ትግሉ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ወይንስ ለምኒልክ ቤተመንግሥት?
ይገረም አለሙ
ፈጣሪ ዕድሜ ከጥንካሬ ጋር ያደላቸው በሀገር ጉዳይ የማይታክቱት ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ሰሞኑን በምድረ አሜሪካ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር ያደረጉትን ውይይት፤ ዘመነ ቴክኖሎጂ ምስጋን ይግባውና በያለንበት ሆነነን ተከታትለናል። ከውይይቱ ታዳሚዎች ከቀረቡ በርካታ ጥያቄዎች አንዱ፣ “በያ ትውልድ ላይ ጨከኑበት” የሚል ነበር። ፕ/ር መስፍን ሲመልሱም፤ አልጨከንኩበትም እውነቱን ነው የተናገርኩት፣ አንዳንዶቹ እንደውም ተማሪዎቼ ነበሩና አነጋሬአቸዋለሁ፣ ፍላጎታቸው ለሀገርና ለሕዝብ ሳይሆን ሥልጣን ነበር ብለዋል።