በራያና ቆቦ የሚኖሩ ገበሬዎች በቂ የእህል እርዳታ ካላገኘን ለከባድ የረሃብ አደጋ እንጋለጣለን ብለው ይፈራሉ – VOA


በራያና ቆቦ፥ ልዩ ስሙ “መንደፈራ” በተባለው አከባቢ የሚኖሩ ገበሬዎች፥ በድርቁ ምክንያት ከደረሰባቸው ረሃብ ለማምለጥ፥ ምግብ የሚገዙት ከብቶቻቸውን እየሸጡ እንደሆነ ይናገራሉ። በአከባቢው በአሁኑ ሰዓት እየጣለ ያለው ዝናብ፥ ዘሩን ይመልስልናል ያሉትን እህል እንዳያበላሽባቸውም ኩፉኛ ሰግተዋል። ከመንግስት በቂ የእህል እርዳታ ካላገኘን፥ ለከባድ የረሃብ አዳጋ እንጋለጣለን ብለው ይፈራሉ። በሰሜን ወሎ ዞን የኣደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበርያ ፅህፈት ቤት ተጠሪ አቶ መሐመድ ያሲን ደግሞ በዞኑ ለ54 ሺህ ህዝብ የእህል እርዳታ እንደተሰጠና፥ መንግስት በቂ የእህል ክምችት እንዳለው ይናገራሉ። ግርማይ ገብሩ ከቆቦ የላከውን ዘገባ ያዳምጡ… listen

4 Comments on “በራያና ቆቦ የሚኖሩ ገበሬዎች በቂ የእህል እርዳታ ካላገኘን ለከባድ የረሃብ አደጋ እንጋለጣለን ብለው ይፈራሉ – VOA”

  1. ሰው ከሆኑ በድርቅ ወቅት ሕዝብ በረሃብ የእሞት እነሱ በጭፈራ ደንዝዘዋል/ሰውንም አደንዝዘዋል ከቶ ምን ይሻለን ይሆን?
    አይ የሰው ልጅ ከንቱ ምን ለመሆን ታስቦ ይሆን በኢትዮጵያ ላይ
    ሃገርን ለማጥቃት ብአንዱን (300.000.000) ሶስት መቶ ሚሊዩን ብር ወጪ አውጥቶ ድግስ ደግሶ በየከተሞች፣በችግር በኩፉ ቀን ወገን፣እንሰሳት በርሃብ ፣በጥም እየሞቱ ፣ስደት አይግባኝ እየነጎዲ
    ደግሞ የብአድን ታጋይ ተባየዋ መጽሃፍት አስመረኩኝ ትላለች ጉድ ጉድ ዘመነ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ጡት ነካሾች ብዛታቸው
    ለወደፊትም እናጠፋታለን ነው የሚሉን/ቱ/ ሃገረን፣ወገን ለረሃብ አጋልጦ ስንት ወር ጨፈሩ እውነት እነዚህ አማራን ይወክላሉ?
    ወንድሙን ገድሎ ሃውልት የሚስራ/ት/ የኢትዮጵያ ጠላት ማን ነው?
    ብአንድን በዘመናት የሚፈነዳ ለትውልድ ትውልድ ያስተላለፈው የማይሽር ሃኪም የሌለው ነርሳ የተከሉ እሾኮች ናቸው!

    ሳተናው አሊ

  2. ውድ ወገኖች ሁሉ እንደሰው ለሚያስቡ ጤናይስጥልኝ ሰላም ናችሁ
    እኛ መቼም ቢሆን ያለንበትን ሁኔታ ከባድ ነው
    ጥያቄ አለኝ
    1- በ22/03/2008 ዓ.ም በአዲስ አበባና አካባቢዋ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች ራሳቸውን ስተው መውደቃቸውን በሆስፒታልና ከተጎጅ ቤተሰቦች እየተነገር ነው ስለዚህ እባከችሁ ወገኖች ሬድዩ ሆስፒታሎችንና ትምህርት ሚኒስትር ጠይቃችሁ ለወደፊቱ ለሚደረገው ጥንቃቄ እንድንወስድ ብትረዱን?
    2- በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው ድርቅና ርሃብ ምክንያት የሚመጣው የበሽታ አይንት ምን እንደሚሆን ወርርሽ፣ተስቦ፣ኮሌራ ወዘተ ሕዝብ ቢያውቀውና ብናውቀው መልካም አይመስላችሁም ?
    3- ሌላው ጥያቄዩ በአዲስ አበባ ውስጥ ለህክምና ለካርድ ብቻ 1000 (አንድ ሽህ ብር) የሚጠየቀው በምን ምክንያት ይሆን? እሱም ሎሪት የማነብርሃን ክሊኒክ ሲሆን እውነት ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያዊነትን ያውም ብዙ ድሃ ሕዝብ ባለት ሃገር ውስጥ ለካርድ 1000 ብር ለካርድ 1000 ብር ተው ዶ/ር በዛ እጅግ በዛ ከዚህ ሕዝብ ነው የተፈጠራችሁት ያስተማራችሁ ተው እባከችሁ እንደ ሰው አስቡ?
    ሳተናው አሊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*