ይነጥፋል የተባለው የስዑዲ ሃብት

የሳውዲ አረብያ የተፈጥሮ ሃብት፣ ሃገሪቱን ባለፀጋ እና ተሰሚነት ያላት አገር እንድትሆን አድርጓል ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የሳውዲ የሃብት ምንጭ የሆነው የነዳጅ ዘይት ዋጋ መውረዱና የየመኑ ጦርነት እንዲሁም በአካባቢው ከኢራን ጋር የሚካሄደው ሽኩቻ እስካሁን በገንዘብ አቅም የያዘችውን ቦታ ሳያሳጣት አይቀርም