“ስለ ረሃብ የተናገረ ሰው ያስራሉ፣ ይደበድባሉ፤ ሕዝቡንም ያስፈራራሉ” ሲሉ አንድ የምዕራብ አርሲ አርሶ አደር ለVOA ገልጸዋል
የተዘራው ሁሉ መጥፋቱን ለቪኦኤ የገለፁ አንድ የምዕራብ አርሲ አርሦ አደር የሰሞኑ እርጥበት ሊያበቅልልን ይችላል በሚል ተስፋ ያደረ መሬት ለማረስና ለመዝራት እየሞከሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ “ሰዉ ስለ ድርቅና ስለ መራቡ መናገር ይፈራል” ያሉት እኒሁ አርሦ አደር “ስለረሃቡ ይደብቃሉ፤ በፍፁም አይናገሩም፤ ስለ ረሃብ የተናገረ ሰው፤ ሰው እንደገደለ ተደርጎ ይታያል፤ ያስራሉ፣ ይደበድባሉ፤ ሕዝቡንም ያስፈራራሉ” ሲሉ ከስሰዋል፡፡ ዘገባውን ያዳምጡ ↓