የፖለቲካ ፓርቲዎችና አዲሱ ዓመት

በአዲሱ ዓመት ሰላማዊ ትግላቸዉን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ አድርገዉ እንደሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ። የኢትዮጵያ ፊደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ «መድረክ» በአጭሩ ፤ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ « ኢራፓ» ሰማያዊ ፓርቲ፤ አንድነትና የመላዉ የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት «መኢአድ» አመራር አባላት ለዶቼ ቬለ በአዲሱ ዓመት ሰላማዊዉን የሕዝብ ንቅናቄ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉበት ተናግረዋል። ያለፈዉ ቁርሾ በብሔራዊ ዕርቅና መግባባት እንዲፈታ የትግል አቅጣጫዬ አድርጌ እንቀሳቀሳለሁ ሲል የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ «ኢራፓ » ገልፆአል። የሰማያዊ ፓርቲ ለቀመንበር በበኩላቸዉ ፓርቲያቸዉ በቅርቡ ጉባኤ ማካሄዱንና የካቢኔ አባላት የመሰየም ሂደት በቅርቡ እንደሚካሄድ ገልፀዋል። ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ → LISTEN

1 Comment on “የፖለቲካ ፓርቲዎችና አዲሱ ዓመት”

  1. any one of political party can’t rebail with weyane jointly weyane need’s separated party cus if the party is separated the vote of the people is separated why not all party joined & fight with weyane

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*