ፖሊስ መምህር ግርማን በነፍስ ግድያ በመጠርጠሩ በዋስ አልተፈቱም

በተጠረጠሩበት የማታለልና ሐሰተኛ ሰነድ መጠቀም ወንጀሎች የ50 ሺሕ ብርና የ40 ሺሕ ብር ዋስትና የተፈቀደላቸው መምህር ግርማ ወንድሙን፣ ፖሊስ በነፍስ ግድያ እንደሚጠረጥራቸው በማመልከቱ አለመፈታታቸው ታወቀ፡፡
ፖሊስ መምህር ግርማ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ሳያገኙ ፈቃድ እንደተሰጣቸው በማስመሰል ሐሰተኛ ሰነድ እንደተጠቀሙ በመግለጽ፣ ሰነዱን እያስመረመረ መሆኑን ገልጾ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ኅዳር 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ ተጠርጣሪው በ40 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ፖሊስ እሳቸውን በነፍስ ግድያ እንደሚጠረጥራቸው በመግለጽ ለፍርድ ቤቱ ማመልከቻ በማቅረቡ፣ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ሰነዶችን እንዲያቀርብ ለኅዳር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ተጠርጣሪው ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ የሚኖሩ ግለሰብን ቤት በማሸጥና ገንዘቡንም ‹‹ይፀለይበት›› በማለት መውሰዳቸውን በሚመለከት ፖሊስ ካቀረበባቸው ክስ፣ በ50 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
ነገር ግን በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ቅር የተሰኘው ፖሊስ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያለ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ኅዳር 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የፖሊስን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ የሥር ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አፅድቆ በ50 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ አዟል፡፡ ነገር ግን ተጠርጣሪው በነፍስ ግድያ በመጠርጠራቸው ከእስር አልተፈቱም፡፡
አንድ ሲባል ሁለት …ሁለት ሲባል ሶስት…ይሁን መምህር እግዚአብሄር ከእርስዎ ጋር ይሁን………መታሰር የእውነተኛ ሰወች መገለጫ ከሆነ ቆየ……………………………………………………………………………………
መምህር ግርማ ወንድሙ አንድ እውነተኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባት ልብ ያለው ልብ ይበል አስተምረውናል ፁም ፀልይ ስገድ ተብለሀል ተብለሻል ያልፀለየ ሰነፍ ሰነፉ ይሞታል የፀለየ ይድናል ሁላችንም አይተናል መምህር ግርማ የህይወት ስንቅ አስታጥቀውናል እንወደወታለን…እናከብርወታለን …እግዚአብሄር ከእውነተኞች ጋር ነውና የታሰሩትን ያስፈታልን……………………………………………………………………………………………………………………………………………!
አንድ የአድስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ሲታሰሩ ገና ዛሬ ኢትዮጵያዊ መሆኔን አወቅሁ ነበር ያሉት ስለዚህ መታሰር የኢትዮጵያዊ መገለጫ ከሆነ ቆየ ………………………………………………………………………………………
ጎበዝ አላስተዋልንም እንጅ ሁላችንም ታስረናልና እንፀልይ………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
ይገርማል እራሱ በሰየመው ፍርድ ቤት እንኳን የማይዳኝ ምን አይነት ዱብ እዳ ወረደብን? ለነገሩ ቅዱስ ፓትርያሪኩም ሆነ ሲኖዶሱ እውነት እፊታቸው ስትጨፈለቅ ዝምታን መምረጣቸው ያስተዛዝባል፤ ያሳዝናልም። እኚህ ሰው (መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅሱሳንና ሰማዕታት ስም ፈውስ ማድረጋቸውና ያላመኑትን ወደ ቤተ ክርስቲያን በመመለሳቸው ሊመሰገኑ፣ ሊከበሩና ሊሸለሙ ሲገባቸው እየወረደባቸው ያለው በደልና እንግልት ለሠማዕትነት እያዘጋጃቸው ይሆን? ያሰኛል። ፈጣሪ ከኣርሰዎ ጋር ይሁን መምሕራችን።
Yih Yewoyanie Sira ena Tenkol new
Benuro Besira Behaimanot yeteregaga Hiwot endainore Degag sewochin Gegna Sewochin Sew yiketelachewal Bilo yasebachewn sewoch Eyasere ena eyegdele endihum bemashemakek anget eyasdefa ager yizerfal meret yichebechibal
Egiziabher Yesirawn Etif dirib yikfelew
በጣም ያሳዝናል ምን አይነት ዘመን ላይ ደረስን ከቤተክህነት ፍቃድ የላቸውም አላቸው እያለ የእስር ጊዛቸውን የምያራዝመው ጠቅላይ ቤተክህነቱ ነው ፓልስ ምን አገባው እዚህ። ላይ እነሱ እራሳቸው ከጎን በመሆን ቃሪያ እየቀቡ ነገሩን ያሰፋት ባለ ብሩም ብሆን ውሸታም ነው ለማየት ያብቃን እሔ ሁሉ ውሸት አንድ ቀን ይወጣል አባታችን ዋናው ጤና ነው አይዞት የርሶ እስር በዝህ ቆሻሻ ምድር ነው የነሱ ግን በዘላለማዊው ቤት በሰማይ ነው በውሸት የፈረደች አፋቸው ምን ይውጣታል በእውነተኛው ዳኛ ፍት” መታሰሩን ታሰር ነገ ትፈታለህ ወዳጅ ጠላትህን ትለይበታለህ” ተብላል አይዞት እመቤቴ ማርያም ከርሶ ጋር ናት።
ትህትና…ማስተዋል…G/Egzi…እግዚአብሄር ሁል ጊዜ እውነት ተናጋሪ ያድርጋችሁ…እውነት እግዚአብሄር የዘገየ ይመስለናል እንጂ ፈጣን ነው………………ትህትና “መታሰሩን ታሰር ነገ ትፈታለህ ወዳጅ ጠላትህን ትለይበታለህ”እውነት ወዳጂና ጠላት ይለያል ከእግዚአብሄር የሚቀር ምንም የለም………………………………………………………………………………………………………………
የደርግ ወታደር ናቸው ሥትሉን አልነበረ እንዴ
ወታደር ለመሆናቸው ምን መረጃ አላችው ? ለምንስ እስከዛሬ አልተናገራችውም ምድረ በውሸታም እውነቱ መውጣቱ እሳቸውም መፈታታቸው አይቀር ብቻ ደህና ይሁኑ ።
ልንገራችሁ መንግስት ስላሰራቸው ብቻ ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎች በግለሰብ መብትና ግዴታ ላይ ልትደራደሩ አትችሉም ሰውዬው ዘራፊ ናቸው ነብሰ ገዳይም ናቸው! ሲመስላችሁ እግዚአብሔር ቢያገለግሉት ኖሮ ዝም የሚል ይመስላችሁዋል፡፡ እግዚአብሔር ኢሕአዴግን የሚፈራ ይመስላችሁዋል! አትሳሳቱ ከዙፋኑ ያወረደው የለም