በርሃብ ለተጠቁት ኢትዮጵያውያን ለሁለት ቀን የሚቆይ የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ ሊደረግ ነው፡፡

በርሃብ ለተጠቁት ዘመቻ ሊደረግ ነው

ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia's photo.

በርሃብ ለተጠቁት ኢትዮጵያውያን ለሁለት ቀን የሚቆይ የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ ሊደረግ ነው፡፡ ዘመቻው አርብ ህዳር 3/2008፣ እና ቅዳሜ ህዳር 4/2008 እንደሚደረግም ታውቋል፡፡ ዘመቻውም በእንግሊዘኛ ‪#‎EthiopiaFamine‬ እንዲሁም በአማርኛ ‪#‎ክፉ_ቀን‬ በሚል መለያ (ሀሽ ታግ) ይደረጋል፡፡

በመጀመሪያው ቀን ስለ ርሃቡ መረጃዎች በመለዋወጥ፣ ለኢትዮጵያውያን፣ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰቡና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ርሃቡን በማሳወቅ እንዲሁም የሁለተኛው ቀን ዘመቻ መፍትሄዎችን በማፈላለግ በተለይም በርሃቡ የተጠቁትን በምን መልኩ መርዳት እንደሚቻል በመወያየት ላይ እንደሚያተኩር ተገልፆአል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ርሃቡ በተከሰተባቸው አካባቢዎችና የርሃቡ ተጠቂዎች የተሰደዱባቸው ከተሞችና አካባቢዎች የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ያጋጠማችሁን፣ ያላችሁን መረጃ በተለይ በፎቶና በቪዲዮ አስደግፋችሁ በነገረ ኢትዮጵያ የፌስ ቡክ ገፅ ብትልኩልን፣ እኛም ለህዝብ እንደምናደርስ እንገልፃለን፡፡ በተጨማሪም በርሃቡ ላይ የግል ትንታኔዎች፣ የመፍትሄ ሀሳቦች ያላችሁ በነገረ ኢትዮጵያ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

7 Comments on “በርሃብ ለተጠቁት ኢትዮጵያውያን ለሁለት ቀን የሚቆይ የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ ሊደረግ ነው፡፡”

  1. It is a good idea, if trustworthy collectors can be organized. Thia time, it is very much drought by nature mostly.

  2. ረሀብ ጊዜ አይሰጥም ፥ ቅዱሳን
    ሐዋርያት ፦ «እምነ ረሀብ ይኄይሰነ
    ኲናት፤ ከረሀብ ጦር ይሻለናል፤
    »ያሉት ለዚህ ነው፤ በረሀብ
    ተሰቃይቶ ከመሞት፥ በጦር
    መሣሪያ መሞት ይሻለናል፥
    ማለታቸው ነው። በረሀብ ወቅት
    ውሎ ማደር ከባድ ነው።
    (አይቻልም)። እያንዳንዷ ሰዓት
    ከዓመት ትረዝማለች፤ ምክንያቱም
    የዕለት እንጀራ ታላቅ በረከት
    እንደሆነ ሁሉ ፥ የዕለት እንጀራን
    ማጣት ደግሞ የመጨረሻው
    ሰቀቀን ነው።

  3. This is likely Elias kifle’s shabia forum. He posts a lot of trash on this site. i hope he is sane.

    Times must be hard in Africa’s sing a poor.

  4. Are you guys that stupid or why cant you see the dirty game ?

    This is an engineered crisis !

    Stop behaving like low IQ morons, this is a theater organized by USA, TPLF and others.

    The goal is propaganda for the more dangerous fraud called climate change that aims to keep Africa poor forever if the conference succeeds.

    How stupid you guys must be not to see this fraud and circus, or are you bought by CIA and ferenjis ?

  5. የረሃብ ዋና ምክንያት ምንድን ነው?
    ዝናብ፣ወንዝ፣ደመና፣ምንጭ ሳይኖራቸው /የሌላቸው ሃገሮች ርሃብ የሚባል አያውቁትም ፡፡
    እኛ ግን ዝንታለም በሰዎች ስግብግበነት በምቀኝነት ወንዞች፣ሰራተኛ ሕዝብ እያለን ለምን ተራብን?
    ርሃብ አለ እንዴ በኢትዮጵያ? ረሃብ መኖሩን የሚነግሩን በዕዳን ናቸው
    የርሃቡ መንስኤ ስግብግብነት፣ሌብነት የምሁራን ስስታምነት ወዘተ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*