ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

Mulugeta Lule
አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለየ። በትላንትናው እለት ከቀትር በኋላ እኔ ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማና ጋሽ ሙሉጌታ በሲልቨር ስፕሪግ ምሳ በልተን፣ ስለመፅሀፍ እያወራን ከዋልን በኋላ በሰላም ነበር የተለያየነው። በዛሬው እለት ግን ቨርጂኒያ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በተኛበት ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል። ድንገተኛው ሞት ለሁላችንም ድንጋጤ ፈጥሮብናል!