የደህንነት ቢሮው ውዝግብ ሊቋጭ አልቻለም::መቀሌ ላይ የታገቱ የደህንነት አባላት ጉዳዩ እንዲያገረሽ አድርገውታል::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በሃሳብ መለየት ብቻ በተከታታይ ደብዛቸው የጠፋውን የሕወሓት አገዛዝ አባላትን በተመለከተ በኢሕአዴግ ድርጅቶች ካድሬዎች መካከል በደህንነት ቢሮው ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ውዝግባቸው ሊቋጭ እንዳልቻለ ለብአዴን በአመራርነት የሚያገለግሉ ለደህንነት ቢሮ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::ካለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ የፓርቲው አባላት/ካድሬዎች ደብዛቸው ስለሚጠፋ የፓርቲ አባላት ጉዳይ በተመለከተ ያቀረቡት ጥያቄ እንዲሁም ከባህር ዳር መጥተው ስብሰባ ላይ ስለተገደሉ የደህንነት አባላት ጉዳይ በተመለከተ ድርጅቱ መፍትሄ እንዲሰጥ የደህንነት ቢሮው ውዝግቡ እንዲቛጭ እንዲያደርግ የተጠቀ ቢሆንም በዚህ ሰሞን ለኢሕኣዴግ ስብሰባ መቀሌ ተጠርተው ከሄዹ በኋላ የታገቱ የደህንነት አባላት ጉዳይ ያሳሰባቸው የፓርቲው ሰዎች ጥያቄውን ዳግም እንዲያገረሽ ማድረጋቸው ታውቋል::
በኢሕኣዴግ ስብሰባ ተብለው ከተጠሩ በኋላ በርካታ የደህንነት አባላት መቀሌ ላይ ታግተው ከፍተኛ ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን የድርጅቱን መረጃዎች ለጠላት አሳልፋችሁ ትሰጣላችሁ በሚል እየተንገላቱ መሆኑን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::የደህንነት ቢሮው በብዛት የተሞላው በሕወሓት አባላት እና በአንድ ብሄር ሰዎች ቢሆንም በቂ መረጃ ባለማግኘት እና ከሕዝብ መሃል ሰርገው የሚገቡ የአንድ ብሄር የደህንነት አባላት በጥርጣሬ ስለሚታዩ እና ማንም ስለማያምናቸው የደህንነት ቢሮው በጠበንጃ ሃይል ስልጣኑን ለማስጠበቅ ብቻ መጓዙ እንዲሁም ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል የመለመላቸው የደህነት አባላት በርካቶቹ ከተራ መረጃ ውጪ ጠቃሚ የሆነ ነገር ባለማምጣታቸው በተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ በአስር ሺዎች ደሞወዝ የሚከፈላቸው መረጃ አቀባዮች መቀዝቀዝ ከዚህ ቀደም ደብዛቸው የጠፋውን አባላቱን ጨምሮ በጉዳዩ በመወጠሩ ከፍተኛ የሆነ አጣብቂኝ ውስጥ ቢሮው መግባቱ ታውቋል እንደ ምንጮቹ ገለጻ::
የደህንነት ቢሮው አሰልጥኖ ያሰማራቸው የአንድ ብሄር ሰዎች በከፍተኛ ጥርጣሬ መታየትን አስመልክቶ ያለውን እደምታ በተመለከተ ያናገርኩት አንድ የአረና ፓርቲ አባል የደህንነት ቢሮው ኤርትራውያንን አሰልጥኖ በማሰማራት በትግሪኛ ተናጋሪ ስም በትግራይ ሕዝብ ላይ ጥርስ እንዲነከስ ያደርጋል ይህ የወያኔ የከፋፋይነት ፖሊሲ ስለሆነ ሕዝቡ በጥንቃቄ እንዲመለከተው አሳስቧል::የደህንነት ቢሮው ምንጮች በግርድፉም ቢሆን በዚህ ይስማማሉ::በአዲስ አበባ ውስጥ የደህንነት አባላት ከኤርትራውያን እንደተመለመሉና አብዛኛው ምልምሎች በሳዋ እና ናቅፋ የወታደራዊ ደህንነት ስልጠና የወሰዱ እንደሚገኙበት ተጠቁሟል::#ምንሊክሳልሳዊ