የማህበራዊ ቦይኮት ዘመቻችንን የመረጃ መሰብሰቢያ ፎርሙን በመሙላት እንጀምራለን! የቦይኮቱ ዓይነት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል!
የማህበራዊ ቦይኮት ዘመቻችንን የመረጃ መሰብሰቢያ ፎርሙን በመሙላት እንጀምራለን!
የቦይኮቱ ዓይነት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል! ረቡእ ጳጉሜ 4/2007
ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች የመንግስትን ወሰን የለሽ በእምነታችን ጣልቃ መግባትን ተከትሎ እያካሄድነው ባለነው የመብት ማስከበር ሰላማዊ ትግል አንጸባራቂ ድሎች እንደተገኙ ሁሉ በተቃራኒው ደግሞ በተደጋጋሚ ከሌሎች በሚደርሱብን በደሎችም ምዕራፉ የታጨቀ ነው፡፡ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ካሉ አካላት ሁለቱ እያደረሱት ያለው አደጋ እጅግ ከባድ ነው፡፡ አንደኛው በጸጥታና በካድሬነት መስክ ያለው የመንግስት ቋሚ ተቀጣሪና ደሞዝተኛ ሲሆን ዋናውን የመንግስትን የጥፋት ፖሊሲ እያስፈፀመ ቆይቷል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በመንግስታዊው ሹመት መጅሊስን የተቆናጠጡ፣ አልያም ከመንግስት የተለያየ ጥቅማ ጥቅም በመሻት በመንግስት ጉያ ስር የተሸሸጉ፣ ኢማሞቻችንና ሙአዚኖችን በመተካት በመስጂዶቻችን በመንግስት የተሾሙ ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት በትብብር በቅንጅት አንዱ ለሌላው ረዳት ሆነው ሽፋን እየተሰጣጡና መረጃ እየተለዋወጡ የበደል ፖሊሲውን በማስፈፀም ላይ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ አካላት በተለያየ መልኩ ሙስሊሙን ሲያጠቁና ለማጥቃት ሲያሴሩ ነበር፡፡ የሃስት ክስ በመፍጠርና መስካሪዎችን በመመልመል፣ በችሎት ፊት ቆመው በአላህ ስም እየማሉ በሐሰት በመመስከር፣ ታሳሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን በማሰቃየት፣ ሙስሊሞችን በማስፈራራትና በማሸማቀቅ፣ መስጂድ በማሳሸግና መድረሳ በማዘጋት ከህዝብ ወጥተው ህዝቡን ሲያስጠቁ ኖረዋል፤ በሙስሊሙ ላይም ከፍተኛ ችግር አድርሰዋል፤ እያደረሱም ይገኛሉ፡፡ ይህን ስንል በትግሉ አካሄድ ዙሪያ የተለየ ሃሳብ ያራመዱ ሙስሊሞችን ማለታችን አይደለም፡፡ የትኛውም ሙስሊም የፈለገውን አመለካከት እና እምነት የማራመድ ነጻነት አለው፡፡ ከሃሳብ ልዩነት በማለፍ ግን ሙስሊሙን በማሳሰር፣ በማስደብደብ፣ መድረሳዎቹን በመቀማት እና ከመንግስት ጋር ተባብሮ ሙስሊሙን በማስጠቃት ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች የዚህ ማህበራዊ ቦይኮት ዒላማዎች ናቸው፡፡
ማህበራዊ ቦይኮት (ሙቃጠዓ) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በውስን ሁኔታ ውስጥ ተግባራዊ ያደረጉት ኢስላማዊ መሰረት ያለው ተግባር ሲሆን በሰላማዊ ትግላችን ውስጥ ደግሞ የበደሉ ጠንሳሽና አስፈፃሚ የሆኑ ግለሰቦችን በመጀመሪያ ደረጃ ማጋለጥ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ተቀዳሚ ተግባራችን ይሆናል፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዲታቀቡና እንዲመከሩ በመርሀ ግብር ደረጃ ተይዞ ከዚህ እኩይ ተግባራቸው ይታቀቡ ዘንድ ቤተሰባዊ እና ማህበራዊ ትስስሮችን ተጠቅመን እንዲመከሩና እንዲገሰፁ አድርገን ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ግን ንፁሃን አንገታቸውን ደፍተው ሳሉ እነሱ ግን አምባገነናዊ ኃይልን ተማምነው ቀና ብለው የሚሄዱበትን አግባብ ማስቆሙ ግዴታ ሆኗል፡፡ ምክርና ተግሳፅ አልመልሳቸው በማለቱና አሁንም የመንግስትን ዘመቻ በማስፈጸም ላይ በመሆናቸው ባሉን ማህበራዊ ህይወቶች ውስጥ ለእነሱ ሊሰጥ የሚገባውን ስም እና ቦታ በመወሰን ሊያፍሩ እና ሊሸማቀቁ የሚገባቸው የታሪክ ጥቁር ገፅታዎች መሆናቸውን በተግባር የምናሳይበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
እስከዛሬ ድረስ ባሉት ወቅቶች በተለያዩ አካባቢ የሚገኙ የጥፋት ተዋንያንና ተባባሪዎችን መረጃ የመሰብሰብ ስራ ውስጥ ለውስጥ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ የቦይኮቱ አይነት በቅርብ ጊዜ የሚገለፅ ሲሆን ስራው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን በሁሉም የሃገራችን ክፍሎች በዚህ የጥፋት ተግባር የተሰለፉ ግለሰቦችን ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ (ማስፈንጠሪያ) በመጫንና ፎርሙን በመሙላት በዳዮቻችን እና የእነርሱ ቀኝ እጅ የሆኑትን አካላትን እናጋልጣለን፡፡ በተያያዘው ፎርም ላይ ስማቸውን፣ ፎቷቸውን፣ መኖሪያ አድራሻና የስራ ቦታቸውን፣ የሰሩትንና እየሰሩት ያሉትን የበደል አይነትና ድርሻ በመሙላት እንላክ፡፡ የበደሉ ተዋንያንና ተባባሪዎች ከህዝብ ውስጥ ሆነው በደል በህዝብ ላይ እያስፈፀሙ ሳይሸማቀቁና ሳያፍሩ መኖር የለባቸውም – ኢንሻአላህ!
የሚሞላው ፎርም ሊንክ የሚከተለው ነው፡-
http://goo.gl/OSCj4q
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
