“ስትሮክ” (Stroke) ምንድ ነው? መከላከል የሚችሉት አደጋ፤ ወይስ? በሕክምናስ ይረዳል?

Signs of stroke
የአንጎል የደም ሥሮች ደም የማዘዋወር ሥራቸውን ሲያቋርጡ አለያም በአንጎል ውስጥ ደም ሲፈስ የሚከሰት ድንገተኛና አደገኛ የሕመም ሁኔታ ነው።

የሕመሙን ምልክቶች፤ ለድንገቱ አጋላጭ የሆኑትን ሌሎች የሕመም ዓይነቶች፥ የመከላከያ አማራጮችና እንዲሁም አጣዳፊ የሕክምና እርዳታና ሊገኙ የሚችሉ ውጤቶች የሚመረምር ተከታታይ ዝግጅት ነው።

በሕክምናው ዘይቤ “ስትሮክ” (Stroke) በሚለው መጠሪያው የሚታወቀውን የዚህን የጤና ሁከት ምንነት ጨምሮ ሌሎች ተዛማች ጥያቄዎች የሚመልሱት በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በአትላንታ ከተማ በነርቭና በአንጎል ሕክምና አማካሪ ሃኪምነት በማገልገል ላይ የሚገኙት ዶ/ር ዳንኤል ተስፋዬ ናቸው።

“ስትሮክ” (Stroke) ምንድ ነው? ያድምጡ

ስትሮክ’ን ለመከላከል የሚያግዙ መንገዶች ይኖሩ ይሆን? ያድምጡ

የሕክምና አማራጮች ያድምጡ