የፖለቲካ መሪ ነን ያላችሁ የታላችሁ?

ከሎሚ ተራተራ

እረ ያገሬ ስው ፤ ለማን ልናገረው፤
እረ የመሪ ያልኽ ምድሩን ባዳ አረስው።
ታማሚዎች በዝተው ሃኪም ቤት አልረዳ፤
ሆስፒታሉ ሞልቶ መኝታው በረንዳ።

የተቃዋሚ ፖሎቲካ መሪ ማለት ምን ማላት እንደሆነ ሳይገባቸው ነው መሪ የሆኑት ብዬ ለመናገር ባልደፍርም ቅሉ አንዳንድ መሪ ነኝ ተብዬዎች ግን እራሳቸውን በመሪነት ቦታ አስቀመጡ እንጂ መምራት ግን እንዴት እንደሆነ ምን አይነትም ዋጋ እንደሚያስከፍል በቅጡ ገብቷቻዋል ብዬ አልደፍርም።

የዚህ ድረጅት” መሪ” ብለው እራሳቸውን የጠሩ ግን እንደገና እራሳችውን በመመርመር የት እንዳሉ፤ምን እንደጎደላቸውም ጭምር በመጠየቅ ወይ መምራት ወይ ቦታ መልቀቅ እንዳለባቸው ግን እርግጠኝ ነኝ።

ፋይዳ የሌለው ምሳሌ ነው። ተብሎ ሊፈረጅ እንደሚችል ብገምትም፤ አንድ ምሳሌ ልናገርና ወደዋናው ሃሳቤ ልግባ ።

ባል እና ሚስት በመግባባት ትዳራቸውን መምራት አቅቷቸው፤ አንቺ ነሽ ጥፋተኝ! አንተነህ ጥፋተኝ !

እየተባባሉ በጭቅጭቅ ዘመናት ቢቆጥሩም፤ ባል ለሚስቱ ያለውን ታማኝነት ሚስትም ለባሏ ያላትን ፍቅረና ታማኝነት በተግባር መግለጽ ካልቻሉ ግን የሚያደርጉት አንድ ነገር ነው። ያው መፋታት። ከተለያዩ በኋላ እሦም እሱን በመኮነን የሦን እውነተኝነት ባካባቢዋ ለሚገኙት ማውራትና የሦን ታማኝነት ለመግለጽ በመሞከር ጥሩ ሚስት እንደነበርች ለማሳመን መሞከር ነው። ባልም በአንፃሩ ይህንኑ ነው የሚይደርገው።

የባለትዳሮችን ምሳሌ በ ፖሎቲካ መሪዎችና በሕዝብ መካከል እንዳለ አደርጋችሁ እንድትመለከቱልኝ እፈልጋለሁ።

እውነቱና ለኔ እንደሚገባኝ መሆን ያለበት ግን ከመለያየታቸው በፊት ሁለቱም በመተማመን ለትዳራቸው ታማኝ በመሆን፤ ባልም ሆነ ሚስት ያጠፋው ስው በግልጽነት ይቅርታን በመጠየቅ ዳግመኝ ጥፋት ባለመስራት ተግባብተውና ተማምነው መኖር ነው።

በትዳራቸውም ጉዳይ ላይ በማተኮር ፍቅራቸውን አደሰው ክቡሩን ትዳር እስከፍፃሜ ለማድረስ የየበኩላቸውን ጥረት ማድረግ ነው። እንጂ አንዱ አንደኛውን በመኮነን እንዘልቃለን ከተባለ ግን መጨረሻው ያው ውድቀት ነው እላለሁ። እናንተም የምትሉትን በሉ።

ፍቺ ሲመጣ ድግሞ የሚያደርስው ጉዳትም ቀላለ አይደለም፤ ልጆች ይበተናሉ ኑሮ ይናጋል ብዙም ያልተገመት የስነልቦና ቀውስም ያስከትላል።

በመሪዎች ችግር ምክነያት በሃገር ላይ ሊደርስ የሚችለውም ቀውስ ተመሣሣይነት አለው ባይ ነኝ።

እንግዲህ ጥያቄው መሪዎችም አካሄዳቸውን በማስትካከል ከህዝብ ጋር ተግባብቶ በጊዜውና በስዓቱ መደርግ ያለበትን በማደርግ የብቃትን ተግባር ማሳየት አይመስላችሁም አንድን የጥሩ ፖሎቲካ መሪ ተግባር የሚገልጸው ? ።

እንዲሁም ግራ ቀኙን ተመልክቶ አፋጣኝ የስከነ አመራር በመስጠትና ሕዝብም ሲሳሳት መክሮና ዘክሮ አስተካክሎ አንድ አቆም ይዞ “እትዮጵያዬ” ብሎ እንዲነሣ ማድረግ ተገቢ ነው። መሪዎችም እራሳቸው ሲያጠፋ ድክመትን ተቀብሎና ይቅርታም ጠይቆ አመራሩ ውጤታም እንዲሆን ማድረግ ካልቻሉ ምን ሊገጥማቸው ይችላል ብላችሁ እንደሕዝብ ትገምታላቸሁ ? እኔ ያው እንደ ባለትዳሩ ፍቺ ነው እላለሁ።

መቼም ሚስት ቢፈታ ሌላ ሚስት ይገባል እንደማትሉኝ አምናላሁ ። እንዲህ የሚልም ካለ በድፍረት የሚያገባህ የለም። የሚያገባሽ የለም ። መሆን አለበት የሕዝብ መልስ ባይ ነኝ። ምክነያቱም ይሄ ያገር ጉዳይ ነውና።

ዛሬ በቱኒዝም ሆነ በግብጹ በሌሎችም የአፍሪካ አህጉራት የምናየው ትዕይንት መሪዎች በሃገር ደረጃ መሪ ከሆኑ በኋላ በሚያደርሱት ከፍተኝ ድክመትና ቀውስ ምክነያት ከህዝብ የሚደርስባቸውን ቁጣ ነው።

በኛም አገር ይህ ነው የማይባል ግፍ ደርሦልና በቃኝ! ብለን እንድንነሣ የሚመራን አጥተናል መሪዎች የት አላችሁ?

የ ኢትዮጵያ ሕዝብ በተደጋጋሜ ለመሪዎቹ ታማኝነቱንና ቆራጥነቱን አሳይቶል። የመሪዎች ችግረ ግን በውስጥም በውጪም በግልጽ እየታየ ነው። እንደሕዝብ ምን ብናደርግ ነው መሪዎች ልቦና እንዲገዙ ወይም ልቦና ለገዙ መንገድ እንዲለቁ የምናደርገው ትላላቸሁ? ።

የፖለቲካ መሪነን ያላችሁ ጥያቄው ለ እናንተ ነውና ለሕዝብ መልስ ስጡ ጊዜው ሳይመሽ አገረን አደኑ እላለሁ።

ሕዝብስ አገሬን እወዳልሁ የምትል ምን ትላለህ? ታሪክ እየተነተንን ብሦታችንን እያወራን በዚህ ታላቅ የለውጥ ዘመን ዝም ብለን እንቀመጥ ?

ወየስ መሪዎቸ ባይቀስቅሱንም እራሳችንን ቀስቅስን፤ መሪ ፍጥረን ታሪክ ለመስራት ታሪክ ከስሩት የጎረቤት አገሮቻችን ጎን እንሰለፍ ? ሁላችንም መልስ እንስጥ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በራሱ ቆራጥ ተነሣሽነት መሪዎቿ ቀስቅስው ለድል ባያበቁትም እራሱን ለድል ያበቃል!

በቸር ይግጠመን

ሎሚ ተራተራ