የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አባት በሚል ቅጥያ የሚጠሩትና የተቸገሩ ስፖርተኞችን በመርዳት የሚታወቁት አቶ አቤሴሎም ይሕደጎ አረፉ

መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገራችን አትሌቲክስ ስፖርት ሲነሳ ስማቸው አብሮ የሚነሳውና ለብዙ ሯጮች የችግራቸው ተጋሪ በመሆን አገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩት የቀስተደመና ስፖንጅ ፋብሪካ መስራች እና ባለቤት አቶ አቤሴሎም ይሕደጎ በተወለዱ በ79 ዓመታቸው ሀሙስ መስከረም 20 ቀን 2008 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የአቶ አቤሴሎም የቀብር ስነስርዓት ቤተሰቦቻቸውና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ቅዳሜ ዕለት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን የሚከናወን ይሆናል። አቶ አቤሴሎም የሁለት ወንዶችና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበሩ::
የኢሳት ዝግጅት ክፍል ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

2 Comments on “የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አባት በሚል ቅጥያ የሚጠሩትና የተቸገሩ ስፖርተኞችን በመርዳት የሚታወቁት አቶ አቤሴሎም ይሕደጎ አረፉ”

  1. ኢትዬጵያን የሚወዱ ኤርትራዊ አንድ እሣቸው ነበሩ

    እግዚያብሄር ነፍሣቸውን ይማር!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*