መምህር ግርማ ወንድሙ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።መምህር ግርማ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄም ወድቅ ተደርጓል። …” ሆን ተብሎ ከጀርባ የተጠነሰሰብኝ ሴራ አለ ” መምህር ግርማ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ መርማሪ ቡድን ዛሬ ግለሰቡን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት አቅርቧቸዋል።ፖሊስ ግለሰቡ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል ቀሪ የምርመራ ስራ ስላሉብኝ ተጨማሪ 14 ቀን ይፈቀድልኝ ብሏል።ተጠርጣሪው በራሳቸውና በጠበቃቸው በኩል ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ በመቃወም የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል::የፖሊስ የምርመራ ቡድን በበኩሉ እሳቸው ቢለቀቁ ሌሎች ተፈላጊዎችን እና የተለያዩ ሰነዶችን ስለሚያሸሹብን ጥያቄያቸው ውድቅ ይሁን ብሏል።ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገን ክርክር መርምሮ ፖሊስ አብዛኛውን የምርመራ ስራ ያካሄደ በመሆኑ ለቀሪ የምርመራ ስራዎቹ ይረዳል በማለት ከጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ 7 ቀን ብቻ ፈቅዷል።ውጤቱን ለመጠባበቅም ለጥቅምት 25 2008 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
የወንጀሉ ዝርዝር
ፖሊስ መምህር ግርማ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆነው ወንጀል የተፈፀመው መስከረም 2006 ዓ.ም ነው ብሏል።በየካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሰን ግሮሰሪ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩት አቶ በላይነህ ከበደ በመምህር ግርማ የማታለል ወንጀል የተፈጸመባቸው ግለሰብ ናቸው:እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እኚህ ግለሰብ ከትዳር አጋራቸው ጋር 400 ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ መኖሪያ ቤታቸው ይኖሩ ነበር።
እንደ ምርመራ መዝገቡ መምህር ግርማ የግል ተበዳይን እምነት በመጠቀም የምትኖርበትን መኖሪያ ቤት እስከ ጥር 30 2006 ሽጠህ ካልወጣህ አስከሬንህ ይወጣል ይሏቸዋል።
የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚለው ልጅ ያልወለዱት ባልና ሚስት ከመሞት መሰንበት በማለት ይህንን ቤት በጣም በዝቅተኛ ዋጋ በ800 ሺህ ብር ይሸጡታል።ቤቱ በዚህ ዋጋ እንዲሸጥ መምህር ግርማ በራሳቸው ሰዎች አማካኝነት ብዙ ያልተገባ ስራ ሰርተዋል ነው የሚለው የምርመራ መዝገቡ።ከዚያም መምህር ግርማ በዚህ ብቻ ሳይመለሱ የግል ተበዳዩን ቦሌ አካባቢ በራዕይ ያየሁት ቦታ አለ እዚያ ነው ገዝተህ የምትኖረው ይሏቸውና ሌላ የማታለያ ዘዴ ቀየሱ ይላል ምርመራው።
ቤቱ የተሸጠበትን 800 ሺህ ብር አምጣና እንዲበረክትልህ ልፀልይበት ብለው ወሰዱ፤ በዚያው ውለው አደሩ፤ የግል ተበዳዩም በእርሳቸው ላይ ያላቸው እምነት ባለመጥፋቱ በትዕግስት ስልክ ቢደውሉላቸውም ስልካቸው ዝግ ሆነባቸው ይባስ ብሎ ከሀገር ወጡ ተባለ።ሁኔታው ማታለል መሆኑን ስለተረዱ 2007 መጋቢት ወር ገደማ ወደ እኛ መጥተው አመለከቱ የሚለው ፖሊስ እርሳቸው ከሄዱበት እስኪመለሱ የግል ተበዳዩን እና የምስክሮችን ቃል ተቀብሎ ቆይቶ ተጠርጣሪው መምህር ግርማ ወንድሙን ትናንትበቁጥጥር ስር አውሏቸው ነው ዛሬ ፍርድ ቤት ያቀረባቸው።
ተጠርጣሪው እኔ የተባለውን ሰው ቀይ ይሁን ጥቁር አይቼው አላውቅም፤ ሆን ተብሎ ከጀርባ የተጠነሰሰብኝ ሴራ አለ በማለት ለችሎቱ አስረድተዋል።ጠበቃቸውም የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የሚከለክል አይደለም፤ ፖሊስም የሚጠበቁ ምርመራዎቹን አጠናቋል፤ ደንበኛዬ የዋስትና መብታቸው ይከበርልኝ በማለት ጠይውቋል።ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጓል።

Tamerat Geleta ena Taye ( yetekemet. Gebrail ) Mechreshachew yet yehon. Girmas genzbun le set Stefo ena tiru Vila Gezto neber . Tamerat Geletana Taye Kerama new yetktlut . Gen ande ken Ewnten tawkalchew.
Who like money? Tekekel neh Taye Kermam Agantet awtetew ena setanawi teamer sertew neber. Tamerat Geltama aynsa sentun endaste? Hoo yechenekew erguz yagebal
ሲጀመር መነኩሴ መኪና ምን ያደርግለታል:አየ ምንኩስና!
ይህ ክስ መሠረታዊ ተቀባይነት የሌለው እውነትነት የጎደለው ተራ ሀሰት ነው። መምህር ግርማ ወንድሙ የሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት ግልጽ በሆነ በዓይን የሚታይ በመረጃ ላይ የተደገፈ በአደባባይ የሚታወቅ ነው። የቅስና ክህነቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዓባላት ሊቃነ ጳጳሳት በተገቢው ሁኔታ የተቀበሉ አረጋዊ አባት ናችው። የሚሰጡት አገልግሎት በከፍተኛ የሙያ ፕሮፌሰሮችን ሳይቀር ያስደነቀ፣ የውጭ ዘጎች ጭምር እያስገረመ የፈውስ ተግባር ነው። ብዙ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ፣ በሱሰኝነት፣ በርኩስ የአጋንንታዊ መንፈስ የተጠመዱ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ዜጎች ከበሽታቸው ተፈውሰው ሰላማዊ ሕይዎታቸውን እየመሩ ነው። ከማንኛው ዓይነት ፓለቲካዊ ግኙኝነት የጸዱ ናቸው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ ሐዋርያዊ እምነት የቀና መሆኑ እያስመሰከሩ ነው። ብዙ ኢአማንያን ከጠፉበት የተዋሕዶ እምነት መልሰው የእገቡ ነው። ካህኑ በማጥመቅ ብቻ ሳይሆን ከመንጋው የተለይተው የጠፉትን በጎች ፍልጎ በማጝነት እና ወደ በረቱ በመለስ ሐዋርያዊ አስተዋጻኦ እያበረከቱ ነው። አገልግሎታቸው ሰዎችን በመንፈሳዊ ቃል መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ማነጽ ነው። የሰው ልጅ መንፈሳዊ ሕይወቱ ሰላማዊ ማንነት ጤናማ ስብናው ከተገነባ ጥሩ የሀገር ዜጋ ይሆናል። በእምነት ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ብቃት የታነጸ ዜጋን በማፍራት እረገድ በጠቅላላው ለሀገራችን የሚሰጡት አስተዋጾ በመሪዎች ዘንድ ሊበረታታና ከፍተኛ ግምት ውስጥ መግባት አለበት። ይህ የሀሰት ክስና ውንጀላ መንፈሳዊ ክህነት አገልግሎት ለማናናቅና ከሁልም በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለማዋረድ ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ሴራ ነው። ከክሱ መሠረተ የሌለው በመሆኑ ከዚህ የምንረዳው ካህኑን ሆን ብሎ ስብናቸውን ለማዋረድ ኢላማ ያደርገና የተቀነባበረ መሆኑን ብቻ ነው። ከሁሉም በላይ የቤተ ክርስቲያንዋን ክብር ለመንቀፍና ለማዋረድ የተደረገ ተልካሻ ጥንስስ ነው። መላው የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤት ክርስቲያን ተከታዮች በሙሉ ይህን አሳፋሪ ድርጊት በአንድነት መቃወም አለብን። ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባው ከማጠናቀቁ በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህን የሆኑት መምህር ግርማ ውንድሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲፈቱ የሚቻለውን ሁሉ ማደረግ ይጠበቅበታል።
ማሰርና ካስፈለግ ስንት በቢሊዮኖች የሚቆጠር የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ የሚዘርፍና የሚያዘርፉ፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚያዋርዱና ቤተ ክርስቲያንn ፈጽሞ እንድትጠፋና እንድትከፋፈል ሽጦ ለመከፋፈል የሚፈልጉ ካዲዎችና ንቅልፍ የሌላቸው ስንት ወንጀለኞች በዙሪያችን እያሉ አንድ ካህን በተሰጠው የክህነት መንፈሳዊ አገልግሎት ኃላፊነት አጠመቀ ብሎ ማሰር ተገቢ አይደለም።
የሕዝብ መገናኛ ብዙሀንም ካህኑ መምህር ግርማ ወንድሙ በሀገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው በፊት ወንጀለኛ አስመስሎ ወሬ ማሰራጨትና የተከበረ ስማቸውን መንፈሳዊ አገልግሎታችውን ለማበላሸት ዜጋዊ መብታቸውን ሰባዊ ክብራቸውን ያለፍርድ መቀማትና ፈጹም ሕገውጥና ሙያዊ ስነምግባር የጎደለው ተግባር ነው።
አየ ዲያስፓራ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት ትሯሯጫለሽ:አባ ግርማ እንደወ ታምራት ገለታን ተቀላቅለዋል
tsre D,,
Egziyabher yegesitsh !!!
Be orthodox ena Pentecostal church Ye temesegu leboch mechreshachew werdet new, elekun said Jesus is the King of King Almighty God ,demo Ye ethiopi hezeb Ewnte yawkal menem Sedetena mekera bebzben
Dedeb.yesytamn.melktga.deros.kednre.aynt.nebse.geday.men.yitbkal.yetwahdo.leji.antnm.tamrat.wedmhnm.yfwsal.
ምን አለ በማስተዋል ብ ናስብ!!!!እሳቸው እኮ የገንዘብ ችግር የለባቸውም !!! በየ ሀገሩ ለአገልግሎት ሲሄዱ ከሚገኘው ገንዘብ እንኻን ቤሳ ቤስቲ ለራሳቸው የማያስቀሩ ስውየ አሁን በዚህ በማይረባ ገንዘብ የአዛውንቱን ስም ማጥፋት ምን ይባላል . ይሄ የተቀነባበረ ሴራ ነው!!!!!!!
እዉነት ከሆነ ጊዜ የሚያሳየን ነገር ነዉ በእኛ ሃገር ተመሳሳይ የፈጠራ ክሶቸ የተለመዱ ናቸዉ ጊዬ ሰጥቶ ማየት ያስፈልጋል ሰዉየዉ ከዚህ በፊትም ታስረዉ እንደነበር ኣዉቃለሁ::
Alem zetgn nech aser moleto aywekem
JESSES IS lord
አባ ግርማ የኛ ሀይማኖት ተከታይ ነበሩ:ኢየሱስ ጌታ ነው!ሀሌ ሉያ!አሜን በሉ!
ለመልአከ መንክራት ቀሲስ ግርማ ወንድሙ እንኳን ደስ አለዎት፤
አባቶቻችን ነብያት፣ሐዋርያትና ቅዱሳን ሰማዕታት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሰጣቸው ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በአደባባይ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ የተያዙትን በሽተኞች በመፈወስ፣ ልቦናቸው የናወዘውን በማጽናናት፣ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን በማነጽ፣ የአምላክን ፍቅር፣ሰላማዊ ቃል ዜና ማዋዕሉን በማብሰር፤ ገቢረ ታአምራቱን በማወጅ ለሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት የሚከፈላቸው ትልቁ ደመወዝ የሀሰት ክስ፣ እስራትና እንግልት ነበር።
ሳውል ሲፈጽመው ከንበረው ወንጀል፣ ወድቆ ከነበረበት የሐጥያት ቀንበረ አምላካችንና መድኅኒታችን አየሱስ ክርስቶስ እራሱ ሳውል! ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ ብሎ ጠርቶ ጳውሎስ የሚል ስያሜ ሰጠቶ መለኮታዊ ሐልዎቱን አብርቶ፤ ተዘዋውሮ እንዲያስተምር ኃይል ሰጥቶ፣ ሕሙማን እንዲፈውስ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ተቀናጅቶ፤ ጳውሎስ ብዙዎችን አስትማረ ከደዌያቸውም ፈውሳቸው፣ ብርሃናዊ ቃሉን ሰበከ አስተማረ ኃይለ አጋንንትን በመዶሻ ሰባበረ ነገር ግን የዚህ ሁሉ መንፈሳዊ ተግባር ውጤቱና ደመዎዙ እስራት ነበር፤ በመጨረሻም ስለፈጣሪ ሕይወቱን አሳልፎ በሮም አደባባይ በስይፍ ተቀልቶ ሞተ።
በመሆኑም በዘመናችን እግዚአብሔር በሰጠዎት ሀብት ክህነት በአልጋ ቆራኛ በደዌ ዳኛ የተያዙ ብሽተኞችን፣ ቀኑ ጨልሞባቸው በእርኩስ መንፈስ በአደገኛ ሱስ ተይዘው ሕይወታቸውን መምራት የተሳናቸውን፣ እያላቸው የሚበሉት ያጡትን፣ አፍ እያላቸው መናገር የተሳናቸውን፣ ጉልበት እያላቸው ሽባ ሆነው የሀገርና የወገን ሸክም የሆኑትን ወገኖችን ሁሉ በሀገር ውስጥና በሀገር ውጪ በተጨባጭ ማስረጃ ግልጽ በሆነ አደባባይ ከመስቀል በስተቀር ምንም ሳይጨብጡ እግዚአብሔር በፈቀደ መጠን በሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት ምክንያት ወንጀል ሆኖበዎት የመጨረሻውን ትልቁን ለቀደሙት ሐዋርያትና ቅዱሳን ሰማዕታት የተከፈልለውን ደመዎዝ ተከፋይና ተሳታፊ በመሆነዎት እንኳን ደስ አለዎት እላለሁ።
በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አንጋፋ ሊቀ ጳጳስ የሆኑትና መንፋሳዊ አባትነታቸው ፀሐይ ከሚመስለው መልካቸውና ተክለ ሰዎነታቸው ጋር የተዛመደው ገዳማዊው የማኅበረ ስላሴው አበእምኔትና በጎንደር ክፍለ ሀገር ቋራ አካባቢ ተወልደው ያደጉት ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አባ ዮሴፍ፤ ከሳምንታዊ የግል ጋዜጠኛ በወቅቱ በነበረው የቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ብዙ ጥያቄዎችን ቀረቦላቸው ነበር። ብፁዕ አባ ዮሴፍ ማንንም ሳይፈሩ ጥያቄዎችን ሁሉ በተገቢው ምላሽ እወነቱን ተናገሩ። ጋዜጠኛው ስለሊቀ ጳጳሱ ሕይወት አዝኖ፤ «አባታችን የበላይና የበታች ሳይፈሩ ይህን ሁሉ እውነት የሚናገሩት ለራስዎትና ለሥራዎት አይሰጉም» አላቸው። አረጋዊው ሊቀ ጳጳሳ አባ ዮሴፍ «እውነትን መስክሮ መሞት ከቅዱሳን አባቶቸ ከሐዋርያት የተማርኩት ነው።» በማለት መልስ ሰጥተዋል። ይኸው ቃላቸው በተቀበሩበት መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከሀውልታቸው ላይ ተጽፎ የዘመናችን መሪና አስተማሪ ኃይለ ቃል ሆኖ ይገኛል። ቤተ ክርስቲያንን የተሳለመ ሁሉ ይን ቃል ያነባዋል እውነትን የመናገር መንፈሳዊነትን በቀላሉ ይማራል። በመሆኑም እርሰዎ መልአከ መንክራት ቀሲስ ግርማ የተከሰሱበት እውነትንና ታላቋን ቤተ ክርስቲያን የሀብተ ክህነት ተስፋ መንፈሳዊ አገልግሎት በተግባር በመተርጎመዎ የተከፈለዎት የሐዋርያት ትሩፋት ደመዎዝ በመሆኑ እንኳን ደስ አለዎት።
ዛሬ የእምነት ጎህ ቀዳጅ ዋልታ፣ ሀገር አድነት ባለውለታ፣የታሪክ መዛግብት አለኝታ፣ የዕውቅት ገብታ የሆነችው ታላቋ የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ከሰባት ሚሊዮን በላይ መቀነሳቸው የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት ሊቃነ ጳጳሳት በሚገባ ጽፈውታል የታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን በማለት አስጠንቅቀዋል። አሁን በቅርቡ በሰላሳ አራተኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ስብሰባ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የምዕመናኑ ቁጥር መቀነስና መባዘን ያሳሰባቸው መሆኑ በአጽንዖት ገልጽዋል።
በዚህ ፈታኝ ጊዜ በዕውቀታቸው ከሚመጻደቁት መካከል ሳይሆ ከደካሞች መካከል እግዚብሔር እርሰዎን አስነስቶ በሀብተ ክህነት ላይ የሰጠውን ኃይል አበርቶ የቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ከተያዙበት ደዌ፣ ከያዛቸው ከእምነታቸ ካጠፋቸው አጋንንት እያጠመቁ እያዳኑ ከጠፉበት በረት ተመልሰው እዲገቡ በማድረገዎት፤ በልዮ ልዮ መንገድ የጠፋውን ምዕመናን መልሶ በመፈለግ በሚችሉት መጠን በመንፈሳዊ የሀብተ ክህነት አገልግሎት ቤተ ክርስቲያኗ ቀዳሚ ሐዋሪያዊት መሆንዋን ለውጪ ሀገር ሰዎች ችጭምር በታሪክ ብቻ ሳይሆን በተግባር ለማስተዋወቅ መታደለዎት፣ የሰው ልጆች ከወደቁበት አዘቅት ወጥተው ጤናማ ሕይወታቸውን እንዲመሩ በማደረገዎት ለዚህም የቀደሙት ሐዋርያት የተሰጣቸው የእስራት ክፍያ በማግኘተዎት እንኳን ድስ አለዎት።
በአሁኑ ወቅት አንዳንድ በማስመሰል ክህነት እየተቀበሉ የክህነት አርማ እየደረቡ በቤተ ክርስቲያንና በእግዚአብሔር መካከል የተሰጣቸውን ከባድ መንፈሳዊ አደራ ዘንግተው የገቡትን ቃል ኪዳን ሽረው ከህነቱን የግል ጥቅማቸው ማስፈጸሚያ ከማደረግ በስተቀር ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ ሆነው ባልተገኙበት፤ ይልቁንም እነሱ በሚፈጽሙት ተግባረ እየተሰናከለ ከዋርያዊት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በረት እየወጣ ጫካ የሚገባና በአውሬዎች የተነጠቀው ቁጥር እየበዛ በመጣበቱ፣ የተከፋፈለውና የተለያየው የመንጋው አካል መጠነ ሰፊ በሆነበት፤ በተለይም ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን እያሉ እያዋቀሩ በቤተ ክርስቲያን ጉልላት የተደራጁ ግለሰቦች ተፈናጠው ደገኛውን አማኙን ሕብረተሰብ የሚያታልሉት ብዙዎች በሆኑበት፤ ከእነ ጭራሹም እኔ በምኖረበት በለንደን ከታማ በቅዱስ ሲኖዶስ ቡራኬና የተመሠረተችውን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ሽጠው ለመከፋፈል ለፍርድ ቤት ጥያቄ ያቀረቡ «ካህናት» መሰል ተቃዋሚ ፓለቲከኖችና ተከታዮቻቸው በአመጽ በሰከሩበት በአሁኑ ዓይን ያወጣ የክህደትና የፈተና ዘመን፤ ምዕመናን ተዘዋውረው በማስተማረዎ በእግዚአብሔር ፈቃድ የታላቋን ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ፀጋ በረክት ተካፍለው ማካፈለዎ ምዕመናን በሚችሉት መንገድ በአግባቡ መጠበቀዎ የጠፉትን በመፈለገዎ የተከፍለዎ የእስራት ደመዎዝ በመሆኑ እንኳን ደስ አለዎት።
ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመታዊ የጥቅምት ጉባዔ ላይ እንዳለ አውቃለሁ፤ እርሰዎን መልአከ መንክራት ቀሲስ ግርማ ወንድሙን ክህነት ሰጥቶ ለአገልግሎት እዳሰማራዎት እንረዳለን፤ አገልግሎተዎም የሚፈጽሙት በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ መሆኑ ይታወቃል። የሚሰጡት አግልግሎትም በቀኖና ሐዋርያት የተደገፈ የማጥመቅና የመፈውስ መንፈሳዊ አገልግሎት መሆኑን ይታመናል። ለዚህም ብዙዎች ጠንካራ የሚባሉ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ምስክርነታቸውን ሲሰጡ ቆይተዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ለዕርሰዎ ለቀሲስ ግርማ ምን ዓይነት የአገልግሎት መመሪያና የሥራ ዝርዝር እንደሰጠዎት አላውቅም። አግልግሎተዎት ሰፊ ተገልጋዮቹም በርካታ እንደመሆኑ መጠን አገልግሎተዎትን የሚያጠናክር ልዮ መመሪያን እንደሚስፈልገዎት እረዳለሁ። ሆኖም ሰብሕዎ በክህሎቱ ነውና በሚችሉትና እግዚአብሔር በፈቀደለዎት መጠን በዚህ የማጥመቅ አገልግሎት ተሰማርተው የቤተ ክርስቲያንኗ አንጡራ ሀብት የሆኑት ምዕመናንን እያገለግሉ ቆይተዋል። አሁን እያገለግሉ እደሚገኙ ለማንም ግልጽ ነው። በዚህ መንፈሳዊ አገልግሎተዎት በሀገር ወስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገር ጭምር ታውቀዋል። በዘመናችን በሳይንሳዊ ጥናት የላቀ ዕውቀት አለን የሚሉት ሁሉ እስኪደንቃቸው ድረስ ብዙ በሽተኞችን በእንግዚአብሔር ፈቃድ እንዲፈወሱ ምክንያት ሆነዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ እርሰዎ የሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉ በተሰጠዎት ክህነት በመሆኑ እያንዳንዷ አግልግሎት ቤተ ክርስቲያንዋን ወክሎ የተከናወነ መሆኑን ከሁሉም በላይ የቤተ ክርስቲያንኗኝ ሐዋርያዊነት ይበልጥ በተግባር ያስተዋወቁ መሆነዎትን እንደሚረዳ ተስፋ አደርጋለሁ። ከዚህ አንጻር የቀረበበዎት ክስ እንደተመለከትነው ሆን ተብሎ የተቀነባበረ እንደሆነ በመረዳት ወይም በትክክል መጣራት እንዳለበት ሰፊ ትኩርት ይሰጥበታል ብየ አስባለሁ። ምንም እንኳን እርሰዎ ቀሲስ ግርማ ከቀደሙት ሐዋርያት የበለጠ ሕይወት ባይኖረዎትም፤ የአባቶቻችን የሐዋርያት ጉባዔ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ወቅት አብሮ የመታሰር ስሜት ወይም እንደ እኔው እንኳን ድስ አለዎት በማለት በደሉን ማሰማት ብሶቱን በማጽናናትና በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚፈቱበትን መንገድ ማመቸት ይኖርበታል ብየ እገምታለሁ። እሁንም በድጋሜ ለተከፈለዎት የገልግሎት ዋጋ እንኳን ደስ አለዎት።
መንግሥት ወንጌልን የሚሰብኩ፣ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዘው ለሀገርና ለወገን ሸክም የሆኑትን ወገኖች በተሰጠዎት ፀጋ በመንፈስ ቅዱስ ዕርዳታ ምክንያተ የድህነት ክህነታዊ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ መሆነዎትን፤ በአጋንንትና በአድንዛዥ ዕጾች ተተብትበው አስቸጋሪ ዜጋ የሆኑትን መልሶ በማነጽ የሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ተሳታፊ ኃይል እንዲሆኑ የሚያደርጉትን መንፈሳዊ ጥንካሬ፣ ዜጎችን በጤነኛ አስተሳሰብ መልሶ የማቋቋምና በሞራል ግንባታ የሚደርጉትን አስተዋጽዖ፣ ሁሉም በወንጌል ተመርቶ በሰላምና በፍቅር በመረዳዳትና በመፈቃቀር አንዱ አንዱን እንዳይበድል በማስተማር ከፓለቲካ የፀዳ ትምህርት በማስተማረዎት፣ በጠቅላላው ሰዎች ሰላማዊ ግኑኝነትና የተረጋጋ በጸሎት ላይ የተመሠረተ ሕይወት እንዲኖራቸው ምክር በመስጠት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ጎሳ፣ ዘር፣ ቀለም፣ የትውልድ ቦታና ሀገር ሳይለዩ የሚሰጡትን አገልግሎት በሕግና በሥርዓት የተከበረና ተጠናክሮ የሚቀጠልበትን ሁኔታ ማበረታት እንደሚገባ ይሰማኛል።
ይሁን እንጅ የሀሰት ከሳሾች ተነስተው ብዙዎችን የሚያገለግሉትን መንፈሳዊ አባት ምክንያት ፈልጎ ዘብጥያ መጣል የማይገባ ተግባር መሆኑ ሁላችንም መረዳት ይኖርብናል። ይህ አስከፊ ተግባር ከቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ትሩፋት በመሆኑ እንኳን ደስ አለዎት። ሆኖም በሥጋዊ አስተሳሰብ ያሉት መሪዎች አሁንም በድጋሜ በሰፊ አዕምሮ በሰከነ አስተሳሰብ አጥንተው በአጭር ጊዜ ውስጥ በሰላም ተለቀው የሚሰጡትን መንፈሳዊ አገልግሎት ከማዳከም ይልቅ እንዲ ያጠናክሩት እመኝለዎታለሁ።
እኔ በግሌ በበኩሌ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይነቴና ወዳጅነቴ እግዚአብሔር በፈቀደ መጠን የሰጡትን መፈሳዊ አገልግሎት መማስታዎስ በበሽታ የጠወለገን፣ በጋንንት የተከበበውን፣ በምጥፎ ሱስ የዛለና የተበላሸውን ዜጎቻችንና የውጪ ሀገር ሰዎችን ጭምር መንፈሳዊ ሕይወት መልሶ በማነጽ ቀኖና ሐዋርያት በሚፈቅደው መሠረት በሀብተ ክህነት በመንፈስ ቅዱስ ዕርዳታ ሲያገለግሉ በመቆየተዎ ምክንያት በዘመናችን የቅዱሳን ሐዋርያት በረከት የሆነው የሀሰት ክስ እስራት ደመዎዝ ስለተከፈለዎ መልአከ መንክራት ቀሲስ ግርማ ወንድሙ እንኳን ደስ አለዎት በማለት መንፈሳዊ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ። እግዚአብሔር እርሰዎን መሣሪያ አድረጎ ከበሽታቸው የፈወሳቸው ሰዎች አምላክ እንዲረዳዎት ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን!
ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ
ካለችው ከተማ ድውያንንና
በርኵሳን መናፍስት የተሣቀዩትን
እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤
ሁሉም ይፈወሱ ነበር። 17 ሊቀ
ካህናቱ ግን የሰዱቃውያን ወገን
ሆነውም ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ
ተነሡ ቅንዓትም ሞላባቸው። 18
በሐዋርያትም ላይ እጃቸውን
ጭነው በሕዝቡ ወኅኒ ውስጥ
አኖሩአቸው።የሐዋ ሥራ 5፥
ምንም መወራጨት አያሥፈልግም የወያኔ መንግሥት ታዋቂ ህዝብን ትኩረትና ተቀባይነት ያላቸውን ሁሉ ይገላል ያሥራል ከሀገር ያሥወጣል
This is the 21st century and human beings have done away with childish things like majic and religious “fews”. Memhir Girma or Tamrat Geleta or anyone promising religious or Tenwquola “fews” has no place in the modern world.
It is not surprising why money is envolved in these cheating scandals.
yebego neger telat satnael yesherebew ymeslal getam besnbet beshitegn fewese ewur abera teblo new yetekesesew egziabher Bertatun hilun endisetachw laba girma bemehaym andebetachin hulachin enlemnalen
Abebech. Are you trying to tell us you are civilized and modern? Are you trying to compare Tamirat and Aba Girma? By the way how much are you paid to say your nonsense? This is not a surprise for a man of God. Ewnet and Fikir said it all so got nothing to add
Ye Egzabiher sewochu hulem yfetenalu Amen!!!
yihe uhlu wenjel erasachew yiakenebaberute new ;yemenafkan sera new
yemenafekan sera new ;menafekan yegzabihirn mengst aywrsum
memher germa egzabehir tegawen setuwachwan ;enante selerasachew eweku
menafikan weyouleshe?
We cannot say anything about the honesty of Memhir Kebede. This is a civil issue. I believe that posting such cases should take place after a court verdict. However, posting this uncertain story is more likely funning things. Moreover, it is killing the reputation of many priests and the Church itself.
While there are more burning issues that can be educational, why diverting the attention of the public on such an issue?
አንተም ሆንክ መምህር ግርማ ዳግም ከመንፈስ ቅዱስና ውሀ ተወልዳችሇል ወይ?, ክርስቲያን ማለት ከሰው ወይም ከእናትና አባት ተወልዶ ጌታ እየሱስን ማመን ብቻ አይደለም,ክርስቲያን ለመሆን ከውሀና ከመንፈስ ቅዱስ ተወልዶ የመንግስተ ሰማይ ዜጋ መሆን ማለት ነው ።
መምህር ግርማ ወንድሙ ክስና የአገልግሎት ፍቃድ እንዲሁም ሀይማኖታዊ ተቀባይነት
መምህር ግርማ ሓሳዌ መሲህ ይሁኑ እውነተኛ አገልጋይ አስተያየት ለመስጠት የሚያበቃ መረጃ የለኝም፡፡ እኔ ደግኖ እንደ ሽዋ ዝም ብየ በላውቀው ጉዳይ ላይ አልቀደድም፡፡ በእርግጥ መምህሩ ብዙ ሰዎች ሲያለፋልፉ ጠበል ሲያጠምቁ በዓይኔም በጀሮየም አይቻሎህ ሰምቻሎህ፡፡ ግን እንደ አማኝ ያታልላሉ ብየ ባላምንም ሰው ናቸውና አያደርጉም ብየ አልከራከርም፡፡ ምክንያቱም ሽይጣን በትልልቅ ሰዎች ላይ ፈተናውን ያበዛልና፡፡
አሁን የክሱ ጉዳይ ስመለከተው ተራ የመንደር ወሬ ነው፡፡ ዋስትና ለከልከል ይቅር እና ክስለመመስረትም የሚያበቃ አይደለም፡፡እንደ ወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ስርዓት ሕጋችን እንዲሁም ህገመንግስታችን ማስረጃ የሌለውን ነገር አያሰከስስም፡፡ተበደልኩ የሚሉን ተበዳይ ነኝ ባይ ግለሰብ ብሩን ለ መምህር ግርማ ወንድሙ ሲሰጡ ማን አየ መቸ ነው በምን ሰጡአቸው የሚሉ ነገሮች የሚያግባቡን አይመሰለኝም፡፡
ግብ ቅናት የያዛቸው ሰዎች ሆን ብለው እሳቸውን ለመነጀስ ያደረጉት ይመስላል፡፡ ለማንናውም ጢማቸውን ላጭተው መፍታታቸው ስለማይቀር ኣያሳስበንም፡፡ እግዚአብሄር ያውጣቸው እያልን ብንፀልይ ይሻላል፡፡
ፖሊስ መምህር ግርማ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆነው ወንጀል የተፈፀመው መስከረም 2006 ዓ.ም ነው ብሏል።በየካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሰን ግሮሰሪ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩት አቶ በላይነህ ከበደ በመምህር ግርማ የማታለል ወንጀል የተፈጸመባቸው ግለሰብ ናቸው:እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እኚህ ግለሰብ ከትዳር አጋራቸው ጋር 400 ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ መኖሪያ ቤታቸው ይኖሩ ነበር።
እንደ ምርመራ መዝገቡ መምህር ግርማ የግል ተበዳይን እምነት በመጠቀም የምትኖርበትን መኖሪያ ቤት እስከ ጥር 30 2006 ሽጠህ ካልወጣህ አስከሬንህ ይወጣል ይሏቸዋል።
የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚለው ልጅ ያልወለዱት ባልና ሚስት ከመሞት መሰንበት በማለት ይህንን ቤት በጣም በዝቅተኛ ዋጋ በ800 ሺህ ብር ይሸጡታል።ቤቱ በዚህ ዋጋ እንዲሸጥ መምህር ግርማ በራሳቸው ሰዎች አማካኝነት ብዙ ያልተገባ ስራ ሰርተዋል ነው የሚለው የምርመራ መዝገቡ።ከዚያም መምህር ግርማ በዚህ ብቻ ሳይመለሱ የግል ተበዳዩን ቦሌ አካባቢ በራዕይ ያየሁት ቦታ አለ እዚያ ነው ገዝተህ የምትኖረው ይሏቸውና ሌላ የማታለያ ዘዴ ቀየሱ ይላል ምርመራው።
ቤቱ የተሸጠበትን 800 ሺህ ብር አምጣና እንዲበረክትልህ ልፀልይበት ብለው ወሰዱ፤ በዚያው ውለው አደሩ፤ የግል ተበዳዩም በእርሳቸው ላይ ያላቸው እምነት ባለመጥፋቱ በትዕግስት ስልክ ቢደውሉላቸውም ስልካቸው ዝግ ሆነባቸው ይባስ ብሎ ከሀገር ወጡ ተባለ።ሁኔታው ማታለል መሆኑን ስለተረዱ 2007 መጋቢት ወር ገደማ ወደ እኛ መጥተው አመለከቱ የሚለው ፖሊስ እርሳቸው ከሄዱበት እስኪመለሱ የግል ተበዳዩን እና የምስክሮችን ቃል ተቀብሎ ቆይቶ ተጠርጣሪው መምህር ግርማ ወንድሙን ትናንትበቁጥጥር ስር አውሏቸው ነው ዛሬ ፍርድ ቤት ያቀረባቸው።
ተጠርጣሪው እኔ የተባለውን ሰው ቀይ ይሁን ጥቁር አይቼው አላውቅም፤ ሆን ተብሎ ከጀርባ የተጠነሰሰብኝ ሴራ አለ በማለት ለችሎቱ አስረድተዋል።ጠበቃቸውም የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የሚከለክል አይደለም፤ ፖሊስም የሚጠበቁ ምርመራዎቹን አጠናቋል፤ ደንበኛዬ የዋስትና መብታቸው ይከበርልኝ በማለት ጠይውቋል።ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጓል።