የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል የእጅ ስልክ ባልታወቁ ሰዎች እጅ ገባ::

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የእጅ ስልክ ባልታወቁ ሰዎች እጅ የገባ ሲሆን ኢንጂነር ይልቃል በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር ላሉ አባሎቻቸው እና ደጋፊዎቻቸው የሚቀጥለውን ማሳሰቢያ አስተላልፈዋል::

ማሳሰቢያ :- የእጅ ስልክ (ሞባይሌ) ባልታወቁ ሰዎች እጅ ስለገባ ከዛሬ ጥቅምት 24/2008 ዓ.ም ጠዋት 2 ሰዓት ጀምሮ በፌስቡክ፣ በኢሜልና በሌሎችም አድራሻዎቼ የሚተላለፉ መልዕክቶች የእኔ አለመሆናቸውን ወዳጆቼ እንድትገነዘቡልኝ እፈልጋለሁ፡፡

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት : የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር