ኢትዮጵያን የመታዉ ድርቅ፤ ምክንያቱና መፍትሔዉ


ድርቅ እና ረሐብ ለኢትዮጵያ አዲስ እንዳልሆነ-ሁሉ የመወያያ ርዕሥ ሥናደርገዉም ይሕ የመጀመሪያችን አይደለም።የመጨረሻ እንዲሆን እንመኛል።ግን ከምኞት ማለፉ አጠራጣሪ ነዉ።ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግሥት እና ዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች በጋራም፤ በተናጥልም እንዳስታወቁት ከ8.2 በላይ ኢትዮጵያዊ ለረሐብ ፤በተለሳለሰዉ አገላለጥ ለምግብ እጠረት ተጋልጧል። Listen