‹‹ርሃቡን ያመጣው የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ነው!›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

‹‹ርሃቡን ያመጣው የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ነው!››

• ‹‹ለመፍትሄው መረባረብ አለብን››

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ የሰጡት አስተያየት

‹‹የርሃቡ የቅርብ ጊዜ ምክንያቱ የዝናብ እጥረት ነው፡፡ የዝናብ እጥረት ድርቅን እስከተለ፡፡ ርሃቡን ያመጣው ግን የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ነው፡፡ የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ለረዥም ጊዜ፣ ለሀገር በሚጠቅም መልኩ ታቅዶ እንዳይሰራ አድርጎታል፡፡ ኢህአዴግ የሚሰራው ለአጭር ጊዜ የፖለቲካ ጥቅም እንጅ ለህዝብ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ የሚሰራው አቅዶ ቢሆን፣ 10 አመት አደግን ተብሎ የ2 ወር ዝናብ መጥፋት ይህን ያህል ርሃብ ባላስከተለ ነበር፡፡ አሁን በየቀኑ የሚያወሩልን የውሸት ክምር ነው፡፡ የጭካኔያቸው ጭካኔ ደግሞ፣ ያኔ ርሃብን የስልጣን መወጣጫ እንዳላደረጉት አሁን ይህን ያህል ህዝብ ተርቦ ‹‹የአፋር ድርጅት በዓሉን አከበረ፣ ብአዴን የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው›› የሚል ዜና ነው በመንግስት ሚዲያ የምንሰማው፡፡ ይህን የሚያደርጉት ስለ ርሃቡ እንዳይሰማ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው እነዚህ ሰዎች ምን ያህል ጨካኞች እንደሆኑ፣ ከህዝብ ጋርም እንደተጣሉ ነው፡፡ ተግባራቸው ሁሉ የእብሪት እንጅ ህዝብን የሚጠቅም አይደለም፡፡

Negere Ethiopia's photo.

አገዛዙ ለርሃቡ ትኩረት አልሰጠም፡፡ በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያውያን ዋናው ትኩረታችን መሆን ያለበት መፍትሄው ላይ ነው፡፡ በችግሩ የተጎዳው ህዝቡ፣ እንዲሁም መፍትሄም የሚያመጣው ህዝቡ መሆኑን አውቀን መረባረብ ይገባናል፡፡ ለችግሩም ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ የአደባባይ ሰዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ለዓለም መንግስታት ቅርበት ያላቸው ኢትዮጵያውያንና ደርጅቶች በሙሉ ልንረባረብ ይገባል፡፡ ለመፍትሄው መረባረብ አለብን!››

11 Comments on “‹‹ርሃቡን ያመጣው የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ነው!›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት”

  1. የ10 አመቱን እድገት ጠላቶቻችን ቢክዱትም ማሳያው 8.2 ሚሊዮን ህዘብ ተርቦ እንኳን ጡረታ ለሚወጡት ባለሰልጣኖቻችን ቤት ለመስራት የመደብነው ባጀት ምስክር ነው

  2. እናንቴ ተቃዋሚዎች ስትባሉ በጣም ነው ውሸታቹ እየበዛ የመጣው አንተን ሚያክል ሰው ግብደ ውሸት ለፕሮፕጋንደህ ስትጠቀም ይደብራል። ምክንያቱም ድርቁ በተለያዩ ሀገራትም በመከስት ላይ ንውና መንግሥትም ቢሆን አርፎ አልልተቀመጠም አመቻችቶአል ምትናገሩትን ለይታቹ እወቁንጂ

  3. እውነት ነው ለወገን ደራሹ ወገን እንጂ ወያኔ አይደለም!!!

    እነሆ በርሀብ ምክንያት ያነገባችሁት ብረት አሁን ዳቦ ሊሆን ከቻለ አሣዩን እንናንት ሌቦች እህል ተትረፈረፈ ብላችሁ በፓርላማ እንዲሸጥ አረጋችሁ የአለም የአየር ንብረት ለውጥ እያለ ከሚያናፋ መንግሥት መጠባበቂያውን ሽጦ መጨረሥ ለሙሥና በር መክፈቻ ዘዴ ነው በባለፈው የሥንዴና ዘይት እደላ ምን እንደሠራችሁ ታውቁታላችሁ አሁንም ወገን ተርቦ ገና እህሉ ጅቡቲም አልደረሠም የተራበው ወገን በቅርቡ ከተማ ገብቶ ህዝቡ እንደሚረዳው አልጠራጠርም።

  4. እርዳታ በአየር እንጂ እንዴት እንደመኪና መለዋወሥጫ በመርከብ አሥቸኳይ 3ወር ይጠብቃሉ ይህ ወገን ላይ ማላገጥ ነው።

    እንደቀድሞው የብአዴንን ኬክ ላኩላቸው ማለታቸው አይቀሬ ነው

  5. ወያኔ ለጦርነት እንጅ
    ለረሀብ አይበገርም
    የሚያልቀዉ ህዝብ እንጅ
    ካድሬዉ ሳይባላ አይበላም የሀገሬ ሆዳሞች ወያኔ ስሙን ሰርዞ ‘ወይ አይኔ ወይ አይኔ’ የሚልበት መድረክ በቁርጥ ቀን ልጅ ተሰልፏል::

  6. Hey Mr. Liprosy !

    Where you been ? Agoteh 60 ye Ethiopia Berkeye
    lejochin indalasfeje Izieh
    Hulum yawkewal meslot
    Mawenabed ayechelem Asafari.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*