ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ ቅጥፈቶች፣ እርባናቢስ ውሸቶች እና የሀሰት የቁጥር ቁማር ጨዋታዎች፣
ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)
ጆን ሚልተን ገነትን ማጣት/Paradise Lost በሚለው መጽሀፋቸው “የቱም ዓይነት ቅጥፈት ቢሆን ዘለቄታዊነት የለውም የሰማይ ቁጣንም ይስባል።” በማለት ጽፈዋል። በእርግጥ ሚልተን ሊጨበጥ ሊዳሰስ ስለማይችለው ባዶ ምናብ ስለሚፈጥረው ስለሰይጣን እና ስለዕኩይ ምግባሩ ነበር የጻፉት።