የመጨረሻዉ መጀመሪያ አሜሪካ ለምን የአርባ ምንጭ የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማስነሻ ጣቢያዋን መተዉ አስፈለጋት? (ከሳዲቅ አህመድ)

ወደ አለም አቀፉ የዲፕሎማሲ መንደር ቀረብ ቀረብ ማለት ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል።ከሐያላኑ አገራት ጋር የቀጥታ ሳይሆን የእጅ አዙር የዲፕሎማሲ ጉዞን ሳይጀምሩ አልቀሩም የሚሉም አሉ። በጠመዝማዛዉ መንገድ የሚጓዙት የዲፕሎማሲ ጉዞ ከሚፈልጉበት ቦታ እስኪያደርሳቸዉ ድረስ እምብዛም አትኩሮት አልሳቡም። እርሳቸዉ ግን እየተጓዙ ነዉ። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈርቂ።

ዜናዉ፦
አሜሪካ አርባ ምንጭ ዉስጥ ያላትን የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማብረሪያ ጣብያ መጠቀም ማቆሟ ታወቀበሱማሊያ ያሉትን አል-ሸባቦች ለማጥቃት አሜሪካ እንደ ኢሮጵያዉያን አቆጣጠር ከ2011 ጀምሮ ትጠቀምበት የነበረዉን የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማስነሻ ጣብያ መጠቀም ማቆሟን አሶሽየትድ ፕሬስ አዲስ አበባ ያለዉን የአሜሪካ ኤምባሲ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ዴቪድ ኬኔዲ የተባሉት የኤምባሲዉ ቃል-አቀባይ ለአሶሽየትድ ፕሬስ በኢሜይል በላኩት መልእክት ሁለቱ አገራት ባደረጉት ስምምነት አሜሪካ በአርባ ምንጭ የምታደርገዉ ቆይታ አስፈላጊ አይደለም።የኤምባሲዉ ቃል አቀባይ ይህንን ቢሉም የኢትዮጵያና የአሜሪካን ግንኙነት የሚከታተሉ ባለሙያዎች ክስተቱ አሜሪካ የፖሊሲ ለዉጥ ማረግ መጀመሯን አመላካች ዱካ ሊሆን ይችላል ሲሉ ይጠቁማሉ።

ለጋሽ አገራትና ፍላጎታቸዉየቀድሞዉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ሽብር ፈጠራን የመዋጋት ዘመቻ ማወጃቸዉ የሚዘነጋ አይደለም።ኢትዮጵያ የዚሁ ሽብር ፈጠራን የመከላከል ሚና ተሰጥቷትበምላሹ ከለጋሽ አገራት ድጎማን ስትቀበል መቆየቷ ይታወቃል።መረጃዎች እንደሚያመላክቱት አሜሪካ ለኢትዮጵያን በደንብ አርጋ ትለግሳለች። በ2008እንደ አዉሮፕያዉያኑ አቆጣጠር አሜሪካ ለኢትዮጵያ 969ሚሊዮን ዶላር ለግሳለች። በ2009 916 ሚሊዮን ዶላር፣በ2010 የለገሰችዉ ወደ 513 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱ ይታወቃል።

አሜሪካ ኢትዮጵያን የምትለግሰው አገሪቷ ዉስጥ የሚከሰተዉን የድርቅና የርሃብ አደጋ ለመከላከል፣ድህነትን ለመቋቋም፣ ለመልካም አስተዳደር፣ ማህበራዊ ሁናቴዎች ላይ ያሉ መመሪያዎችን ለማሻሻልና ለወታደራዊ ስልጠና መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ በመኖሩ አሜሪካ እና ሌሎች ለጋሽ አገራት የሚለግሱት ገንዘብ የአገሪቱን ዜጎች ህልዉና አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ያስጠነቅቃሉ።

አኩሪ ስራን ሰሪ ወይስ ሽብርን ፈጣሪ?
የአሜሪካዉ ፕሬዝዳት በራክ ኦባማ በሐምሌ 20/2007 ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት “ኢትዮጵያ ሽብር ፈጠራን በመከላከል ጽኑ የአሜሪካ አጋር ናት፣ ኢትዮጵያዉያን ጠንካራ ተዋጊዎች ናቸዉ” ማለታቸዉ ይታወሳል።

ኦባማ ይህንን ቢሉም፤ የኢትዮጵያ መንግስትን የሚቀናቀኑ ቡድኖች በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ መንግስት ‘ሽብር ፈጠራ በሱማሌ ዉስጥ እንዲስፋፋ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ያደርጋል፣የሶማሊያን የጦር አበጋዞች እያስታጠቀ ሽብር ፈጠራን መነገጃ አድርጓል፣የኢትዮጵያ ወታደሮችን ሶማሊያ እየላከ ያስፈጃል ሲሉ መንግስትን ተጠያቂ ያደርጋሉ።ጄከብ ጁማ የተባሉ ኬንያዊ ቱጃር በመጋቢት 25/2007 በትዊተር ገጻቸዉ ላይ በለቀቁት መረጃ “የኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪዉን አል-ሸባብ ያስታጥቃል።

አዲስ አበባ ለአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋት ተጠያቂ ናት።የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የአፍሪካዉ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስትን እንዲመረምሩ ግፊት ማድረግ አለባቸዉ!” ብለዉ ነበር። የቱጃሩ መረጃ አነጋጋሪ ሆኖ መሰንበቱ ይታወሳል።ለኢትዮጵያ መንግስት ቅርበት ያላቸዉ የመገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን ለማስተባበል ስሯሯጡ መታየታቸዉ የሚዘነጋ አይደለም።

የእጅ አዙር ዲፕሎማሲ?

በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ የኢትዮጵያ መንግስት ተቀናቃኝ አጎራባች አገራት ስለመጡበት ለምእራቡ አገራት የሚኖረዉ ስልታዊ አጋርነት እየቀነሰ ነዉ በማለት የሚገልጹም አሉ።የአሜሪካ ስልታዊ አጋር የሆኑ የባህረሰላጤዉ ሱኒ ሙስሊም አገራት የአሰብ ወደብን መገልገያ ለማድረግ መወሰናቸዉ አነጋጋሪ ሆኗል።

በአሜሪካ የዉጭና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች 38 አመታትን ያገለገሉት አምባሳደር ሐርማን ኮህን በአፍሪካ ቀንድ እየተከሰተ ስላለዉ ፈጣን ለዉጥ በታህሳስ 18/2008 በግል ገጻቸዉ ላይ ጽፈዉ ነበር።…”እናንተ አቢሲኒያዉያን ሆይ!” ብለዉ የተጣሩት አምባሳደር ኮህን “እናንተ በእርስ-በርስ ግጭት ስትጣሉ…ስትጯጯሁና…ሳትነጋገሩ… የባህረ ሰላጤዉ መንግስታት ምሳቹን እየበሉባቹ ነዉ” ብለዉ አስጠንቅቀዋል። ኮህን አክለዉም የተባበሩት አረብ ኤምሬት አይሮፕላኖች ከአሰብ ያለማቋረጥ መንቀሳቀሳቸዉንና ሳዑዲ አረቢያ በአሰብ ላይ የ50 አመታት ኪራይ መዉሰዷን አመላካች ሪፖርቶች መኖራቸዉን ገልጸዋል።

የባህረ ሰላጤዉ የሱኒ ሙስሊም አገራት በየመን በኩል ያለዉን የኢራንንና የሺዓ መስፋፋት ለመከላከል ኤርትራ ላይ አትኩሮት ማድረጋቸዉ የሚታወቅ ነዉ። እነዚህ በነዳጅ ዘይት ገንዘብን ያካበቱ አገራት ከአሜሪካ ጋር ስልታዊ አጋሮች ናቸዉ። ከአሜሪካ ጋር በኢኮኖሚዉና በወታደራዊ ግንኙነት የዉዴታ ግዴታ ቁርኝት አላቸዉ። ወደ አሰብ መዘንበላቸዉና አሰብን መከራየታቸዉ ያለአሜሪካ ይሁንታ በራሳቸዉ ፍላጎት ብቻ የተደረገ ነዉ ለማለት አያስደፍርም።

ሽብር ፈጠራን ለመከላከል በሚል መርህ በሳዑድ አረቢያ የሚመራ የ34 አገራት ጥምር ጦር በታህሳስ 5/2008ተመስርቷል። ይህ ጥምር ጦር የኪራዩን የአሰብ ወደብ አይጠቀምም ማለቱ አስቸጋሪ ነዉ። የጥምር ጦሩ አላማ ISIS እና ሌሎችን በኢስላም ስም የተነሱ አሸባሪዎችን ማመናመን መሆኑ እየተነገረ ነዉ።የአገራቱ ጣምራ ጦር የተዋቀረዉ ለፕሮፓጋንዳ ካልሆነና አላማዉ ተግባር ላይ ከዋለ፤ ISIS ብቻ ሳይሆን በሶማሊያ ያለዉም አል-ሸባብ የጣምራ ጦሩ ተጠቂ የሚሆንበት እድል የሰፋ ነዉ።ስለዚህ አሜሪካ ለምን አርባ ምንጭ ላይ የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማስነሻ ይኖራታል? ስልታዊ አጋሬ የምትላቸዉን አገራትን በጅ አዙር ከመጠቀም ምን ይከለክላታል? ለምን የጠገበዉን አሳማ (ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ) ትቀልባለች? ለአሜሪካ በጅ አዙር የተራበችዉን ኤርትራ ማብላት አይሻላትም ?

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወቂ ለምን በአንድ አመት ሁለት ግዜ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጓዙ?
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወቂ መጀመሪያ በሚያዚያ 21/2008 ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመጓዝ ከአገሪቱ ንጉስ ሰልማንቢን አብዱል አዚዝ አል-ሱዑድ ጋር መገናኘታቸዉ በአረቡ አለም በሰፊዉ የተዘገበ ቢሆንም ኢትዮጵያዉያን እምብዛም አትኩሮት የቸሩት አይመስልም ነበር። ኢሳያስ አፈወርቂ ዳግም በታህሳስ 10/2008 ወደ ሪያድ ሳዑዲ አረቢያ የሁለት ቀን የስራ ግብኝት ለማድረግ ማቅናታቸዉ በአገራቱ መካከል የጠበቀ ስልታዊ ግንኙነት መመስረቱን አመላካች ነበር።የኢሳያስን የዑኡዲ ሁለተኛ ጉዞ ተከትሎ ኤርትራ ጣምራ የ34 ጦርን አገራትን ሐይል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደምትደግፍ ከአገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዉጡ መረጃዎች አመላክተዋል።

ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ለጸረ ሽብር ተግባር ከለጋሾች እርዳታ የሚቀበልበት አል-ሽባብ የጣምራ ጦሩ አባልና ደጋፊ በሆኑ አገራት ተከቧል። ሶማሊያ፣ጅቡቲ እና ኤርትራ ጣምራ ጦሩን ደጋፊ ናቸዉ።ስለዚህ አሜሪካ ለምን የሰዉ አልባ አዉሮፕላን ማስነሻዋን አርባ ምንጭ ማቆየት ያሻታል?

ማስጠንቀቅና ልመና

በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ያሉ አርሶ አደሮችን እያፈናቀለ መሬትን ለሳዑዲ አረቢያና ለሌሎች አገራት ሲያከራይ የነበረዉ የኢትዮጵያ መንግስት አስመራም ተመሳሳይ ስራ በመጀመሯ ደስተኛ አለመሆኑን እየገለጸ ነዉ። በባለፍዉ የህዳር ወር መገባደጃ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ማስጠንቀቃቸዉ ታዉቋል። ለአገር ዉስጥ ጋዜጣ ቃለ መጠይቅ የሰጡት ሐይለማርያም ደሰላኝ በአሰብ ወደብ ላይ የሚያደጉትን እንቅስቃሴ ተከትሎ ኢትዮጵያ ለሚኖራት ምላሽ ሐላፊነቱን ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ይሸከማሉ ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ማስጠንቀቂያ ሳይሻር በከፍተኛ የኢትዮጵያ የመንግስት ባለስልጣናት የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በታህሳስ23/2008 በመግባት አቡ ዳቢ ፈንድ ፎር ዴቨሎፕመንት የሚባል የተራድኦ ድርጅትዘንድ በማምራት በሁለትዮሽ የእድገት፣ የመዋእለ ንዋይ እና የእርዳታ ጉዳዮች መነጋገራቸዉ ተዘግቧል።

እየቀረበ ያለዉ ለዉጥ

ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ በጅ አዙር አሸባሪን የመዋጋት የገበያ እሽቅድም ከጁ እየተፈተለከበት ይመስላል። ኤርትራ እና የ34 አገራት ጣምራ ጦር እየተፎካከሩት ነዉ። ስርዓቱ በከፍተኛ አጣብቂኝ ዉስጥ ገብቷል። ከዚህ አጣብቂኝ ለመዉጣትም እንደ አማራጭ የወሰደዉ የጅምላ ግድያንና እስር ነዉ። ተሰሚነት ያላቸዉሰዎች፣አክቲቪስቶች፣ጋዜጠ
ኞች፣የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ተማሪዎች፣ መምህራንና ሌሎችም የስ ርዓቱ ሰለባ እየሆኑ ነዉ። የማሰቃያ እና የማጎሪያ እስር ቤቶች መሙላታቸዉ እየተነገረ ነዉ። በጥቅሉ በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ መንግስት አይደለም አሸባሪነትን ሊከላከል እራሱ አሸባሪ በመሆን ለዜጎች ህልዉና ስጋት መሆኑን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁናቴ መቃኘቱ በቂ ነዉ።

አዲሱ የኢትዮጵያ አመት ከገባበት ግዜ ጀመሮ በተለያዩ ቦታዎች ቦምብ መፈንዳት ጀምሯል። በታላቁ አንዋር መስጊድ ዉዳሴ (መንዙማ) ሲያሰሙ በነበሩ ምእምናን ላይ በታህሳስ 1/2008 የቦምብ ጥቃት ደርሷል። በጥቃቱም እስከ 18 የሚደርስ ሰዉ ተጎድቷል።ተመሳሳይ የቦምብ ጥቃት በታህሳስ 22/2008 በዲላ ዩንቨርስቲ ተከስቶ 3 ሰዎች ሲሞቱ 6 መቁሰላቸዉ ታዉቋል። ዜጎች በነቂስ ድርጊቱ የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ነዉ የሚል መግባባት ላይ የደረሱ ይመስላል። ይህንኑ ለማረጋገጥ እስኪመስል ድረስ ዊኪ ሊክስ የተባለዉ የመረጃ አነፍናፊ ድረ ገጽ በበመስከረም5/2004 የኢትዮጵያ መንግስት እራሱ ቦምብ አፈንድቶ በኤርትራና በኦነግ እንደሚያላክክ አዲስ አበባ ከሚገኘዉ የአሜሪካ ኤምባሲ አፈትልኮ የወጣ መረጃን ዋቢ በማድረግ ለአለም ህዝብ አሳዉቋል። ታዲያ ህወሃት ወራሹ መንግስት እንደምን በጸረ ሽብር ዘመቻ ሁነኛ ስልታዊ አገር ሊሆን ይችላል?

ከብሔራዊ ጭቆና ወደ ብሔራዊ ድል

ህወሃት መራሹ መንግስት በእምነት ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገባ ክስ ይቀርብበታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ጣልቃ ገብቷል የሚል ለአመታት የዘለቀ ብሶት አለ። ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች መጤ አንጃ አምጥቶ ጫነብን ብለዉ በመቃወም አለም አቀፍ ሰላማዊ ንቅናቄን ጀምረዉበታል።ህወሃት የአገሪቷን ሐብት ተቀራመተዉ፣ጥቂቶች ሐብታም ሲሆኑ ሚሊዮኖች በድህነት ማቀቁ የሚለዉ እሮሮ በሰፊዉ ይሰማል። አገሪቷ ዉስጥ የተንሰራፋዉ የርሃብ አደጋ በተፈጥሮ ክስተት የመጣ ቢሆንም የመልካም አሰተዳደር እጦት ርሃቡን የከፋ እንዲሆን አድርጎታል የሚለዉ ህዝባዊ ብሶት በሐዘና በሲቃ የሚሰማ ነዉ። የኢትዮጵያን ድንበር ቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት የኢትዮጵያ መንግስት መስማማቱ የአገርን ሉዓላዊነት አስደፈረ የሚል ብሔራዉ ቁጭትን ፈጥሯል።በአገሪቷ ላይ የተንሰራፋዉ የመሬት ቅርምት ዜጎች በጫንቃቸዉ ላይ ሊሸከሙት ከሚችሉት በላይ ሆኖ እየተንገፈገፉበት ነዉ።

የኦሮሞ ተማሪዎች “መሬቴን አላስነጥቅም!” የሚለዉ ንቅናቄ አገራዊ ሆኖ ስርዓቱን ለመናጥ የበቃ ነዉ።ህወሃት ይህንን ሰላማዊ ንቅናቄ ለመቀልበስ በሰላማዊ ዜጎች ላይ አጋዚ በሚባለዉ ቅልብ ጦሩ የሚወስደዉ ዘግናኝ እርምጃ ህዝቡ ወደ “ህዝባዊ እንቢተኝነት” እንዲያመራ እየዳረገዉ ነዉ።

ወልቃይት ጸገዴዉ ተገድጄ ትግራይ ዉስጥ ተካለልኩ ወደ አማራ ክልል ልመለስ በማለት የማንነት ንቅናቄን ጀምሯል። የጎንደሩ ገበሬ በደሙ የዋጀዉ መሬት ለሱዳን ሊሰጥ በመሆኑ እምቢኝ አሻፈረኝ ብሎ እየተነሳ ነዉ። አኝዋኩ መሬቴ ለባእዳን ተሽጦ በግፍ ተገደልኩ፣በግፍ ተፈናቀልኩ እያለ ነዉ። አርበኞች ግንቦት 7 በጦርነት ህወሃት መራሹን መንግስት እጥላለሁ ብሎ እየተዋደቀ ነዉ።
ብሶት የማይሰማበት የኢትዮጵያ ክልል የለም።ዜጎች ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ለ25 አመታት ባንሰራፋዉ አምባገነናዊ ስርዓት ተንገፍግፈዋል።

የማይቀር ህዝባዊ እምቢተኝነት ከፊት ለፊት ተጋርጧል። አሜሪካንም ሆነች ሌሎች ሐያላን አገራት ለህዝባዊ ጩኸት ‘ጆሮ ዳባ ልበስ’ ያለዉን ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ጣል-ጣል ቢያረጉ አይገርምም። የሚገርመዉ ‘ከማይታወቅ መልአክ… የሚታወቅ…’ ብለዉ በህወሃት ላይ ተስፋ ቢያረጉ ነዉ።

አሜሪካንም ሆኑ ሌሎች በኢኮኖሚ የበለጸጉ አገራት ቅድሚያ ለብሔራዊ ጥቅማቸዉ ነዉ የሚሰጡት። አገራቱ ብሔራዊ ጥቅማቸዉ ህወሃት ጋር አለመኖሩን ቢረዱትም ያቺን የመጨረሻዋን ሰዓት የሚጠብቁ ይመስላል። ታዲያ!…ዉድና ጠቃሚ የጦር መሳሪያዎቻቸዉን ወደ ሌላ ቦታ መዉሰዱ መጨረሻዉ እየጀመረ አይመስልምን? “የመጨረሻዉ መጀመሪያ!” ለማንኛዉም ልብ ያለዉ ልብ ይበል።

Rafi Smart's photo.

24 Comments on “የመጨረሻዉ መጀመሪያ አሜሪካ ለምን የአርባ ምንጭ የሰዉ አልባ አይሮፕላን ማስነሻ ጣቢያዋን መተዉ አስፈለጋት? (ከሳዲቅ አህመድ)”

  1. That is just a wishful thinking. There is no government which is serving the American interest than Woyane. The most likely scenario for US to move its UMV out of Ethiopia is, the security improvement in Somalia as they had been deployed to counter Alshebab. Now a days, mushrooming buildings and vibrant shopping centers all over Somalia becoming the braking news of many medians. For a realty check, we don’t see them condemning TPLF after the recent brutal crackdown on revolting Ethiopian students.

  2. So many persons are writing about the recent clashes between Oromo students and security forces alas most of the comments are one sided and inclined to be politically correct. The reality on the ground tell us a competition, which is unhealthy, between the Addis Ababa plan developers (the Federal government) and Oromo nationalists. It seems to me that the whole confusion and altercation took root from the very political arrangement called ethnic federalism. Therefore, the ethnic federalism recognizes the country as a mere collection of various language groups than logical composition of citizens in terms of geographical distribution, cultural connection, economic viability and resource allocation. If you see Addis Ababa, it is an island under the mercy of Oromia to pursue its development. Secondly, the region themselves are unbalanced in terms of land mass, population size, material resources, skilled labor, etc. which benefits only Oromia, Amhara, Debub Hizboch and Tigray regions while not less than 70 language groups segregated into disadvantageous minority status.
    The writer correctly cited good urban development system in Eastern Asia. For example, Japan has a land mass of one third of Ethiopia and it has three major ethnic groups – the Ainu in Hokkaido, the Yamato in Honshu main land and the Okinawans in Okinawa (far south of Japan). The Japanese system of governance guaranteed self rule but not on ethnic basis. Japan is divided in to almost equal 48 prefecture which has all conceivable rights of self governance. Such system effectively shuts down ethnic confrontation and allowed them to fairly distribute resources and population across all 48 prefectures. The capital city, Tokyo is recognized as one of the prefectures with equal rights and privileges. Self governance based on geographic distribution and fair allocation of resource helped them to have 47 secondary cities (seats of the prefecture government) with almost identical growth.
    You will be surprised to know that, world famous big corporations, such as Toyota, Honda, National Panasonic, Mitsubishi, Nisan, Subaru, Sumitomo, Takata corporation, Bridgestone, Fuji, Hitachi, etc are established out of Tokyo. You will equally be amazed to see how development is equally distributed throughout the breadth and width of Japan thanks to creating identical size and economically sound prefectures.
    Having said that, the Central government has also a role defined by law to bridge this prefectures in major development undertakings. For instance, the construction and maintenance of cross country roads, express highways, cross country rail systems, electric grid, and other common infrastructure developments are handled by the Central government. Local governments also has joint ventures such as bridges connecting them, waste disposal, environmental protection, river development and navigation, etc.
    They cooperated out of common good than ethnic or regional rivalry. All these good staff was possible thanks to the Japanese political arrangement. Therefore, Ethiopia’s politics which is poisoned by the TPLF regime and other ethnic oppositions is the main culprit of all these instability rocking the country. Unless, we change that course of destructive political understanding we will be unlikely to fix all the ills festered for the past 25 or so years.

  3. ZeKirstos,Is that fair way of balancing the unbalanced resources? If you take for instance, Britain or USA, the resources are not equitabl among all states, but the one with fertile soil produces agricultural products, the arif areas can be used for industrialization, and it can be balanced with the pre-existing situation, and as you may know it they do not involve into the individual land or property. If somebody involves into individuals property or land, what do we call such type of governance? It is about a single point of comment, and it is not the whole of your analysis.

  4. everybody has a right to express his or her idea through media but it doesn’t mean that they are correct! as to me the current Ethiopian situation has good side and bad side in the current political system, the advantage is it implies to the world the past election was fake . and the government currently knows that they can not force people to accept whatever they want. but the bad side is the killing of innocent people, distraction of infrastructure and recism expended people are leaving their home town because they are not oromo. The main things is the current American situation it doesn’t have anything to do with the current Ethiopian situation!!!

  5. “በጥቅሉ በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ መንግስት አይደለም አሸባሪነትን ሊከላከል እራሱ አሸባሪ በመሆን ለዜጎች ህልዉና ስጋት መሆኑን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁናቴ መቃኘቱ በቂ ነዉ።”

    ደጋግሜ እለዋለሁ ወያኔ ትልቁ የኢትዬጵያ አሸባሪ ድርጅት ነው!!!

  6. የአሜሪካ መንግሥት ወያኔን የደገፈበት ትልቁ ውል አቅራቢው ያሥነበበን ሢሆን ከዚህም ባሻገር በዚህ ገልቱ የወያኔ ወታደር ሥለምን አላማ መቆሙ የማያውቅ ደሞዝህ በዶላር ነው ብለው እያታለሉት ደሙን በየኮሢው እየዘራው ነው በአሁኑ ሠአት ወያኔ በህብረተሠባችን ላይ እየሠነዘረ ያለውን የፈንጂ ጥቃቶች አልሸባብ ወይም ኦነግ ፈፀማቸው ማለቱ አይቀርም ግን ሁላችንም ወያኔን ክከሣሽም ምሥክርም ሆኖ በአደባባይ ተገናኝተነዋል እናም ገና ብዙ እናያለን ራሣችሁን ከአሸባሪው ወያኔ ጥቃት ጠብቁ።

  7. የተከበራችሁ የኢትዬጵያ ህዝቦች አኝዋክን ከጎኑ ከልቆምንለት አበቃ እሡም ወደ ጁባ መካለሉ አይቀርም ለምን የጁባ ሥደተኞች መንደር ማሠባሠብ በሚል ዘዴ ወደ ውሥጥ ዘልቀው መሬትና እርስሻ መጀመራቸውን ሥንቶቻችን እናውቃለን ይህ ሥፍራ በሳትኮን ኮንሥትራክሽን የነዳጅ ማውጣት ሥራ ለማሥጅመር መንገድ የተሠራ ሢሆን የነዳጅ ግኝቱ እንደታወቀ ከደቡብ ጅባ በተላኩ ሽፍቶች ከ10 በላይ ዜጎች እንደተገደሉ በ1996 መዘገቡን አሥታውሡ ይህ ጉዳይ ችላ መባል የለበትም ገላጋይ መሥለው ድንበርን እየሸጡ ያሉ የዘራፊው የወያኔ ቡድኖችን እባካችሁ እናሥወግድ።

    ሞት ለወያኔ

  8. Personally I believe that the current American withdrawal from arbaminch, may not be related directly with the current crisis in Ethiopia because such decision can not be made overnight or in a month or two, time of incidents. However the existing political crackdown of the regime could be the potential source of this decision. Tplf could no longer be a partner to counter terrorism for the western countries while it’s not disciplined itself over its own people human rights.moreover tplf can’t get on well with its African nation forces over combating allshabbab in Somalia instead using allshabbab as an opportunity to swing over its criminal acts.probably this kind of decision by America will put tplf in difficult position from now on there will not be any excuse for tplf, for its crime against humanity rather being responsible for it and faces the consequences. We will see the difference soon.

  9. ” . . . በባለፍዉ የህዳር ወር መገባደጃ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ማስጠንቀቃቸዉ ታዉቋል። ለአገር ዉስጥ ጋዜጣ ቃለ መጠይቅ የሰጡት ሐይለማርያም ደሰላኝ በአሰብ ወደብ ላይ የሚያደጉትን እንቅስቃሴ ተከትሎ ኢትዮጵያ ለሚኖራት ምላሽ ሐላፊነቱን ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ይሸከማሉ ብለዋል። ”

    Quote above should be supported by all Ethiopians. Opposition parties should also protest and give warnings to the crazy and barbaric Saudis and Arabs.

    That action of Saudis is a hostile act against Ethiopia, and is related to the Nile. The Saudis intend to keep Ethiopia weak and vulnerable.

    We have to discuss more about that, more articles should be written.

    But the author is wrong when he says the Saudis fight ISIS, no, the Saudis are ISIS.
    ISIS was created and is supported by,

    1. USA

    2. Saudi Arabia

    3. Qatar

    4. Turkey

    5. Israel

    6. UK

    7. In general the West

    ISIS serves three agendas,

    1. to create a caliphate (sunni)

    2. to serve as a tool of USA and the West to distabilize Russia and China.

    3. to distabilize whole regions in Africa and the middle east and create chaos.
    This is part of what the neoconservatives call “creative destruction”.

    The 34 countries alliance created by the Saudis should worry Ethiopia and other Nile upstream countries. It could now be used against Ethiopia and other Nile upstream countries should a Nile conflict break out between Egypt and Ethiopia plus the other upstream countries.
    But the 34 countries are not all part of the alliance, the dumb Saudis put on the list name of countries without asking them if they want to be part of it.

  10. This the second in command
    of the terrorist group Dimtsachin
    yisema after the notorious Jihhadist
    Jawar Mohammed .

  11. @ ZeKirstos,

    you are a half baked analyst.

    You sound to be against tribalism but use TPLF imposed TRIBALIST LANGUAGE, like
    Oromo nationalists. NO, they are not what you called them they are oromo tribalists.
    There is only one group of nationalists in Ethiopia, Ethiopian nationalists.

    You also don’t have to go as far as Japan to find an example of a non-tribalist political organization, we had that in Ethiopia for centuries till TPLF came to power thanks to USA support.

    http://www.emapsworld.com/images/ethiopia-provinces-map.gif

  12. Guregna anten billo
    Potential tentagne hidena
    Ke Jawar Mohammed gar seaw
    Indiet indemitared temaker .
    Awaki lememsel atmoker aboye Sebehat dehena bilohal

  13. Yehie demo alehu alehu
    Yelal mejemeria ante akrari
    Muslim nehe Ethiopian
    lemaferares inkelf yeleleh
    hidina yante mehayimn
    kededelet

  14. Sadik Deputy comander of the terrorist
    Dimtsachin Yisema inante ke Democracy gar
    Yet tetewawekalachehu ? Chewataw min
    Indehone rawkewaleh ANGETE MEKURET kefelegeh
    Aggotocheh Saudi WO he GA mehed techlalehe .

  15. If you ask me, we should thank the author for this article, and should encourage him to write more in the future.
    This view from a geopolitical perspective is extremely important, above all in a country like Ethiopia,

    1. with a very complex neighborhood and

    2. with such a low level of knowledge and understanding in geopolitical matters.

    We should not forget that one key reason why that “cursed generation” brought us so many problems was lack of geopolitical knowledge.

    Regarding the non-Ethiopian Jawar Mohammed, he could be a CIA agent, also a Saudi or Arab agent.

    ” Teddy says:January 4, 2016 at 11:44 am

    Guregna anten billo
    Potential tentagne hidena
    Ke Jawar Mohammed gar seaw
    Indiet indemitared temaker .
    Awaki lememsel atmoker aboye Sebehat dehena bilohal “

  16. Read guys,
    GOP presidential candidate Trump says Obama & Hillary Clinton created ISIS:

    ” … He then blamed US President Barack Obama and his former secretary of state, Hillary Clinton, for the Islamic State’s rise.

    “They have a bunch of dishonest people,” he continued. “They’ve created ISIS. Hillary Clinton created ISIS with Obama — created with Obama. But I love predicting because you know, ultimately, you need somebody with vision.”

    The next morning on “Fox & Friends,” Trump repeated his statement that Clinton “created ISIS.”

    “She has a terrible record as secretary of state. I mean, she’s literally created ISIS,” Trump said. “If you look at her, between her and Obama, they’re the ones — we have this big ISIS problem they created with their bad policies and their bad thinking.” “

  17. አሜሪካ አርባምንጭ ያለውን ወታደራዊ ማዘዥዋን ተዘጋ ተባለ ግን አልተዘጋም ወደሌላ ቦታ ተዛወር እንጂ በአማራ አካባቢና በዲፊት አካባቢ መሆንኑ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ ውስጥ አዋቂ ምንጭ ነገሮናል

    ነገር ግን አሜሪካ የዒትዮጵያ ወዳጅ አልነበረችም ልትሆንም አትችልም ወያኔንና ሻቢን በቢሊዩን ዶላር በማገዝ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ያደረገች ቆሚ የኢትዮጵያ ጠላት ናት!ሕዝብ ይህን ማወቅ አለባት
    ይባስ ብሎ አሜረካ በማን ፈቃድ ነው በአንድት ልዋላዊ ሃገር ውስጥ ወታደሮችን የምታሰፍርው ፈቃጁ ማን ነው ወያኔ እንደት ብሎ ኢትዮጵያ የሚወከል ሲሆን ብቻ ነው አሁን የአሜሪካን ወታደር ሰንት ናቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ድፍረት ነው የድፍረት ድፍረት ንቀት ነው
    አሜሪካን የኢትዮጵያ ጠላት ናት!
    ሳ.አ

  18. These so-called Ethiopians in USA dont alert Ethiopians of the grave danger USA poses to Ethiopia, and also to all blacks.

    USA policy towards Ethiopia since 1945 was that of containment, that means:

    1. to prevent industrialization

    2. to prevent investments (that it allowed in Japan, South Korea, Taiwan etc)

    3. to distabilize

    4. to impose hostile economic policies through IMF and world bank

    5. to block the possibility to borrow money from the international market etc

    The containment policy of USA against Ethiopia is racially motivated and its intention is to keep all black countries unindustrialized, poor and weak.
    So far the USA was successful.

    USA for example excluded Ethiopia as the only allied country from reconstruction programs after the end of world war 2, but included foes like Germany and Italy.

    Now for decades the USA prevents the return of skilled and educated Ethiopians from the West back to their country of origin. USA is letting them get old in the West to prevent them from using their skills and knowledge (also capital) for the benefit of the Ethiopian society, like the Indian and Chinese returnees did for their countries.

    Nazi USA / CIA were behind:

    1. the so-called Ethiopian Students Movement

    2. overthrow of Haile Selassie

    3. overthrow of Derg

    4. separation of Eritrea

    5. landlocking of Ethiopia

    6. introduction of tribalism and killils in Ethiopia as initial steps to dismantle Ethiopia

    7. the failure of the Qinijit revolution in relation to the 2005 elections.

  19. Sadik please correct the Calendars you mentioned in your analysis. Is it in G.C or E.C if it is in GC the rent thing if the Asab is a status quo phenomenon not in 2008 and if it is in our calander “Miazia” is not the past it is coming ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወቂ ለምን በአንድ አመት ሁለት ግዜ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጓዙ?
    ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወቂ መጀመሪያ በሚያዚያ 21/2008 ወደ ሳዑዲ አረቢያ
    በመጓዝ ከ….

  20. You guys would be wrong if you had thought USA had a containment policy only towards Ethiopia. No, that ferenji country had such a policy also towards the whole of Africa.

    USA is an enemy.

    ” … To understand why the BRICS bloc’s proposed bank is a different and new banking dynamic, you need to identify and understand the nature of Empire in Africa. The corporate-owned mouthpiece of Empire, the media, will not have told you that colonialism/neo-colonialism in Africa is finally ending.

    Colonialism did not end in the 1960s; it just mutated into an invisible/hidden form of control that involved keeping Africa as a raw materials market of an unindustrialized and undeveloped continent for the copper, oil and diamond lords that have operated a corporate empire from the City of London. They own the big banks like HSBC, Bank of England and Federal Reserve of America. Through these banks and their initiatives of the IMF and World Bank they have managed by trickery and corruption to enslave by debt nearly every nation on the planet.

    Key to the power, riches and success of this empire are minerals. And the situation in the most mineral-rich region on Earth is testament to the ruthless and satanic nature of the corporations that form Empire. The bloodbath that has soaked the countries in the heart of Africa – Rwanda, Burundi, Uganda and critically the DR Congo – has been orchestrated by these corporations to buy into power their chosen clients and to buy time in a sea of instability and chaos, in which to rape and pillage for maximum profit the mineral resources of the Congolese nation. This corporate presence is a heart of darkness, the likes of which Humanity has never seen before. This Empire has been at work across the continent. It has murdered millions by war and poverty. It has orchestrated war in Sudan, Mali, Somalia, Central African Republic, Mozambique, Zimbabwe, Eritrea, Liberia, Sierra Leone, Rwanda and the mother of all wars and the genocide of all genocides – the DR Congo. ”

    Full article:
    http://www.pambazuka.net/en/category.php/features/95065/print

  21. This George F. Kennan:
    https://www.ias.edu/sites/default/files/sites/default/files/images/Kennan%20for%20web%20release.jpg
    personifies the “heart of darkness” that was stated in the above article.

    “We have about 50% of the world’s wealth, but only 6.3% of its population. … In this situation, we cannot fail to be the object of envy and resentment. Our real task in the coming period is to devise a pattern of relationships which will permit us to maintain this position of disparity. … To do so, we will have to dispense with all sentimentality and day-dreaming; and our attention will have to be concentrated everywhere on our immediate national objectives. … We should cease to talk about vague and … unreal objectives such as human rights, the raising of the living standards, and democratization. The day is not far off when we are going to have to deal in straight power concepts. The less we are then hampered by idealistic slogans, the better.”

    —George F. Kennan, Policy Planning Study 23 (PPS23), Foreign Relations of the United States (FRUS), 1948

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*