መድረክ በኦሮምያ ጉዳይ ባለ አምስት ጥያቄ መግለጫ አወጣ
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ ባለአምስት ጥያቄ መግለጫ አውጥቷል፡፡ ከመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ጉዳይ መምሪያ የወጣው ይህ መግለጫ “ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በማሠርና በማንገላታት የኦሮሞን ሕዝብ ሰላማዊና ሕጋዊ ትግል መግታት አይቻልም” የሚል ነው፡፡ መድረክ ታሥረዋል ወይም በቁም እሥር ይገኛሉ ብሎ የአሥር የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪዎችን የስም ዝርዝር ካወጣበት መግለጫው ውስጥ ጥያቄዎቹና ጥሪው እንደሚከተለው ይነበባል