የ«ሞት በኩላሊት ይብቃ» እና የስኳር ህሙማን ማህበራት ጥሪ
«ሞት በኩላሊት ይብቃ» የተባለው የኩላሊት ህሙማን ማህበር ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጀው የእግር ጉዞ ላይ የኩላሊት ህክምና የሚያስፈልገው ወጭ ከፍተኛ በመሆኑ መንግሥት የማከሚያ መሣሪዎች በነፃ እንዲገቡ እንዲፈቅድ ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ የስኳር ህሙማን ማህበር ትናንት ባከሄደው ተመሳሳይ የእግር ጉዞ የስኳር በሽታን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት መንግሥት እና ህብረተሰቡ ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፏል። ሁለቱንም ጉዞዎች የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል → listen