በኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር መተማ ገላባት ውጥረት ነግሷል ፡፡

ኢትዮጵያ እና ሱዳንን በሚያዋስኑ የመተማ እና ገላባት ከተሞች የመተማ ነዋሪዎችን ቁጣ ተከትሎ ውጥረት መንገሱን የአከባቢው ነዋሪዎች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል ፡፡ነዋሪዎቹ እንዳስታወቁት ባለፈው ሳምንት የአስረአንድ ኢትዮጵያውያን መታረድ የፈጠረው ሕዝባዊ ቁጣ አከባቢውን ውጥረት ውስጥ በመከትቱ ድንበሩ የተዘጋ ሲሆን የከተሞቹ የንግድ እንቅስቃሴ ጭር ያለ ሲሆን ከሁለቱ አገራት የሚነሱ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እና የጭነት መኪኖች የኡመራ ከተማ እየተጠቀሙ እንደሆነ ምንጮቹ ገልፀዋል ፡፡

ባለፈው ሳምንት የወጡ መረጃዎች እንዳስታወቁት አስረ አንድ ኢትዮጵያውያን ስራ አለ በሚል ወደ ገላባት ከተማ ከገቡ በኃላ ታርደው ተገኝተዋል ፡፡ይህ አሰቃቂ ግድያ በመላው አለም የኢትዮጵያዊያንን ቁጣ ያስከተለ ሲሆን በመተማ ተቃውሞ በመቀስቀሱ ድንበሩ እስከመዘጋት ደርሷል ፡፡

ውጥረቱን ተከትሎ ወያኔ በአከባቢው ካሰፈረው ጦር በተጨማሪ ከመሐል አገር እና ከምእራብ እዝ ጦሩን ማጓጓዝ መጀመሩን የአይን እማኞች ተናግረዋል ፡፡ የሰሜን ኢትዮጵያ ክልል ላለፋት አመታቶች በሕዝብ ቁጣ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መሆኑ ይታወቃል ፡፡