የሰማያዊ አመራር አባላት የፍርድ ቤት ችሎት

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ምድብ ችሎት በብርሃኑ ተክለ ያሬድ መዝገብ በተከሰሱ አራት የሰማያዊ አመራር አባላት ላይ ብይን ለመስጠት ዛሬ ቢሰየምም ለውሳኔው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ኢትዮጵያ የሰማያዊ አመራር አባላት የፍርድ ቤት ችሎት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ምድብ ችሎት በብርሃኑ ተክለ ያሬድ መዝገብ በተከሰሱ አራት የሰማያዊ አመራር አባላት ላይ ብይን ለመስጠት ዛሬ ቢሰየምም ለውሳኔው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ድንበር አቋርጠው ወደ ግንቦት ሰባት ሊቀላቀሉ ሲሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው የተገለፀው እነዚሁ ተከሳሾች ዛሬ ያቀረቡትን አቤቱታም አዳምጧል ። ተከሳሾቹ እነ ብርሃኑ በማረሚያ ቤት እርስ በእርሳችን እንዳንገናኝ እና ህክምና እንዳናገኝ ተከልክለናል ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል ።ጉዳዩን ያዳመጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ምድብ ችሎት ፤ይህ አስተዳደራዊ ችግር እንደሆነ በመጥቀስ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች እንዲያስተካክሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል። listen