የግንቦት ሰባት ቃል አቀባይ ዶ/ር ታደሰ ብሩ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የTPDM መሪ መክዳት ቀሪዉን ከፍተኛ ኃይል ያጠናክራል እንጂ አያዳክምም አሉ

ትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ «ደሚህት»ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ከተዋጊዎቻቸዉ ጋር ከጥቂት ቀናት በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋአል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣዉ መግለጫ ፣የኢትዮጵያ መንግስት የደሕንነት አካላት ከድተዉ ከገቡት ከደሚህት መሪ ጋር ዓመት ከዘለቀ ምስጢራዊ ድርድር በኋላ ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ መደረጉን መግለፁ ይታወቃል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አዳማ ናቸው የተባሉትን የ(ደሚህት)ን መሪ አቶ ሞላ አስገዶምን ለማግኘት አዳማ ሄዶ ሊያገኛቸው አለመቻሉን ገልፆልናል።
በሌላ በኩል «የአርበኞች ግንቦት ሰባት» አመራር አባልና የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዶክተር ታደሰ ብሩ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራስያዊ ንቅናቄ በምህፃሩ «ደሚህት» መሪና ጥቂት አባላቱ መክዳት ቀሪዉን ከፍተኛ ኃይል ያጠናክራል እንጂ አያዳክምም አሉ። ዶክተር ታደሰ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የደህንት መሪ ኢትዮጵያ ይዘው ገቡ የሚባለው ተዋጊ ቁጥር ቡድኑ ካለው ሠራዊት ቁጥር ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነው ብለዋል።
ትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ ወቅታዊ ሁኔታ→ listen
የደሚህት መሪን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር የሰጡት አስተያየት→ listen