የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትሪያርክ አቡነ ዲዮስቆሮስ አረፉ – VOA


የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አራተኛው ፓትሪያርክ አቡነ ዲዮስቆሮስ ከረዥም ጊዜ ህመም በኋላ ዛሬ ማረፋቸው ታውቋል።

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ በፓትሪያርኩ ማረፍ ጽኑ ሀዘን እንደሚሰማው ገልጿል። የቀብር ስነ-ስርአት በመጪው ቅዳሜ መንደፈራ በሚገኘው የአቡነ አብራንዮስ ገዳም ላይ እንደሚፈጸም ታውቋል። የዜና ዘገባ አለን – ያዳምጡ → listen