ethiopians. Trust me, this fight is not going to go away despite the torture, killing and imprisonment. The seed of freedom has been planted. So, i suggest that you leave the Oromo alone and keep sharpening your pencil.

    Selam,
    Ke Debire Birhan

  8. @Amsalu,

    It is nice and expected from any Ethiopian to be concerned about the country and the direction where the administration is leading this country of us. There are many who write a lot about issues and their solution – it is questionable if all the writings are for the goodness for the goodness of the entire population or based on hatred against the others.
    I have followed your writings many times and it is so clear that where you are coming from and where you are heading. Your comments and writings are either trying to criminalizing all Tigrai people or to demonize the Oromo people. That shows that you are totally out of touch of the truth on the ground and trying to implicitly expressing your hateful feeling about these two groups using new news or events that come up in the media.

    I am sure you clearly knows that the current uprise in Oromia is not masterminded by the OLF. It is the general public grievance against the injustice rule of the TPLF/EPRDF. But you try to express your hatred to the organization on the topic and the scenario which has nothing to do the organization. Let you do not try to level down this big case to a single organization level. The Oromo resistance is bigger cause covering from one corner to the other in all villages and towns.It is much bigger than act of a single organization.

    Secondly, you wanted the Oromo people to sing with you about Ethiopia. No single Oromo is less Ethiopian than you and your likes. But most of them put it aside because of you and your types. At this moment Oromo people have ignited the resistance which you have been scared off for years. et you tae it from their if you truy want to mae it an issue of the entire nation.

    Rest in peace!
    Giday

  9. Ato Amsalu ,,

    Oromo lefetemew wenjel yeqerta ayteyqem ere

    gena yefejunal,!!! Bekele Gerba ;amata dingay yezo yeqerta yeteyken selu alsemum ende Ato Amsalu

    ye Oromo tiyake, Ethiopia yemitbal Hager atiften oromeya,,! ADDIS aBEBAN ATIFTEN FINFINEN MESRITEN

    KEZA BE JAWAR MENCHA YEFEJUNALEGNA DEMO ;KKKKK BESO CHBITEN ENITEBIKACHWALEN

    AYZON kkkkkkkk

  10. @Amsalu;
    Let me ask you just one thing,are Oromos says no to any people not to uprise against this fascist woyane. You are either a joke or you helping woyane. Try to follow the information coming out there. Majority of the people agree now the division doesn’t help any body out except woyane. So instead of writing simply to write nonsense go ahead.

  11. I suspect the Dedebit cadre, Amsalu the moron, is an unsuccessful, half baked, failed artist who is in search of a suitable profession for his low IQ. Thus he started scribbling this “masterpiece” to impress his Weyane bosses and land top position . Galtu Amsalu, Hadgi!

  12. Mr. Amsalu has shown his deepseated prejudice and contempt for the Oromo. His piece is simply rubbish, and should be discarded altogether.

  13. Artist Amsalu,
    your article is very fascinating and a rebuke to the whole saga of “oromo students rebellion” promoted and driven by ethnocentric forces on the backseat.
    Your reasoning is well meant and reasonable to unseat the Woyane junta once and for all. I totally agree with you that there is no much difference except name between Woyane and OLF and Co. The guys like Juhar Mohammed even raise the stake into sectarian dimension. Ethiopia is an old nation where nation building was organically done unlike colonized people. The recent up rise following the expansion project of Addis Ababa and the largely silent population of Ethiopia is a testament how the Ethiopian people are not easily hijacked by self made ethnocentric idiots.
    Despite the Diaspora media (such as ESAT) hype, I found out different stories back in home that ordinary Ethiopians are not buying the merit of the recent debacle. As you correctly mentioned it, the people are wary of the ethnic dimension of the up rise while the entire nation is under similar serfdom exploitation, arbitrary eviction and wholesale takeover by a few connected with the regime.
    That wrong headed ego by the OLFites simply backfired and used as a tool for Woyane to continue dividing and rule as usual. In my view, unless we divorced with retrogressive ideology of TPLF, EPLF and OLF (ethnic consciousness), the suffering of the Ethiopian people will definitely long last even our grand grand children. We accept it or not, the bitter truth is nothing further than this. Yes you called the so called “educated people” are no more smarter than the average ones, and I rather call them power hungry, brainwashed, militant pseudo intellectuals who happen to come to this world much much later than their generations in the stone age. They are not fit in the age of consumerism and knowledge economy where the abundance of population maters. They called themselves intellectuals, but not able to read and decode the readily available data how growth and the size of population are proportionally interconnected. At the time where EU is in breakneck struggle to expand, US sweating to forge Transatlantic and Transpacific trade relationship, BRICS knotting economic tieup – our retards are bleeding to blow up existing relations. What a contradiction!
    I think the Ethiopian people have got enough lesson from the session of Eritrea and consequent loss of the strategic Red Sea coastline and will not allow that same insanity one more time again. If we are to shade tears and blood, it will not be for installing another version of Woyane, but for complete eradication of Woyane and its retrogressive ideology called ethnic consciousness! We will not settle for anything less than every citizen has equal right and privileges wherever he / she may be, a government by the people for the people, a right for pursuit of happiness, liberty, and justice for every citizen regardless of religion, language or social status, a national defense forces answerable to the Ethiopian people and a respected and proud Ethiopia under the banner of green, yellow and red flag. Call me Neftegna, and I will say yes I am Oromo clan Ethiopian Neftegna!

  14. Amsalun mtawegzu:
    1. Andm woyaniena oneg nachuh.
    Mkniyatum artist amsalu ejg
    Tere-woyanie new. Ejg bzu gizie
    betedegagami woyanien
    bemawgez, bemagaleT ena le
    Tere-woyanie tagayoch mkr
    bemaberket yetaweqe new.
    2. Weim mtawegzut hasabun
    satredu yetesasatachuh nachuh.
    Mkniyatum kezih lay Tfot
    yanebebnew hasabu minegren:
    be oromowech lay yederesew
    chfchefa endasazenew gelTual.
    Neger gn yh hulu mesewatnet be
    tkkl bimera nuro yegar Telatachn
    woyanien ydemess neber,
    alemetadel hono tru amerar
    bemaTatu woyanien saydemess
    liqer new bemalet quchtun glT
    argual. Ahunm woyanien
    endndemess ebakachuh Tyaqiewn
    ye oromo bcha asmeslachuh
    ataqrbut silm temaTnual.
    Ye mulaw ethiopia adrgut ena
    hulum
    ethiopiawi enditebaber Tri aqrbu
    new yemilen.
    Eniem ende amsalu:
    tgrai woyanie ye hulum yandnet
    felagi ethiopiawiyan Telat new.
    Hulum ethiopiawiyan Tyaqieyachn
    woyanien tebabren enaswegdew
    ena le hulachn bekulnet
    yemtTeqm adisuan andit
    ethiopian enaquaqun elalehu.
    Mot le tgrai woyamnie.
    Dl le adisua ethiopia Tere-woyanie tagayoch.

  15. I think it is important to consult in private ato Tesfaye Gebreab (aka Gaada) who is an expert on the mentality and psychology of the oromo elite or intellectuals.He would tell you in private conversations that the Oromo elite and intellectuals are very emotional and easy to manipulate and abuse. He blames these short comings of the Oromo guys on the demoralizing and oppressive Amhara rules and would tell you that he is working hard to help them overcome them and build self confidence.The Gaada is smart and had acquired a lot of knowledge on the weakness and vulnerability of Oromo elite and intellectuals.

  16. Seali Amsalu,
    Your long article contains a lot of good ideas that will help the nation. You also provided an in-depth analysis of the situation. There, however, things that did not come out clear. I will rasie some of these to you. What can the Oromoo People do to make the current issue a national issue? For instance, you mentioned the land and eviction problem in Bahir Dar city area. Who you think should protest on this? Should Oromoo go there and encourage the victims for uprising? How do you think it will be possible to raise a nation-wide question or make it a nation wide question when others (nations and nationalities)could not move a single inch to join the Oromoo people? Do not you think it needs to stand and die together. You have not analyzed or hinted on why other people kept quite the last 2 months. If the Oromoo people is uprising against dictatorship in the nation, why is that not considered as a national question or a nationwide issues? In your thinking you seem to downgrade the rights issue, in a wide range of its dimensions, the Oromoo is raising to “master plan’. More dangerously, you dare to blame people labeling the protestors as if they take instructions for action from the OLF. This is similar to what the Government is saying right now to justify its acts of massacre perpetrated on the innocent Oromoo people. Do not you think you are, indirectly, contributing to the Government’s arguments? The worse, you say people are ignorant. It is the people, whom you call ignorant, who have been living under tyranny for decades and rising up to get rid of it now. People can ask for its rights in its own terms. It is not a matter of being an elite or intellectual. Your article has missed its line. No body said, and you do not have an evidence to say that the current popular protest in Oromia is led or agitated or directed by the OLF or related, as you wished to say. We did not see or hear, either, where OLF has claimed responsibility for this massive event that is happening in Oromia now. You need to revisit your assertions and get your pints clear.

  17. 1.eyetederege yalewun techebach huneta kalemawek
    2.kechifin tilacha
    3. gize kalefebet hoalaker astesaseb yemeneche hasab hono agengichalew. mikiniyatum:
    1. tekawumowun yasnesaw yemerawum beginbar kedem hizbu bicha new
    2. sile bahir dar beginbar kedeem mekawem yalebet yebahir dar hizb nw inji lela mehon aychilim
    silehonem wey kelay ketetekesut andu wey demo yewewane telalaki neh

  18. OLF dekama new hulum ye Ethiopia hizb yawkal 60amet yale minm wtet ye gosa zer chigr alebet ke hulu belay wgya aychilm ke woyane sinetsatser 0 le 100 new camp wist asgebto referefew jawar amerarun meyaz alebet gragn Mohammedn liteka ychilal meslotal AGAAZI rasun ende koblstone ferkso new yemiwlew esat poletican medeberiya aderegew mehon yalebet hulachin ethiopian tekebabren hulum bhereseb ekul new agerachin masadeg oromo tigre amara eyaln gizeachin anatfa yeahun poltikegnoch hizubun medeberiya aderegut yesamntu engida tikuret eyalu rasachewn betesebachewn yastedadralu yimechachew ebc esat hizb mehel lay yigalbal be heger keld yelem entebaber

  19. I fully agree with your post.
    For example in this movement around Adaba town a hotel of an Amara (Ethnic) was burns by Oromo people similarly in last year in Ambo it was occurred. in 1985EC more than 1000 amahar was assasinated in bale and Aresi by OLF. If god help me i will publish a book which will talk about this brutal done by OLF on Amahar

  20. @Addis, Fuck you, you Adwan bastard. It is because of you we Tigrayans are alienated, you savage, greedy, incompetent Weyane. Leave us in peace.

  21. @Hagos,
    You little mind ascaris go and fix your Eritrea aka the North Korea of Africa. Leave us alone, and be advised that you have no the moral as well as the intellectual power to advise Ethiopians.
    For Shabiya brainwashed OLFites, I advise you in our fable “Manni abbaan gube abbaa hube.”

  22. To: Amsalu, Waquoo, Kaleab and all the other “AMARA Menga”

    It is sad that you are spreading your Amhara venom to satiate your fear, hate and contempt towards the Oromo. Regardless of your highland “debtera” intrigue on behalf of your Tigre masters, the Oromo will, sooner or later, come out triumphantly.

  23. Sm jaloo yalk:
    juwar neh lbel wois lencho.
    Wonjel tdefraleh, endiet
    wonjeleña luTi ye zegemte
    angolu ye sbhat nega yechn gered
    yeneberechwn tesfa gerbebab
    tTeqsaleh.
    Endiets dro kesnt zemen befit
    yemoten yetewogeden ye amara agezaz, nefTeña malet felgeh kehone (amara rulers blehal).
    Chnqlatkn neka yaderghal lbel?
    Kederg wdqet jemro eyegezah,
    amaranm eyegeza yemigeñew ye
    tgrai neTa awchu tgrai woyanie
    new enj amara aydelem.
    Amarama enkaun ligeza
    beTeqeskew gebrebab qesqashnet
    be woyanie, oneg ena ohdd1opdo
    techefchfo yezer maTdat
    feTmachuhbet medresha Teftobet
    ygeñal.
    Le techemari wonjel etezegajeh ymeslal.
    Mot le tgrai woyanie, mot le oneg, mot le opdo.
    Dl le andnet hayloch.

  24. Gobez yh oneg malet mn nekaw dro kezemenat befit yemotutn ywoqsal.
    Ahun yalenbetn chgr meredat tesnot dhazoyedha ljoch, enjera
    flaga minkeratetutn amaras ychefechfal yaschefechfal.
    Yebegoch amlak yfaredachuh.
    Ke tgrai woyanie gar temesasay nachuh.
    Bn yargachuh.
    Yegebawn Telat ye tgrai woyanien maswoged aqtonal, be liela oneg bemibal ye woyanie diqal lntekaw befeTum anfelgm.

  25. Gobez yh oneg/olf malet mn nekaw dro kezemenat befit yemotutn ywoqsal.
    Ahun yalenbetn chgr meredat tesnot dha-yedha-ljoch, enjera
    flaga minkeratetutn amaras ychefechfal, yaschefechfal.
    Yebegoch amlak yfaredachuh.
    Ke tgrai woyanie gar temesasay nachuh.
    Bn yargachuh.
    Yegebawn Telat ye tgrai woyanien maswoged aqtonal, be liela oneg bemibal ye woyanie diqal lntekaw befeTum anfelgm. Mot le tgrai woyanie

    mot le oneg/opdo

  26. Gobez yh oneg/olf malet mn nekaw dro kezemenat befit yemotutn ywoqsal.
    Ahun yalenbetn chgr meredat tesnot dha-yedha-ljoch, enjera
    flega minkeratetutn amaras ychefechfal, yaschefechfal.
    Yebegoch amlak yfaredachuh.
    Ke tgrai woyanie gar temesasay nachuh.
    Bn yargachuh.
    Yegebawn Telat ye tgrai woyanien maswoged aqtonal, be liela oneg bemibal ye woyanie diqal lntekaw befeTum anfelgm. Mot le tgrai woyanie

    mot le oneg/opdo

  27. Ato Amsalu
    Ande 2 tiyaqe lexayeqot ende?
    Malkam Faqadanga Kahonu……
    1.Kazih Bafit La Shabiyaw Mari Ato Esayas Afawaqi Yaxayaqut Xiyaqe Tamalasalot? Malate SilaErtiria Hizb Aquwamena OLF,Gibot 7,TPLF lelochim patiwoch Guday yaloten Xirxare…..malate naw…….
    2.Anta Raseh Kawadet Nah….Malate Sa’ali Sabaki wayes tazabi….etc
    Ene Bezum Altamarkum Bech Antan Chamero Tamarn Yamilu Hulu Yafaru Yemaslalu…..Abatochen Alalkum Gen ……
    “Madaniyalem Eyasus Kerstos” ferat Alastamaranem Anfaram
    “Blue Kidanen Ena Addis Kidanen”Astarqul “Ene Samrawi Ante Ayehud Endet Wuha Texayiqangaleh……..Damom Gudgudu Xelqe Naw Maqeja Enkuwa Yaleh Bamen Teqadaleh& Ante Ka Abatachin Yaqob Tebalxaleh” Alachiw…..
    1.Maqeja Yelah yalechiw ewunatun naw Zare Ya Ethiopia Hizb Ande Muse Yalahum Hulum Sabara Maqeja naw Enena Antan Chamro Malate naw? Ande Muse Mari Binor Noro Ya Ethiopia Hizb Wuha Balxamaw nabar Man Wuhawun Qadeto Yatatan Ka Beranaw,Kagadelatu,Katamratu.Ka adebaratu,Ka Betakerestiyan……Nachoch Enqelf Yaxulat Ethiopia Tafaxero Habtuwa Malate naw….
    2.Madaniyalem Eyasus Kirstos Ya Yaqobe Amlak Mahonun Ataweqem nabar. La Andandoch Zarem Ka Madaniyalem Yaqobe Yebaxal(La Andandoch Zare Talkasha Party….
    “Ka Madaniyalem Eyasus Kerstos Yebalexibal”) yeqerta “Liqa Kahen Eyasus Kerstosn” Kapary Gar Lamawadadar sayehon “Enen Bamaqalu Kasaqalach Medir Enanta min Texabeqalachihu Belo Astameronal”……silazih KA 2000 ya Ethiopiawiyan Abatochachin Tarik Ya Samonu Talkasha Party wakaba Asfarachew Wagane…..Sigaban Enda TPLF& OLF Mastar Plan &Behertengenaten Sayehon Enda Abatoch Mariwochachin Sandaquwan & Ya Ethiopian Andenat Ka Caf Caf La Alam Ensabkalen Enastameralen…Dagamom Faran Anaweqem……
    Bamcharasham Ya Ethiopian Andenat Lamimangu Hulu Balubat Emabrehan Texabeqachew……Fatari Char Yasamachihu….

  28. All Woyane mercenaries, the likes of Amsalu, Kaleab, & Waquoo are working overtime. The gallant Oromo children, have become your nightmare. To respond to your semi-cooked, illiterate and dark comments deserve no response – Get Lost – I am done with you!

  29. Obbo Waaqoo,
    Dubiin koo siif galle jedheen abdadha. Makmaaksi assin olliti jette/ jettan naaf hin galle fakkaattaa mee irra deebi’aa naaf ibssaa. Oromoon waan kittaaba tokko ta’u makmaaksa gababdudhaan ibssa.

  30. jaleta አንት የወያኒ አሽከር የደብተራን ያክል እውቀት ቢኖርህ ኖሮ የፈረጅ አሽከር ባልሆንክ ባንተቢት የሰለጠንክ መስሎህ አምሃራን ማዋረድህ ነው የደብተራን እውቀት ለመማር ወያኒና አንተ ቂጡን የምትልሱለት ፈረጅ ለማወቅ አክብሮ ይመራመርበታል ይማራል ከደብተራ እውቀት ይወስዳል ደፍተራን ሆነህ ቢሆን ኖሮ የኒ የምትለውን ኦሮሞ አገሩን ለወያኒ ባንዳ ተባብረህ ሰተህ ደሙን ባላስፈሰክ ወያኒ የማንን መሪት የያዘ መሰለህ ትልቃን ለብዙ ሺ ዘመን የነበረችውን ኢትዮፒያ ነው እንዳተ አይነቱን ኦነግ እና ኦህዲድ አምሃራ የወሰደባችሁን መሪት አስመለስኩላችሁ እያለ ፎጋግሮ ከፋፍሎ ከፈረጅጋ የሚሸቃቀለው የኦሮሞ መሪት ነው እያለ መሰለህ ? ኢትዮፒያ ትልቅ መሪት አላት እድሚ ለአጺዎቹ እድሚ ለደፍተራዎቹ እነ Jaletan (ኦህዲድ ,ኦነግ) ፍርፋሪ ወርወር እያረኩ ብሸጠው ምን አባቱ ይሆናል ያለህ ወያኒ ነው አንተ አምሃራን ደብተራን የአጺዎችን ስረአት በጋራ ገለን ቀብረን ኢትዮፒያን እንደ ኪክ ቆርሰን እንገምጣለን ለደሃ ኦሮሞ ደግሞ ዳቦ እናበላዋለን ብለህ አስበህ ነብር ከወያኒ ያለምከው ህልም ዛሪ ደግሞ መልሰህ መላልሰህ አምሃራ ትላለህ መሳቂያ ነህ አሁን ያለህ ችግር ከወያኒ ጋር እንጂ ከአምሃራ ጋር እና ከደብተራ ጋር አይመስለኝም ወያኒ የኦሮሞ መሪት ነው ብሎ እንዲሰጥህ ነበር ለትግሪ መሪት ባድሚን ለማዳን ኦሮሞን አሰልፈህ ያስጨፈጨፍክው ?መሳቂያ ነህ ወያኒ አንተን ቆልፎ መግደያ ክልል እንጂ የፈለገው አይ አገር መጥቺ አከፋፍዪ እኒም ወደ ትግሪዪ ወደሞትኩለት ህዝብ እሂዳለው ዋናው እንካን ኦሮሞ ከአምሃራ ነጻ ወጣ አላለም አልሰማህም የወያኒው የውጭ ጉዳይ ሚንስተር በ VOA የተደረገላቸውን ቃለ ምልልስ በህወሃት ምክንያት ያንድ ዘር የበላይነት የለሞይ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች በነማ እንደተያዙ ይታወቃል ወይስ አንቀስ 39 ተጠቅማችሁ ትገነጠላላችሁ ወይ ነበር አንድ ጎበዝ የጠየቃቸው ይህን ለመመለስ የሰጡት መልስ ነው ለኒ ያስደነቀኝ የብሂር ጥያቂ ተመልሳል ስለዚህ ለምንድነው ትግራዊነት ,ወላሞነት , አምሃራነት….ኢትዮፒያዊ የማይባለው ለምንድነው የኦሮሞ ስም ሲነሳ ሲገን መገንጠል የሚታሰበው ኦሮሞ ኩሩ ኢትዮፒያዊ ሆኖ መኖር የማይችለው ነው ያሉት Jaleta ኦነግና ኦነጋዊያን ወያኒ ከመጣ ኩሩ ኢትዮፒያኖች እንድትሆኑ አርገው እንደሰሩ ነው የገለጹት አንተ አሁንም አምሃራ መንጋ ድፍተራ እያልክ አፍህን ትከፍታለህ እሳቸው እንደውም ለአምሃራ እኮ ሲመውሰክሩ አምሃራው ችግር የለበትም እራቁቱን እየሂደ ላገሩ የሞተነው ብለው መሰከሩ ምክንያቱም የሚቸበችቡት አገር ስላገኙ አንተ ያውም ፈረጅ አገር እየለመንክ እየኖርክ ሰው አገር መኖር ልመና ነው ምንም ሁን ምን በዘር እያሰብክ ህዝብ ባገሩላይ እንዲህ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ደም ስታስፈሥሥ አታፍርም ያውም እዚህ ኩጭ ብላችሁ የኦሮሞ መሪት ለኦሮሞ ብቻ ባእድ ባገራችን መኖር የለበትም ይውጣ እያልክ የሚቸበችብህን ወያኒ ትተህ ባገሩላይ ኮርቶ በቆሎ ተደስቶ የሚኖረውን ደብተራ አምሃራ አንተ የፈርጅ በርገር እየዋጥቅ የመናገር ሞራሉም አለኝ አትበል ታየህ እኮ ዶማ ራስ ነህ የወያኒ አሽከር

  31. Dear Amsalu,

    instead of criticising just as you mentioned on your article why dont you talk or write to Bahirdar farmers to rise with Ethiopian brothers?if you are truly think to Ethiopia but you are woyane supporter thus why you are not happy with the struggle for freedom From Gonder to Harar that shake woyane regiem.Woyane is the enemy of all Ethiopian.

  32. Oromians are more than enough by them self to bring down more than a century long habasha colonial domination for ever!!! Oromians not beg any one to join uprising for human freedom it is up to them weather to join or not to join. Ethiopia is only colonial phenomenon of 19th century please read history. Who ever continue living with us in Oromia we don’t have any problem but we are not change because of others choices!!!!

  33. @ Artist Amsalu,

    If you all know who artist Amsalu is you will never be bothered to his trash talk. If a shop lifter in America is an artist then he is. He is a damn high school dropout
    “Tewozawash” turned “journalist”. Dinkem journalist.

    There is a saying in Amharic “ganoch alekuna minchetoch gan honu”. Let alone talking about a very sofisticated Ethiopian politics he even can’t comprehend what is going on in that country. He is leading a secluded life style in washington metropolitan area because every body knows him that he is a wuyane paid collaborator. He always opose the unity of Amhara and oromo. He is not only against OLF. He is also agsinst G7 only because G7 has a vast majority, modern and educated class from every ethinic groups in ethiopia.

    So my advice to both Amhara and Oromo moderates is forget about this trash guy. There is a political diference among us, Amhara and Oromo. My attitude is we work it out with great care and redpect for each other. We both face today an existencial threat from Wuyane/TPLF. America and soviet union have agreed to fight Adolf Hiller together during WWII. The SHOP LIFTER CAN’T UNDERSTAND THIS. To be honest to my readers I have to confess there are same kind of people who are radical and agsinst allaince making with Amharas from Oromo side too. But they are few uneducated.

    Let us grab this one in a generation oportunity of good will of Amhara and Oromo unionist. That is the only way we defeat wuyane.thanks.

  34. Yadisua yekulnet ager ethiopia
    ziegoch:
    ke eskahunu chwwt yetayew ye
    gara aquam:
    1, Tere-andnetochn quTr and
    yetglachn fetañ enqfat nachew.
    Enesum woyaniewoch bedbq
    teqawami meslew, taktik qeyari
    juwar ena mesel islam
    ashebariwoch ( ke oneg/olf, ke
    ohdd/opdo wsT yalu gleseboch),
    lielochm ende ene tefa gebrebab
    (ke eritrea) yalu nachew.
    2. Lieloch letglachn enqfatoch ke
    etiopia wsT huno tglun
    bequaminet astebabro lememrat
    aschegarinet, ye woyanie
    hgalbanet, moralyelesh bahrina,
    yetgrie agazi Torun hulunm
    etiopiawi yale mawelawel
    bekuratna bemeshamat
    lemechfchf mezegajetu new.
    3. Tere-tgrai woyanie tglachn
    befTnet ena banese kisara
    woyanien medemses yemischlen
    andnetachn aTenakren sntagel
    new mefthiew.
    4. Mntagelew tgrai woyanien
    lemegdel lemedemses enj
    lememot bechrash aydelem.
    Ejg belaqe gubzna ena belTet
    mehon alebet tglachn.
    Yechelemewn bemabrat ena
    beweldechn ethiopia ye abronet
    fqr yetgrai woyanien tbit
    bemedemses neTa mewTat new. Mot le tgrai woyanie

  35. አቶ አምሳሉ ለመሆኑ አንተ ከምትኮነነው ኦነግ የምተለይበት ምንድ ነው፧ ለመሆኑ የጻፍከውን ጽሁፍ መልሰህ ኣንብበሃል፧ ወይስ እንደ ጻፍከው ነው የለጠፍከው ፧ በኔ አመለካከት አንተ ከወያኔ የምትለይበት ቁም ነገር ቢኖር፤ ስልጣን ሳትይዝ በቃላት ሰው መግደልህ ነው። እንዳንተ አመለካከት ሁለት ኢትዮጵያ አለች። አንድዋ፡ የህዝቦችን መብት የምታከብር ገራገር ኢትዮጵያ ስትሆን፤ አንድዋ ደግሞ በስመ የኢትዮጵያ አንድነት ሌሎችን ቆርጥማ የምትበላ ሂትለርዋ ኢትዮጵያ ናት። አንተ የምታልማት፡ ሂትለርዋን ኢትዮጵያ ከሆነ፡ አሁንም አንዴ ሳይሆን አንድ መቶ ሺህ ጊዜ የምልህ፡ እስዋን እርሳት። ገራገርዋ ኢትዮጵያ ግን መገንባት ያለባት፡ ኦነግን ጨምሮ እነ ሞሬሽ ወገኔና ሌሎችም ሲፈቅዱ ነው። በነገራችን ላይ፡ የወያኔ በሃሪይ ያላቸው ብዙ አንድነታውያን እንዳሉ መገንዘብ የግድ ነው። ከነሱ መካከል ደግሞ ያንተን አመለካከት የሚያራምዱት ጭምር፤

    ለመሆኑ ደንቆሮ አመለካከት ያላቸው እያልክ ደጋግመህ የሰደብከው ህዝብ፡ የኢትዮጵያ ወገን ነው ፧ ወይስ ሌላ? ፧ አንድ ሁን የምትለውን ወገን መልሰህ ደንቆሮ ማለትህ፡ ያንተኑ ድንቁርና ከሚያስተጋባ በቀር፡ ሌላ ምንም መልዕክት አይኖረዉም። አንተ ደንቆሮ የምትለው ህዝብ መስዋዕት እየከፈለ መሆኑን ረሳኸው? ለነገሩ አንተ የደብቅከው የዘር ካንሰር ስላለብህ አይታወቕም። ሊገባህ የሚገባው ነገር፡ አንተና አንተን የመሰሉ ሰዎች አንድነት ከምትሰብኩ የጥላቻ በሽታችሁን እንደታቀፋችሁ ሙቱ። አንድ ነን? አዎ ፥፥ ምንም ከፋፋይ ቢበዛም አንድ ነን። አንድ አንደሆን እንቆያለን።

    ሌላው ምንም እንኩዋ ሁሉም የራሱን መንገድ ይዞ ለነጻነት ቢታገልም ይጠላላል ማለት አይደለም። የፓርቲዎች አላማ የግላቸው ሲሆን ኢትዮጵያ ደግሞ የሁሉም ናት። ስለዚህ ማንም ማንንም ይቅርታ ሊጠይቅ የሚችልበት ሁኔታ አልተፈጠረም። ህዝቦች ሁሉ ላለፈው ይቅርታ መጠየቅ ካለባቸው ከማን ቢጀምር የተሻለ ነው? ፧ እስኪ አንተ እዚህ ጽሁፍ ላይ ደንቆሮ ያልካቸውን ህዝቦች ይቅርታ በላቸውና አስተምረን። ከዚህ ውጭ ወያኔ ፪፭ ዐመት ለፈጃቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ ኦነጋውያን ሃላፊ አይደሉም። አንተ የምትለውን መቀበል ካስፈለገ፤ ኦነጎች የሚሉትንም መቀበል ሊኖርብን ነው። ያ ማለት ደግሞ በግልጽም ይሁን በስውር የወያኔን አላማ ማስፈጸም ነው። ታሪኩን ለባለ ታሪኮች ትተን ታሪክ የምንሰራበትን መልካም ጊዜና አጋጣሚ ባናባክን ለተውልድ ጥሩ የሚነበብ ታሪክ መስራት እንችላለን።

    በመጨረሻም ለጸሃፊው የምለው ቢኖር፡ ይህ ትግል አንተ እንደተመኘኸው አይከስምም፥፥ ወደ ሰዎች ጣታችንን ስንቀስር፤ ሌሎች ጣቶች ወደኛ ያመለክታሉ። ሰው ይሚያጭደው የዘራዉን ነው። ካረጀ ጥላቻ ነጻ ሁን ። አ ዲ ዮ ስ

  36. ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው” are u their until know ?
    u are stupid gay? we are not need ur assistance what we need is oromia and oromia

  37. Reading Amsalu G/Kidan (artist?) commentary brought the very sickness and disgust I always felt decades back regarding ignorant Amharas who think they are better than others and are educated but in reality are some of the most ignorant persons on the face of the earth. The language they use when they address the entire population of Oromo and other southern peoples is so disgusting that one would not think it comes from a mind of a humanoid, but from a mouth of a Neanderthal. Rather than educating themselves, they read archaic literatures from monasteries, memorize these insults written by ignorant priests. These uneducated but truly illiterate debteras then try to preach about country, politics, law and civilization to which they are actually alien to. Today, this ignorant is trying to lecture us what we Oromos should do and vomits his debtera poison to divide a wedge among the two peoples—Oromo and Amhara. Fortunately, the new generation of Oromo and Amhara are truly educated, civil, respectful of each other’s opinion and politics, and not ignorant preachers like this fool.

  38. ስለ ኦሮሞ ጉዳይ ካልገባችሁ ታሪክን ረጋ ብላችሁ አንብቡ:: ዝም ብላችሁ ከመጻፋችሁ በፊት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኦሮሞን እንደ ጭራቅ (የሌለ አውሬ) ከመሳላችሁ በፊት ቆም ብላችሁ አስቡ:: ኦሮሞ ማለት ኦነግ: ኦሮሞ ማለት ገላሳ ዲልቦ: ኦሮሞ ማለት ጁሃር መሃመድ: ኦሮሞ ማለት ኦፒዲኦ: ወዘተ … አድርጋቸሁ መውሰድ ትልቅ ስህተት ይመስለኛል::

    አንጋፋው (ትልቁ) የኦሮሞ ልጅ በሆነው ቦረና ኑና ጠይቁ ቦረና = ሰው የሚል አባባል ታገኛላችሁ:: ኦሮሚያ ወይም ቦረና ውስጥ ለመኖር ሰው መሆን ብቻ በቂ መሆኑን ትረዳላችሁ:: ይህ የኦሮሞ (ቦረና) ምልከታ ነው::

    ስለዚህ የኦሮሞን ጉዳይ ወሳኝ ከኦነግ: ከገላሳ ዲልቦ: ከጁሃር መሃመድ: ከኦፒዲኦ ጋር በማያያዝ አታሳንሱት:: ኦሮሞ በሃገሪቱ ውስጥ በቁመቴ ልክ መብቴና ጥቅሜ አልተጠበቀልኝም ብሎ ቢነሳ ይህ ሁሉ ውርጅብኝ ለምን ይወርድበታል:: ትግሉ ራሱን ከጭቆና ለማውጣት ስለሆነ ከተቻለ ማገዝ ካልሆነ ዝም ማለት ይገባል ባይ ነኝ:: በሃረሪቱ ያልተበደለ ስለሌለ ሁሉም በሚያዋጣው መንገድ መታገል እንጅ የኦሮሞን ትግል የግድ በዚህ ወይም በዚያ መንገድ ካልሆነ ብሎ ጥላሸት መቀባት የአዛዙን ስርዓት ማራዘም እንጅ ለማንም አይጠቅምም::

    በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ትግል ሌላውን ለመበደል ከሆነ የትም አይደርስም:: ትግሉ ህዝቡን ከዘረኛ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ከሆነ ደግሞ ሌሎችም በራሳቸው መንገድ በመታገል ነጻ ይውጡ:: ከዚያ በመቀጠል ሁላችንም እኩል መብታችን በተከበረባት ሃገር በአንድነት መኖር እንችላለን:: ስለዚህ ሁሉም በያለበት የራሱን የቤት ስራ ይስራ:: ኦሮሞው በራሱ ለብቻው ቢታገል እንደ ወንጀል ባይቆጠር መልካም ነው እላለሁኝ::

    የኦሮሞ ጉዳይ በተነሳ ቁጥር ኦነግንና ጁሃር መሃመድን ማጥላላት የኦሮሞን ጉዳይ ከማሳነስ አልፎ የኦሮሞን ጉዳይ ወሳኞች ኦነግና ጁሃር መሃመድ የሆኑ ያስመስላል:: ህዝቡ ሎጂካል አይደለም የሚል ያስመስላለና ህዝብ ደግሞ የሚበጀውን ያውቃል:: ቦረና = ሰው የሚለውን ብሂል ኦነግና ጁሃር አይደለም ኦሮሞን ያስተማሩት:: በመጨረሻም የኦሮሞን ትግል ለመደገፍ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ባይ ነኝ::

    ገመዳ ቦና – ከቦረና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*