ዶክተር አበበች ጎበና እና ሥራዎቻቸው

Dr Abebech Gobena

ከ30 ዓመታት በፊት የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ያቀናሉ። እናም ያኔ ወቅቱ በሀገሪቱ የረሃብ አደጋ ያጠላበት ጊዜ ነበርና አንዲት ሕፃን የእናቷ አስክሬን እቅፍ ስር ሆና ጡት ለመጥባት ትሞክራለች። ይህ ትዕይንት እጅግ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ይከታቸዋል። ሕፃኗን ከሌላ አንዲት ሕፃን ጋር ይዘውም ለማሳደግ ይወስዳሉ። እናም ወዲያው 21 ሕፃናትን ለመርዳት ያሰባስባሉ። ሆኖም ባለቤታቸው እና የሥራ አለቃቸው ከሕፃናቱ ወይ ከእኔ አለያም ከሥራዎ የሚል ከባድ አጣብቂን ውስጥ ይከቷቸዋል። ሆኖም እሳቸው ለሕፃናቱ ይወስናሉ። በአሁኑ ወቅት ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ከ12 ሺህ በላይ ሕፃናትን ይረዳሉ… Listen