የአቡነ ፋኑኤል የተሐድሶ እንቅስቃሴዎች በሀዋሳና በዋሽንግተን ከተሞች

በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በምትገኘው ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ የተፈጠረው ዓይነት ብጥብጥና ረብሻ ከጥቂት ዓመታት በፊት ሀዋሳ ውስጥ በምትገኘው ድብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ውስጥም ተከስቶ ነበር። ሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ያደራጁት ቡድን አሉባልታ በማስወራትና ምዕመናንን ግራ በማጋባት ለአመጽ በማሰለፍ ቤተክርስቲያን ውስጥ የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ አድጓል። ዋሽንግተን ውስጥ መምህር ተስፋዬ መቆያ “የቅድስት አርሴማ የጽዋ ማሕበር” በማለት ካቋቋመው ማህበር ጋር ተቃራራቢ ስም ያለው “የኪዳነ ምሕረት የጽዋ ማህበር” የሚባል የማጭበርበሪያና መዝረፊያ ማህበር በዲያቆን ያሬድ አደመ መሪነት ሀዋሳ ውስጥ በማቋቋም በቤተክርስቲያንና ምዕመናን ላይ ከፍተኛ ችግርና ጉዳትን አድርሷል።

አቡነ ፋኑኤል ባደራጁት የዘረፋና የብጥበጣ ማህበር በሚያገኙት ሽፋን በመጠቀም እጅግ ስር የሰደዱ የአስተዳደር በደሎች፣ምዝበራዎችና አባታዊ ያልሆኑ ንግግሮችን አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የደብሩን ምዕመናን በማሳዘናቸውና በማስቆጣታቸው ምክንያት ምዕመናን ከፍተኛ ተቃውሞና ትግል በማድረግ ከሀዋሳ ከተማ አባረዋቸዋል። እኝሁ የተሐድሶ እምነት አጋፋሪ የሆኑና የተለያዩ ህጸጾች ያለባቸውን ሰው እንደ ትክክለኛ አባት አሽሞንሙነው እነ ቄስ ዘላላም አንተነህ፣ ቄስ አብርሀም ሐብተ ስላሴ፣ ቄስ ኤሊያስ መዐዛና መሰሎቻቸው በዋሽንግተን ዲሲ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሰገነት ላይ እንዲፈራጠጡ ለማድረግ የረቀቀና በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚደረግ መሰሪ ተግባር በማካሄድ ላይ እንደሆኑ ተደርሶበታል። በዚህም መሠረት ቤተክርስቲያኗን በጉልበት ከተቆጣጠሩ በኋላ ምክንያቱና ዓላማው ግራ በሚያጋባ መልኩ ቄስ ዘላለም አንተነህ “ቤተክርስቲያኗ ገለልተኛ አይደለችም” በማለት አውደ ምህረት ላይ ማወጃቸው ለአቡነ ፋኑኤል መንገዱን በማመቻቸት ላይ ለመሆናቸው ማረጋገጫዎች ናቸው። መምሕር ተስፋዬ መቆያም ከሀዋሳ ጀምሮ ከአቡነ ፋኑኤል ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዳለውና እዚህ አሜሪካም ውስጥ ሹመት እንደሰጡት ይታወቃል።

እነዚህ የአቡነ ፋኑኤል ተላላኪዎች በዚህ ተግባራቸው በርካታ ቁጥር ያላቸውንን ምዕመናንን አሳስተው ደጋፊዎቻቸው ለማድረግ የቻሉበት ሁኔታ አለ። የዲሲ ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ማዕምራን ቀሲስ አማረ ካሳዬ ለእነዚህ የቤተክርስቲያን ጠላቶችና የተሐድሶ አስተምህሮ አቀንቃኞች የጉሮሮ አጥንት ስለሆኑባቸው ያልሆኑትን ስም በመስጠትና የራሳቸውን ጉድፍ በሌሎች ላይ በማላከክ ከቤተክርስቲያብ አለቃነታቸው ለማንሳትና ለማዋረድ የተለያዩ ደባዎችን በመፈጸም ላይ ናቸው። የዲሲ ማርያም ቤተክርስቲያንን በር ሰብረው የተቆጣጠሩት እነዚህ ግለሰቦች ያደረጉትን ዓይነት ተመሳሳይ ተግባር በሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ውስጥም እነዲያቆን ያሬድ አደመ ፈጽመዋል። ይህ በወያኔ ሲኖዶስ ማዕከላዊነቱን በጠበቀ ሁኔታ የሚካሄድ እኩይ ተግባርን የሚያጋልጡና ከዲሲ ማርያም ቤተክርስቲያን ጋር ስላለው ግንኙነትና ተመሳሳይነት የሚያሳዩ እራሳቸው አስረጂ የሆኑትን እነዚህን ቪዲዮዎችን ለግንዝቤ እንዲረዱ ከዚህ ጋር አቅርበናል።