አንድ መሆን ያልቻልንበት ሚስጥርና ማድረግ የሚገባን ተግባር (በነፃነት ለሃበሻ)
አገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ ብሔራዊ ክብሯንና ማንነቷን በረገጡ ግለሰቦች መገዛት ከጀመረች እንሆ 25 አመታት ሆኗቷል። የኢጣሊያንን የከፋፍለህ ግዛው ፓሊሲ የብሔር ካባ አልብሶ ወያኔ እኛን አዋርዶ የመግዛቱ ሚስጢር ምን ይሆን? ይህን እውነት ደረጃ በደረጃ ለመዳሰስ እሞክራለሁ። ከእኔ በተሻለ ሁኔታ የዚህን ፋሽስት ቡድን እኩይ ተግባር የሚያውቁ እንዳሉ አምናለሁ። ሆኒም ግን እኔ እንደ አንድ አገሩን ወዳድ ኢትዮጵያዊ የድርሻዬን ለወገኔ ማሳወቅ ስላለብኝና ለውጡን ማፋጠን ስለሚገባ ይህን ፅሁፍ ለማቅረብ ተገድጃለሁ። ህወኃት/ ወያኔ ኢትዮጵያን የማዳከምና የመበታተን አጀንዳ የነደፈው ገና በ1967 ዓ• ም ነፍጥ አንግቦ ወደ ጫካ ሲገባ ነው። ለዚህም አላማው ስኬት በማኒፌስቶ አዘጋጅቶ የተንቀሳቀሰባቸው ምክንያቶቹና የአሁኑ የጥፋት ስኬቶቹ እንደሚከተለው ይቀርባል።
1• የአማራን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል ፕሮፓጋንዳ መስራት።
የአማራ ገዥዎች በዘመናቸው በነበረው ስርዓት ጨቋኝ ቢሆኑም፣ ብሔርን ማዕከል ያደረገ ብሔራዊ ጭቆና ፈፅሞ አልሰሩም። አገራችን ኢትዮጵያ የአሁኑን ማንነቷን እንድትይዝ መላውን የአገራችንን ህዝቦች በማንቀሳቀስ ወራሪዎችን አንበርክከዋል እኛንም አስከብረው ኖረዋል። ይህ እውነተኛ ታሪክ ደግሞ ለመሰሪው የትግራይ ቡድን የጎን ውጋት ነበር። ስለዚህ ይዘውት የተነሱት አጀንዳ አማራውን በሌላው ህዝብ እንዲጠላና ኢትዮጵያን እንደፈለጉ መበታተን ነው። የአማራ ህዝብ እየተራበ ለአገሩ የሚሞት፣ ሌላውን ወንድሙን የሚያከብር በኢትዮጵያዊነቱም የማይደራደር ኩሩ ህዝብ ነው። ወያኔ ይህን ህዝብ ከሌላው ህዝብ መለየትና ማዳከም ኢትዮጵያን የማዳከም አንዱ አካል አድርጎ ነው የተነሳው። የዚህም መገለጫው ካለፉት 25 ዓመታት ጀምሮ የአማራ ህዝብ በሚኖርበት አገሩ በአርባ ጉጉና በበደኖ በግፍ ታርዷል፣ ከእነ ህይወቱ ወደ ጉድጓድ ተጥሏል። በተጨማሪም በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል ክልሎች በግፍ ተገድሏል፣ ተፈናቅሏል፣ እየተፈናቀለም ይገኛል።
2• የኦርቶዶክስ ኃይማኖትን ደረጃ በደረጃ ማዳከምና ማጥፋት
የዚህ እኩይ ቡድን ሰይጣናዊ ሰይፍ የተመዘዘው ለዛሬዋ ኢትዮጵያ የእውቀት፣ የነፃነትና የታላቅነት ምክንያት የሆነችውን ቤተክርስቲያን ደረጃ በጀረጃ ለማዳከም ነው። በቤተክርሲቲያኗ ዶክትሪን መሰረት አንድ ጳጳስ በህይወት እያለ ሌላ ጳጳስ አይሾምም። ወያኔ የራሱን ካድሬ ጳጳስ ለማስቀመጥና የምዕመናንን አንገት ለማስደፋት ይህን ቀኖና በግልፅ አፍርሷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአማራ ገዥዎች እምነት ስለሆነ መጥፋት አለበት ብለው ነው እነዚህ ጉዶች የተነሱት። ሆኖም ግን ሰፊው የትግራይ ህዝብ የዚህ እምነት ተከታይ መሆኑን ለምን ዘነጉት? አክሱም ፅዮንን አፄ ምኒልክ ነው ወይንስ አፄ ቴዎድሮስ ያሰሩት? ይህን ለታሪክ እንተወዋለን። ኦርቶዶክስን ለመታደግ የተፈጠረው ማህበረ ቅዱሳንም የወያኔ ጡንቻ በተለያዬ ጊዜና በረቀቀ መንገድ አርፎበታል። ይህች ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ህዝብና ለኢትዮጵያዊነት ክብር ያበረከተቸው ታላቅ ታሪክ ሊያሸልማት ሲገባ ሰይፍ ተመዞባታል።
3• የኢትዮጵያ የነፃነትና የሉአላዊነት ባንዲራን ማስወገድ
ይህ የጥፋት ቡድን በሶስተኛ ደረጃ ይዞት የተነሳው አላማ አባቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ደማቸውን አፍስሰው፣ ህይወታቸውን ሰውተው ያቆዩልንን የነፃነት አርማ የሆነውን ባንዲራ ማቃለልና ማጥፋት ነው። በመሆኑም በረሃ እያሉ የዱቄት ማሰሪያ አድርገውታል፣ ረግጠውታል። ወደ መሃል ሲገቡም በግልፅ አቶ መለስ ዜናዊ ባንዲራ ጨርቅ ነው በማለት ተሳልቀውበታል። በመጨረሻም በማንነታችን አሻራ ላይ ወደ ስልጣን ያመጣቸውን የአምላካቸውን የሉሲፈርን አርማ በማስቀመጥ በህልውናችን ላይ ተሳልቀዋል።
4• የአማርኛ ቋንቋን ደረጃ በደረጃ ማዳከምና ማጥፋት
የደደቢቱ የጥፋት ቡድን በማኒፌስቶው ያስቀመጠው አራተኛው ኢትዮጵያን የማፈራረሻ ስትራቴጅው የአማርኛ ቋንቋን ማጥፋት ነው። ወያኔ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ በፍጥነት የተገበረው ይህንን እውነት ነው። ክልሎች በራሳቸው ቋንቋ ይማሩ ይተዳደሩ በሚል የክፋት ካባ ተገበረው። ህዝቦች በቋንቋቸው አይማሩ አይተዳደሩ የሚል አመለካከት የለኝም። ሆኖም የዚህን የጥፋት ቡድን ጤንነት የጎደለውን ስውር ተንኮል ለማጋለጥ እንጅ። ዛሬ በዩንቨርስቲዎች ተማሪዎች መግባባት እየተቸገሩ ነው። በተለይም በኦሮሚያ ላይ ወያኔ የሰራው ተንኮል ትውልድ ይቅር የማይለው ነው። የኦሮሚያ ተወላጆች በአገራቸው ቋንቋ ብቁ ሆነው ስልጣኑን እንዳይቀናቀኑት አንድ ትውልድ አምክኗል።
5• ኢትዮጵያዊነትን ደረጃ በደረጃ በመሸርሸር ማጥፋት
የደደቢቱ የማፍያ ቡድን ሌላው ስውር አላማ እያንዳንዱ ግለሰብ ኢትዮጵያዊነቱን እየተው በብሔር ማንነቱ ላይ እንዲንጠለጠል ማድረግ ነው። ይህም ባለፉት አመታት ለወያኔ ትልቅ ስኬትን አጎናፅፎታል። በአጠቃላይ ወያኔ ከመነሻው ጀምሮ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ጠላት ሆኖ የመጣ ቡድን በመሆኑ ላለፉት 25 አመታት ወዳጅ ልናደርገው ቢሞከርም አልተቻለም። በመሆኑም አሁን ከሆነብን ችግር በላይ ሳይሆንብን እንንቃ፣ እንደራጅ፣ እንነሳ!!” ለዚህ የጥፋት ቡድን ምላሽ ምን መሆን አለበት?
1• የብሔር ታፔላችንን በመቀዳደድ ኢትዮጵያዊነታችንን ማጉላት
2• እርስ በእርስ የምናደርገውን ሽኩቻ በአስቸኳይ አቁመን ለነፃነታችን አንድ መሆን
3• ከወያኔ የንግድ ድርጅቶችና ደጋፊዎቻቸው ጋር ምንም አይነት ግዢ አለመፈፀም
4• በዩንቨርሲቲዎች የምንገኝ ወጣቶች በጋራ መሰባሰብና ህዝባዊ አመፆችን ማቀጣጠል
5• የመንግስት ሰራተኛው በግልፅ ስርዓቱን መንቀፍና የስራ ማቆም አድማዎችን ማድረግ
6• የፓሊስ ሰራዊትና የመከላከያ ሰራዊት ከህዝብ ጎን በመቆም ለውጡን ማፋጠን
7• አርሶ አደሩ በስርዓቱ የሚደርሱበትን ግፎች በመኮነን ህዝባዊ አመፁን መቀላቀል
8• በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት የምትገኙ ተማሪዎች ለውጡን በእየቦታው ማቀጣጠል
9• ሁሉም ሰው በቤተሰብ ደረጃ መነጋገር መደራጀትና ለህዝባዊ አብዮቱ መፋጠን አጋር መሆን
10• በማዎቅም ይሁን ባለማዎቅ በዚህ እኩይ ቡድን ተጠልፋችሁ ስልጣን ላይ ያላችሁ ግለሰቦች በግልፅ ከህዝብ ጎን በመቆም አጋርነታችሁን ማሳየት።
2008 ዓ• ም በሁለንተናዊ መስክ ነፃነታችንን የምንቀዳጅበት አመት ይሆናል!!! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!! ውድቀት ለፋሽስቱ ወያኔ ቡድን!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር። በነፃነት ለሃበሻ መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ• ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ