የግንቦት 7 ስትራቴጂ፤ «ጭብጥ ቆሎ ይዘህ ወደ አሻሮ ተጠጋ»

Berhanu Nega vs Mola Asgedom

ግንቦቶቹ የደምህት አመራርና ወታደሮች ከድተው ለወያኔ እጅ መስጠታቸውን የኤርትራው ትግል እየተጠናከረ ስለሆነ ነው እያሉ ይቀልዱብናል። መቸም የጨነቀው ብዙ ሊል ይችላል ግን ግንቦቶቹ አንድ ነገር እባካችሁ ተረዱ፤ መጀመሪያ የራሳችሁን ግንቦት 7 የሚባለውን ቤታችሁን አጠናክሩ። ለራሳችሁ ጥንካሬና በእግራችሁ ለመቆም ስሩ። ሊቀመንበራችሁም አስመራ ግብቶ ግንቦትን የማጠናከርና ወደ ስራ ማስገባት ሳይሆን የተደራጁ ሌሎች ሃይሎችን ማፍረስ ላይ ነው እየደከመ ያለው። መጀመሪያ የራስን ቤት አጠናክሮ ሃይል ፈጥሮ ነው ሌሎች ጋ ተፅኖ መፍጠርም ማሳመንም የሚቻለው እንጅ የሻቢያን የማስገደድ አቅም ተጠቅማችሁ ዛሬ ውህደት ጥምረት ብትሉ ጊዜያዊ ተስፋ ከመስጠት ያለፈ ነገ ግን ውድቀት ነው። “ጭብጥ ቆሎ ይዘህ ወደ አሻሮ ተጠጋ” የሚባለው ፈሊጥ ትግል ላይ አይሰራም።

በደሚት በኩል ያጋጠመውን ሁኔታ ሁሉም በትምህርትነት መጠቀም ቢቻል ብዙ መማር በተቻለ (መማር የማይችሉትን ሳይጨምር)። ለማንኛውም ሞላ አስገዶም ወደ 700 የሚሆኑ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸውና ንብረታቸው ይዞ ለወያኔ እጅ ሰጥቷል። ወደ ወያኔ ሲሻገሩ ደንበር ላይ ከነበረው ከሻቢያ ወታደር ጋር ከባድ ውጊያ አድርገዋል። ከሁለቱም ወገን የሞተም የቆሰለም አለ። 50 የሚሆኑ ሞላን ተከትለው ሊሄዱ የነበሩ በጦርነቱ መሃል በሻቢያ ተይዘዋል። በተፈጠረው ሁኔታ ኤርትራ በቀሩት የደሚት አባላትና ሲከዱ በተያዙት ዘንድ ብዙ መተረማመስና መጥፎ ሁኔታወች እንደሚኖሩ የታወቀ ነው። ብዙ ኢትዮጵያኖች ሊጎዱ እንደሚችሉ ማሰብ አይከብድም።

እኔ እንደሚገባኝ የነ ሞላ ክዳት ከጥምረቱ ጋር የተያያዘ ነው መባሉ የሚረባ ወሬ አይደለም። ከሁለት መሰረታዊ ጉዳይ የሚነሳ ይመስለኛል። አንደኛው ነገር በሻቢያ በኩል ያለው ሁኔታ ተስፋ ሰጭና የምር አለመሆኑን በረጅም ጊዜ የተረዱት ከመሆን የተነሳ ሊሆን ይችላል። ሌላው ነገር እነ ሞላ ከወያኔ ጋር ባላቸው የዘር ግንድ ግንኙነት የተነሳ ለረጅም ጊዜ ትስስር አድርገው ቆይተው አሁን ለመክዳት የተመረጠ ጊዜ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት መውሰድ ይቻላል። ለሁሉም ወያኔን የማስወገዱ ስራ ገና ብዙ ነገር ይጠይቃል። በጠራ አስተሳሰብና በጽናት በሚረጋገጥ የተግባራዊ እንቅስቃሴ እንጅ በንግግር የትም አይደረሰም። መካሪ የሌለው ንጉስ አንድ አመት አይነግስ እንደሚባለው ግንቦቴወች ከባዕዳን ሃይሎች ይልቅ ከኢትዮጵያኖች ምክር ውሰዱ።

17 Comments on “የግንቦት 7 ስትራቴጂ፤ «ጭብጥ ቆሎ ይዘህ ወደ አሻሮ ተጠጋ»”

  1. ጠቅልሎ ከመሄድ ውስጥ ሆነው ወያኔን ብዙ ማገልገልና አርበኞች ግንቦት ሰባትን ማሽመድመድ ለወያኔ ብዙ ይጠቅም ነብር።ለምን ጠቅሎ ምውጣት ተመረጠ? Any ways my fear and worry for the rest of አርበኞች ግንቦት ሰባት is that since this guy has defected with the master key to the entire base and logistics they will have to change the keys to all the doors,which means a complete restructuring reshuffling of the entire system. This kind of defection for sure is not a result of immediate reaction to the ጥምረት it is obviously a calculated action which might have been planned for a long time.I find it hard to believe such mass defection.

  2. ግንቦት ሰባቶች በጉራጌ ሕብረተሰብ አንድ የተለመደ አባባል አለ ሰውን ሰው የሚያሰኜው ገንዘብ ነው ይላሉ ለዚህም ጠንክረው ይሰራሉ ዶክተር ብርሀሃኑን በምሣሌ መውሰድ የሚቻል ይመስለኛል/የትግሉ ጉዳይ የተሣፈሩበት ባቡር ወደጠገዴ ነው የሚያደርሰው በሌላ ባቡር ቢሣፈሩ ይመረጣል Mr Bunga thanks

  3. በማንኛውም የፖለቲካ ርዬተ አለም ልዩነት መከፉፈል አለ እንደ ወርቅ ተፈትኖ የሚወጣ የነፃነት ሀይል ወያኔ አሸባሪ ብሎ ይፈርጀዋል ግን አሏማቸውን በቅርቡ እውን ያረጋሉ።

  4. Ahun gena Beteglu emnet aderebegne kemehal Yale nekersa endihe new meleyet yalebet yetemare sew bezede new miateraw I really trust Dr Berhanu he is doing his job Ato mola he don’t even know how to express him self let alone to lead so am sure things will get stronger and stronger

  5. ለህወሓት “ከፋፍለህ ግዛ” ፓሊሲ መመቸት የለብንም። በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጾታ፣ በእድሜም ሆነ በቋንቋ ሳንከፋፈል የጋራ ትኩረታችንን የጋራ ቤታችን የሆነችውን ኢትዮጵያን ማዳን ላይ እናድርግ።

    ድል ለG7

  6. ይዘውት የመጡት መሣሪያ ወያኔ ድንበር ላይ ያቀበላቸው ለመሆኑ የምሥል መረጃ ተይዟል እንዲሁም ሣተላይት ሥልክን ጨምሮ በርካታ ወያኔ ለሥለላ ግብአት የዋሉ በG7 በቁጥጥር ሥር ይይገኛል።

  7. እናንተ ወገኖቼ እስከመቼ ድረስ ነው እንደተታለልን የምንኖረው?

    የዚህ ከዳ የተባለው ሰው ጉዳይን ረጋ ብለን ብንመረምረው ሐቁን እናውቀው ነበር። ነገር ግን ፈላስፋና ሁሉን አዋቂ ነው ተብለን መጠራት ስለምንፈልግ አንዱ ሳይቀድመኝ ቶሎ ልቅደመው በሚል ፈሊጥ የመጣልንን እንጽፋለን(እንናገራለን)።
    እንረጋጋ ጎበዝ፦ ለመናገር ብቻ ከሆነ ከበቂ በላይ ጊዜ አለን ለመስሪያ ነው እንጂ ያጣነው(የጠፋብን)። ቢያንስ እንኳን ጓደኞቻቸው (ግንቦት ሰባቶች) የሚሉትን እስኪ እንስማ።
    ቀድሞ ነገር ስንት ወንድሞችና እህቶች፣ በሻዕቢያ በኩል የሚደረግ ዕርዳታ እውነተኛውን ነጻነት ስለማያጎናጽፍ፥ ሌላ አማራጭ ያስፈልጋል ብለው ቢናገሩ ሰሚ ታጥቶ ነው እዚያ ድረስ የተሄደውና፤ አሁንም አልመሸም ቢታሰብበት መልካም ነው።
    እኔ እንደሚመስለኝ ልክ ሰላማዊ ትግል ተደርጎ እንዳለቀ፣ የሰላማዊ ትግል አራማጆችን ወያኔ እያሳደደ እስር ቤት እንዳጎረ፤ ሌሎችም ፈርተን ሸሸን ብለው ከኣገር በመውጣት የሰላማዊ ትግሉ አልቆለታል እንግዲህ የቀረው በመሳርያ መዋጋትና ማሸነፍ ነው የሚል አማራጭ ቀርቦልናል። ታዲያ የሰላማዊ ትግል አካሂደን ካሁን በኋላ አልቆለታል ያሉን ሰዎች ምን ያህል በሰላማዊ የትግል መስኩ እንደተሄደበት ሁላችንም ስለምናውቅ፤ በመሳሪያ ነው እንግዲህ ብለው የተነሱትንም በዚያው መነጽር እንመልከታቸውና፤ ጦር ሜዳ ውስጥ አስገብተውን፣ የተልፈሰፈሰ ዉጊያ ካደረጉና የህይወትና የስነ ልቦና ኪሳራ ካደረሱብን በኋላ፣ ወያኔ በሁሉም መስክ የማይደፈር ገናና መለኮታዊ ኃይል አድርገው ያቀርቡልንና እስከዘላለሙ የርሱ ተገዥና ባሪያ አድርገውን ይቀመጣሉ ማለት ነው።
    አሁን እነዚህን፣ ሰዎች በሏቸው ቡድኖች ለማን እያገለገሉ ያሉ መስሎ ይሰማችኋል?
    መርምሩ!!
    እግዚአብሄር አገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!!

  8. Molla ASGEDOM he is fun even he does not speech well when he says one word he tern onto his pepper so many times I do not like to say any bad words about you but please do not judge professor Brehanu Nega even though you can say he is stubd professor brehanu is professor brehanu he is famous professor in only in Ethiopia he is allover the world famous professor.

  9. Bizu bemawurat bihonma dr Birhanum balasfelege neber, TAMANG,ABEBE BELAWU/Gelawu/….alu aydel ?
    Mola balemawurat min anesewu?
    ETHIOPIAN Melewox yemichalehu besira enji amarigna akelaxifo bemawurat aydelem.
    3000 amet bemawurat asalifenal ahun yalefewun titen gizewu wodet endehone eyayen wodefit enguwaz . Bemignotna bewore hagern melewox bichalima neber gin alseram aytenal .yih hulu tirmis yezane yeneberew woxet mehonun mezengat yelebinm.Ahunm amarigna bedenb balemenageru mesedeb yelebetm( Mola) . Bizu kemilefelifu esu yeserawu tarik hono yemimezegebal . Shabiya leEthiopia kenna endemayasib siyawuk bichahun sayhon beand ken wusx 700 Ethiopian yizo wotuwal.
    Hulum sewu yerasun kuwunka akelaxifo menager yichilal .Ethiopia yebizu biher bihereseboch hager mehonuwan mawok yetesanachew bizuwoch alu, . CHINA , JAPAN,GERMANY & AMERICAN … tekonologiwun beyerasachew kuwanka ekul yixekemalu min chiger ale amarigna bayawora ?
    Betigregna mels mesxet yichilal kasfelege gin bizuwoch yemaysemu silalu new. Esu rasun yegeberij negn eyale lela min yifelegal ?

  10. Mola is inferior to Ginbot 7 and the unity that is put together recently. As Mola witnessed himself, “I Mola Asgedom is the son of a farmer who is uneducated, been the second highest power full leader of the force next to a professor is a reward to me.” At this point he realized that his future as a leader is under tremendous treat, because of the flux of educated leaders from around the world. Mola had been a leader for fourteen years as he mentioned, and he will not allow to relinquish power. He prefer to dismantle the force and surrender to TPLF. After all he is who he was.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*