“ዘመቻ አባ መላኩ” ከወያኔው ተላላኪ ከንጉሴ ወልደማርያም እርዳታ ጠየቀ

maxresdefault

በዋንግተን ዲሲ ከተማ አካባቢ በወያኔ የሚተላለፈው “የሀገር ፍቅር” በመባል የሚጠራው የማደናቆሪያና የማዘናጊያ ሬዲዮ ዝግጅት አቅራቢ የሆነው ንጉሴ ወልደማርያም ከአሳዳሪው ከወያኔ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአባ መላኩ ፊታውራሪነት በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ላይ በተከፈተው ዘመቻ ላይ እሱም ተሳታፊነቱን በዛሬው ዕለት አዉጇል። ዉሻ በቀደደው ጅብ ይገባል እንደሚባለው አዲሱ አበበ በከፈተው ቤተክርስቲያንን ለወያኔ የመሸጥ ዓላማ ንጉሴ ወልደማሪያምም ለካህናት ተቆርቋሪ በመምሰል እስከቅርብ ጊዜ ድረስ “ጥቁር ራስ” እያለ ሲያዋርዳቸውና ስያብጠለጥላቸው የነበሩትን ካህናት አሁን አለኝታቸውና ዋስ ጠበቃቸው  ሆኖ ቀርቧል። የር/አ/ደ/ሰ/ቅ/ ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የባለአደራዎች ቦርድ በሥነ ምግባር ጉድለትና የደብሩን መተዳደሪያ ደንብ በመጣሳቸው ምክንያት ከአገልግሎት ያስወገዳቸውን ካህናት እንደተበዳይ አድርጎ አጣሞ በማቅረብ ወያኔያዊ ተልዕኮውን ለመወጣት ደፋ ቀና ማለቱን ዛሬ ባቀረበው የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ በይፋ አወጇል። ወያኔ በተላላኪዎቹና በተስፈኞቹ አማካይነት ይህንን የመሰለ በገሃድ ቤተክርስቲያንን የመንጠቅ እኩይ ተግባርን አይናቸው እያየ አንዳላየ፣ ጆሯቸው እየሰማ እንዳልሰማ በመቁጠርና በቸልተኝነት እንዲሁም በደብሩ ውስጥ የደረሰ ተራ አለመግባባትና ውዝግብ አድርገው የሚመለከቱ የዋሆች በመሉ ከልቦናቸው ሆነው ቤተክርስቲያናቸውን መርጠው እንዲያስተዳድሯቸው ኃላፊነት ከሰጧቸው ከባለ አደራዎች ቦርድ ጎን አብረው መቆም ይጠበቅባቸዋል። ይህንኑ አስመልክቶ በሬዲዮ የተላለፈውን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ። በሀገር ፍቅር ሬድዮ አቶ ንጉሴ ስለማርያም ቤተክርስቲያን አመጽ እቅድ ሲያበረታታ ዋለ ።