ደመራ በታሪክችንና በባህላችን አንጻር – ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
ዛሬ ዛሬ በስመ “ቲዎሎጅ ምሩቃን” ከካድሬ ማሰልጠኛ ባልተለየ ሁኔታ እየሰለጠኑ ወደተለያየ ቦታዎች የሚበተኑት የዘመኑ “መምህራን” የወያኔን አገዛዝ ህዝቡ አምኖ እንዲቀበል ሐይማኖታዊ ሽፋንና የማሳመኛ ፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራት ምእመናንን በማፍዘዝና በማዘናጋት ላይ ይገኛሉ።የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ለዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ ስታስተላለፍ የነበረውን ትምህርት ከባሕሩ በጭልፋ እንኳ ሳይቀዱ አውደ ምህረት ላይ በድፍረት እየወጡ የምዕመናንን ህሊና በማደንዘዝ ላይ ስለሚገኙት “መምህር” በመባል ስለሚጠሩት የህወሃት ካድሬዎች ጠለቅ ያለ ጥናትና ማጋለጥ ማድረግ አስፈላጊ ነው። እነደዚህ ዓይነቶችን አጭበርባሪዎች የግምባር ስጋ በመሆን በማጋለጥ ላይ ከሚገኙት እውነተኛ አባቶች መካካል አንዱ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ናቸው። ከዘመናችን ታላላቅ ሊቃወንተ ቤተክርስቲያን መካካል አንጋፋ የሆኑት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በተለያዩ ርዕሶች ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአሁን ጊዜ የገጠሟትን ፈተናዎችንና እንቅፋቶች በዝርዝር በመተንተን መፍትሄውንም በማመላከት በርካታ መጣጥፎችን ለንባብ አብቅተዋል። አሁንም አንገብጋቢ የሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮችንን አብራርተው መፍትሄ የጠቆሙበትን “”ደመራ” በሚል ርዕስ ያዘጋጁትን መጣጥፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ደመራ