ዝም አይልም ሕዝቡ፤ በቃ ወዮላቸው!
ከ አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ-ወ-መንፈሳዊ
እንደ ክቡር ደራሲው ከበደ ሚካኤል፦
***”ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት፤
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት፤
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ፤
እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ።”***
ብለው እንደተረጎሙት፤
ይኑር ብዕራቸው ለዘላለም አይሙት።
ሕዝቡ ዝም አይልም ፦በቃ ወዮላቸው!!!
ያጋዚ-ወያኔን
ጠርጎ እስኪፈጃቸው።
ዝም አይልም ሕዝቡ
በቃ ወዮላቸው!!!
እናም፦
እኔም እንደአቅሚቲ ለዘመኑ ብዬው፤
በደም ለታጠቡት ትዕቢተኞች ይሄው።
ኢትዮጵያን ያረዱ የፈጁ ሕፃናትን፤
ሕዝቧን በአደባባይ ገድለው ያስገድሉትን፤
በጊዜ በሥልጣን በገንዘብ ቢ-ገዙ፤
የስጋ-ትል ሆነው ሺህ መግደል ቢያበዙ፤
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው ሥርፅ ነው መዘዙ፤
በሞት-ሲቃ ትግል በጣዕር እስኪያዙ።
አይጠፋም እሣቱ የተቀጣጠለው፤
ደሙ “ዋይ!!! ዋይ!!!” ይላል፦
ሲቃ ነው ያጀለው።
እቶን ነው እሣቱ ጠርጎ እስኪፈጃቸው፤
ሲዖል ነች ኢትዮጵያ ለመጨረሻቸው።
ከተሸሸጉበት ሳይጎለጉላቸው፤
በደም እንዳጠቧት እሷም ሳታጥባቸው፤
እንደሲዖል ማንጉግ :-
ሕዝቡ ሳይበላቸው፤
ዝም አይልም ቀልቡ
ያውቀዋል ውስጣቸው።
ዝም አይልም ሕዝቡ
በቃ ወዮላቸው!!!
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው ሥርፅ ነው መዘዙ፤
በሞት-ሲቃ ትግል በጣዕር እስኪያዙ።
ቱኒሲያ ቢነድ
ትግሉ የመን ቢነጉድ
ግብፅ ቢቀጣጠል
ከኤርትርያ ቢዘል
እግዚአብሔርም ሰምቶ ለሕዝቧ ይሰጣል፤
ኢትዮጵያን የነካት የሞት ሞት ይቀጣል።
የኢትዮጵያ አምላክ:-
እንዲያ ሲታገሳቸው፤
ዝም አይልም ሕዝቡ
በቃ ወዮላቸው!!!