የዞን ዘጠኝ የድረገጽ ጸሐፍት ክስ ዉድቅ ሆነ

Zone 9 Bloggers in Addis Ababa

ዞን ዘጠኝ በመባል በሚታወቁት አራት የድረገጽ ጸሐፍት እና አንድ ጋዜጠኛ ላይ በሽብርተኝነት የቀረበባቸዉን ክስ ፍርድ ቤት ዛሬ ዉድቅ አደረገ። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ላይ የቀረበዉ ማስረጃ ሁሉ ደካማ መሆኑን ማመልከቱን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ የወሰነላቸው በሌለችበት የተከሰሰችው ሶሊያና ሽመልስ፣ ናትናኤል ፈለቀ ፣ አጥናፍ ብርሃነ እና አቤል ዋበላ ናቸው ። በዚሁ መሠረትም ዛሬ ማምሻዉን ከእስር ቤት እንደሚወጡ ይጠበቃል። በሌለችበት በተመሳሳይ የተከሰሰችዉ የዞን ዘጠኝ አባል ሶልያና ገብረሚካኤልም በስደት ሀገር ብትሆንም ክሱ እንደተነሳላት ተገልጿል። ሶልያና ከ18 ወራት በኋላም ቢሆን ክሱ ዉድቅ መሆኑ መልካም መሆኑን ለዶቼ ቬለ ገልጻለች። Listen