ህወሓት ለሀገራቸው ያገባናል ለሚሉ ሴቶች፣ አድርባይ ላልሆኑ ሴቶች፣ እንደ ጣይቱ ሞትን ለማይፈሩ ሴቶች ፀር ነው፡፡

ህወሓት ለሀገራቸው ያገባናል ለሚሉ ሴቶች፣ አድርባይ ላልሆኑ ሴቶች፣ እንደ ጣይቱ ሞትን ለማይፈሩ ሴቶች ፀር ነው፡፡


Empower women, don’t imprison them! #FreeThe20.
ህወሓት/ኢህአዴግ የሴቶች፣ ራሳቸውን ያወቁ ሴቶች፣ ለሀገራቸው ያገባናል ለሚሉ ሴቶች፣ አድርባይ ላልሆኑ ሴቶች፣ እንደ ጣይቱ ሞትን ለማይፈሩ ሴቶች ፀር ነው፡፡ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፡፡ ከቻይና በስተቀር፡፡

ይኸ ስርዓት አንድ ሰሞን ‹‹አፈርማቲቭ አክሽን›› ሆኖ ነበር ቋንቋው ሁሉ፡፡ ሴቶችን ጨምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ‹‹ወደኋላ የቀሩ››፣ የተጎዱ የሚላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ማብቃት ነው ‹‹አፈርማቲቭ አክሽን›› የሚሉት ፀረ ታጋይ ሴቶቹ የስርዓቱ ሰዎች፡፡
ይሁንና ይኸው ስርዓት በሀገሩ ጉዳይ ወደኋላ ከሚለውና ሀገሩን ለጥቅም ከሚሸጠው ወንድ ቀድመው የተገኙትን ሴቶች በእስርና በማሰቃየት ከቻይና ጋር የአንደኛ ደረጃነትን ይዟል፡፡ ተከፍሎትና ተደራጅቶ የደጋፍ ሰልፍ የሚወጡ እንጅ እሱ ሀገር ሲያጠፋ ‹‹ለምን?›› የሚሉትን ሴቶች እስር ቤት ውስጥ በማጎር የአምባገነኖች ቁንጮ ሆኗል፡፡

በአንድ ወቅት ክፍል ውስጥ አስተማሪው ‹‹አፈርማቲቭ አክሽን›› ምን ማለት እንደሆነ ጠይቆን አንዱ ‹‹በእኛ ሀገር አፈርማቲቭ አክሽን ሳይሆን አፈር የማብላት አክሽን ነው ያለው›› ብሎ የራሱን ትርጉም ሰጥቶት ነበር፡፡ ከዛም በአብዛኛው የክፍላችን የአፈርማቲቭ አክሺን ትርጉም አፈርደሜ የማብላት አክሽን ሆኖ ነበር፡፡ ያው ነው፡፡ በተለይ የተለየ ሀሳብ ላለውና ‹‹ራሴ እቀድማለሁ፡፡ የአንተ ድግፋ አያስፈልገኝም›› ለሚል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ የሴቶች፣ ራሳቸውን ያወቁ ሴቶች፣ ለሀገራቸው ያገባናል ለሚሉ ሴቶች፣ አድርባይ ላልሆኑ ሴቶች፣ እንደ ጣይቱ ሞትን ለማይፈሩ ሴቶች ፀር ነው፡፡ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፡፡ ከቻይና በስተቀር፡፡

Empower women, don’t imprison them!
#FreeThe20.