የዲላ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞች በዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት ላይ ኣመፅ ኣስነሱ። ዝርዝር ደብዳቤውን ይዘናል::

የዲላ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞች በፕሬዝዳንታቸው “ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ” ላይ ዓመፅ በማስነሳት ወደ ትምህርት ምኒስቴር ጥያቄያቸው ልከዋል።

ፕሬዝዳንቱ “ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ” ላይ 16 ክሶች ቀርቦላቸዋል።
ከክሰቹ መሃል

፩) ከ229 በላይ ሰራተኞች ከህግና ድንብ ውጪ በራሳቸው ስልጣን እንዲቀጠሩ ኣድርገዋል፣

፪)ሰራተኞች ዩኒቨርስቲው ለቀው እንዲሰደዱ እያደረጉ ነው።

፫) ለኢስትራክተሮችና ሰራተኞች የሚደበድብ ሃይል ኣደራጅተው ኣስደብድበዋል

፬ )በ ስልጣን ያለ ኣግባብ መጠቀም

፭) በኪራይ ሰብሳቢነት

፮) በሃብት ኣባካኝነት

፯) በጠባብነት

፰) “እኔ በሂወት እያለው የኣማርኛና ታሪክ ትምህርት ክፍል በዩኒቨርስቲው ኣላስከፍትም” የማለት ወዘት ያካተቱ 16 ጥያቄዎች ለትምህርት ምኒስቴር ምኒስትር ለሆኑት ኣቶ ሺፈረኣው ሽጉጤ ኣቅርበዋል።

ይህ የሰራተኞች ዓመፅ በታማኝ የዩኒቨርስቲ ሹሞኞች ላይ ኣዲስ ጅምር ነው።
በኣክሱም ዩኒቨርስቲም ፕሬዝዳንቱና ምክትሉ በተመሳሳይ ምክንያት ከቦታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል።

9 Comments on “የዲላ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞች በዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት ላይ ኣመፅ ኣስነሱ። ዝርዝር ደብዳቤውን ይዘናል::”

  1. እንካን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ

  2. ይህ ያሚያመለክተው ያለ በቂ እውቀት እኛ እናውቅላችሀለን ፈሉጥ

    ከጠ.ሚኒሥትር እሥከ ቀበሌ እንደሠርዲን ተሠንገው ወቅታቸው ሢደርሥ

    መሽተታቸው እየታየ ነው ሌላው በየዩኒቨርሥቲው ያለው ዝርፍያና ጎጠኝነት

    ይቁም ተማሪዎች በግዳጅ የሥርአቱ ያለፍላጎት ግብአት መሆን የለባቸውም

    ለጋ አይምሮዋቸው ሥብሠባ እያላችሁ አታደንዝዙብን የነገይቱን ኢትዬጵያ

    እንጂ ወያኔን አይረከቡም።

    የተፍታቱት እጆች ለዝርፊያ ሣይሆን ለለውጥ እናውለው

  3. I was one of former worker who fought against him but at the end I left country. He is stupid, narrow minded,corrupted and dictator. Shame on the system that promote him.

  4. ትልቅ ዉሸት ይህ ሆን ተብሎ የበሔሩን ሰዎች ወይም አዋቂዎች እንድሁም የበሔሩን አንገት ለማስደፋት የተደረገ ሴራ ነዉ፡፡ ዛሬም ቢሆን እኛ የበሔሩ ልጆች ያላማከለ ማንኛውም ወሬ የማንሰማ መሆኑን አዉቃችሁ ተስፋ ቁረጡ፡፡ እን/ዶ/ሪ ስለሺ ወደ ዩኒቨርስቲ ላይመለስ ይችላል ግን ለጌዴኦ ሺህ ስለሺዎችን ፈጥሯል ፡፡ እናዉቃለን ለጌዴኦ ጥሩ አመለካከት የለላቸዉ የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች እንዳላችዉ፡፡እዉነት ብንናገር ለምን የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ትላላችሁ ዉሸታሞች፡፡፡፡፡፡፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*