ኢራን የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ከተካተቱት መካከል ስምንቱ ወንዶች መሆናቸው ተገለጸ።

ከኢራን የሴቶች ብሄራዊ ቡድን አባላት ውስጥ ከተካተቱት መካከል ስምንቱ ወንዶች መሆናቸው ተገለጸ።ለኢራን እግር ኳስ ሊግ ቅርብ ናቸው የተባሉት ሞጅታቢ ሻሪፊ፥ “ስምንቱ ተጫዋቾች ጾታቸውን ለመቀየር ያደረጉትን ቀዶ ጥገና ሳያጠናቅቁ በተለያዩ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፈዋል” ማለታቸው ተሰምቷል።ለዚህም የሀገሪቱ የእግር ኳስ አመራሮች ትችት እየተሰነዘረባቸው ነው።

ባለስልጣናቱ የብሄራዊ ቡድኑ እና በሀገሪቱ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾች የጾታ ምርመራ እንዲያደርጉ አዘዋል። ዘ ሰን እንደዘገበው ከእነዚህ ስምንት ተጫዋቾች ውስጥ ምን ያህሉ ወንድ ሆነው እንደተወለዱ አይታወቅም።ተጫዋቾቹ የሆርሞን መጠናቸው ከወንዶች ጋር ተቀራራቢ የሆነ አልያም በተፈጥሮ ወንድ ሆነው የተወለዱ እና ጾታቸውን ለመቀየር የሚፈልጉ ሳይሆኑ አይቀርም ተብሏል።የኢራን ብሄራዊ ቡድን በተመሳሳይ በጾታ ማጭበርበር ሲታማ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።ባለፈው አመትም አራት የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ወንድ ሆነው መገኘታቸው የሚታወስ ሲሆን፥ በ2010 የብሄራዊ ቡድኑ ግብ ጠባቂ ጾታም ጥያቄ ሲያስነሳ ነበር። በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ በ2014 አስገዳጅ የጾታ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ አስተላልፋ ነበር።

ከኢራን የሴቶች ብሄራዊ ቡድን አባላት ውስጥ ስምንቱ ወንዶች ናቸው ተባለ

ምንም እንኳን ሴቶች በወንዶች መካከል የሚካሄዱ የእግር ኳስ ግጥሚያዎችን መከታተል የሚፈቀድላቸው ባይሆንም ኢራናውያን የእግር ኳስ ጨዋታ አፍቃሪዎች እንደሆኑ ይነገራል።የኢራን የሴቶች ፉትሳል ቡድን በዚህ ሳምንት የ2015ቱን የእስያ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ዋንጫን ሲያነሳ ቡድኑ ያሳየው ብቃት በአለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።የቡድኑ አምበል የ30 አመቷ ኒሎፋር ርዳላን ባለቤቷ በውድድሩ ላይ እንዳትካፈል በመከልከሉ ከቡድኑ መቀነሷ የሚታወስ ነው።በሀገሪቱ የሼሪያ ህግ መሰረት ርዳላን ፓስፖርቷን ለማሳደስ የባለቤቷ ፊርማ ግድ ይላታል።ኢራን ከ1979 ወዲህ ጾታን በቀዶ ጥገና መቀየር የፈቀደች ሲሆን፥ ይህም ሀገሪቱ ከምትከተለው የሼሪያ ህግ ጋር የሚጣረስ ነው በሚል ትችቶችን እያስተናገደች ነው።