ሠዓሊ ዳንኤል ጌታሁንና ቡሩሹ

«ሥዕል ለኔ ሰላም የሚሰጠኝ፤ ሃሳብ ሲበዛብኝ፤ የሚያስጨንቁና የሚያሳዝኑ ሁኔታዎች ሲገጥሙኝ፤ ነፃ የምሆንበት መሳርያዬ ነው፤» ይሉናል ዛሬ በእንግድነት የምናቀርባቸዉ ሠዓሊ ዳንኤል ጌታሁን። ሠዓሊ ዳንኤል ጌታሁን የሚስሉዋቸዉ ሥዕሎች አብዛኞቹ የኢትዮጵያዉያንን ባህል አኗኗር የሚያንፀባርቁ በመሆናቸዉ በሚኖሩበት በቶሮንቶ ካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን «ሀገርን አስተዋቂ አንባሳደር» ነዉ የሚልዋቸዉ። ሠዓሊ ዳንኤል በብሩሽና በቀለም ብቻ ሳይሆን የሚስሉት በዲጂታልም እንደሆነ ይናገራሉ። የዲጂታል ሥዕል ስንል ምንድን ነዉ? በዚህ ዝግጅታችን ሠዓሊ ዳንኤል ጌታሁንና ሥዕሎቻቸዉን እንዲሁም ሥዕል በምሥል የሚታሰብ እይታዊ ቋንቋ ነዉ የሚሉንን የሥዕል መምህር በእንግድነት ይዘናል። ያድምጡ → listen

