በስዊድን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት መርጃ ገንዘብ ተሰበሰበ
ወለላዬ ከስዊድን
ቅዳሜ ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. (ኦክቶበር 31 ቀን 2015 እ.ኤ.አ.) በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መርጃ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተገኝተዋል። በቦታው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ አበበ ቦጋለ የውጪ እንቢተኝነት ሊቀመንበር እና አቶ ቸኮል ጌታነህ የንቅናቄው ከፍተኛ አመራር ናቸው።