በሚነሶታ ሁለት ኢትዮጲያውያን ሞቱ ፣ አንዱ ደግሞ የከፋ ጉዳት ደርሶበታል – ህዳር 25, 2015
ሁለት ወጣቶች በሚንያፖሊስ ከተማ፣ ሚነሶታ መኪና ውስጥ በተኩስ ተገድለው መገኘታቸውንና ሶስተኛው ወጣት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገለት መሆኑ ታውቋል።
ባለፈው እሁድ እአአ ሕዳር 22 2015 ምሽት ላይ ሁለት ወጣቶች በሚንያፖሊስ ከተማ፣ ሚነሶታ መኪና ውስጥ በተኩስ ተገድለው መገኘታቸውንና ሶስተኛው ወጣት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገለት መሆኑን የሚንያፖሊስ ከተማ ፖሊስ ጆን አልደር (John Elder) ለCBS ቴለቪዥን ገልጿል።
“የከተማው ፖሊሶች በወቅቱ ቦታው ላይ የነበሩ ሰዎችን እያነጋገሩና ጉዳዮን እየመረመሩ ሲሆን፣ ተጠርጣሪዎቹ ወድያው በእግር እንደሸሹና እስካሁንም እንዳይልተያዙ” ጆን አልደር ገልጸዋል። የቪድዮ ቃለ ምልልሱን ይመልከቱ ↓