በዲሲ ትላልቅ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ወያኔ አዲስ ዘመቻ ከፈተ

ሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2007 ዓ.ም.

ለዚህ ማስረጃ የሚሆኑ ሰሞኑን በዋሽንግተን ዲሲ እየታዩ የሚገኙት ሁለት አንጋፋ ቤተክርስቲያኖች ላይ የተከሰጠውን ዘገባዎች ይዘን ቀርበናል። በቅድሚያ ይህንን ሪፖርታዥ እንድናጠናቅር የተባበሩን ሁሉ በቅድሚያ እናመሰግናለን።

የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

በዋሽንግተን ዲሲ የምትገኘው የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እሁድ ነሐሴ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. (August 30, 2015) የተክለሃይማኖት ታቦት በሚወጣበት ዕለት ከፍ ያለ ግርግርና ረብሻ እንደነበር ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። የተክለሃይማኖትን በዓል ለማክበር ከየአድባራቱ የተሰበሰቡ ምእመናን ባሉበት የሰንበት ት/ቤት ወጣት መዘምራን አንድ መዝሙር ከዘመሩ በኋላ፣ ታቦት ከመውጣቱ በፊት መግለጫ አለንና እናነባለን የሚል ጥያቄ ሲያነሱ የደብሩ አስተዳዳሪ የሆኑት ሊቀ ማዕምራን ዶ/ር አማረ ካሳዬ የቤተክርስቲያኑን አሰራር የጣሰ ጥያቄ ስለነበር ማንበብ አትችሉም የሚል መልስ ሰጧቸው። ለምን ይህ እንደሆነ የጠየቅናቸው ግለሰቦች እንደሚሉት ሊቀ ማዕምራን ዶ/ር አማረ ትክክል ናቸው ምክንያቱም የታቦተ ሕጉ ሳይፈፀምና ፈቃድ ባልተጠየቀበት ሁኔታ ማንኛውንም ማታወቂያ ማንበብ በቤተክርስቲያን የማያስፈልግ ኹከት ያስከትላል የሚል ነው። ነገር ግን ከካህናቱ መካከል ዘማርያኑን ነገር ጎስጉሰው ሴራውን ያዘጋጁ ስለነበሩ፣ የቀሲስ አማረን ሃሳብ ውድቅ አድገው፣ ያንብቡ በማለታቸው መዘምራኑ መግለጫቸውን አንብበዋል።ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ አደገኛ ሁኔታ እንዳይፈጠር ለማድረግ ፖሊስ ተጠርቶ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ገብቶ የነበረ ቢሆንም ሊቀ ማዕምራን ቀሲስ አማረ የራሳችን ልጆች ናቸው መክረን እናስተካክላቸዋለን ብለው በማስረዳት ፖሊሶቹን ከቤተክርስቲያኑ ለቀው እንዲሄዱ ማድረጋቸውንና ሁኔታው በሰላም እንዲጠናቀቅ በሳል አመራር መስጠታቸውን አረጋግጠናል። በዚህም ድርጊታቸው ቀሲስ አማረ ለቤተክርስቲያንና ለምዕመናን ያላቸውን ተቆርቋሪነትና አለኝታነት አሳይተዋል።ሌሎች በዙሪያው የነበሩ ሰዎችን አነጋግረን የተረዳነው ለመበጥበጥ ሙከራ ሲደረግ ጉዳዩን ያቀዱና ወጣቶቹን ያሰማሩ ሰዎች ፈንጠር ብለው ተቀምጠው እየሳቁ ያዩ ነበር። ከነዚህም ውስጥ እነ ቄስ ተስፋዬ መቆያና ዶ/ር አክሊሉ ሐብቴ ይገኙበታል።

ሌሎች ያነጋገርናቸው ጠለቅ ያለቅ ግንዛቤና ተሞክሮ አላቸው የሚባሉ ሰዎች እንደሚሉት ወያኔ እንግሊዝ አገር እንዳደረገው ዋሽንግተን ዲሲ ላይም ለምድገም ይመስላል የሚሉም አሉ። እንዴት ነው ከለንደን ጋር የሚመሳሰለው ብለን ስንጠይቃቸው እንዲህ አሉን። ለንደን ደብረጽዮን የሆነው የሰባካ ጉባኤ አባለት ( 4 ካህናት፣ 1 ከሰንበት ት/ቤት እና 4 ከምዕመናን) የተውጣጡ ነበር። ከነዚህ ዉስጥ 4 የምእመናን ተወካዮች በጣም ስለተሰላቹና የወያኔ እቅዱ ስላገባቸው ጥለው ወጡ። በዚህን ወቅት 4 ካህናት፣ 1 ከሰንበት ት/ቤት አብላጫ ድምጽ ይዞ ቤተክርስቲያኗን ከሁለት ዓመታት በላይ ውዝግብ አስነስቶ አሁን ወደ መጨረሻው የሆነው ታማኝ የሆኑና የወያኔ ተንኮል የገባቸው ምዕመናን አዲስ ኮሚቴ በመመረጡ ነው። አባ ግርማ አሁን ለንደንን ለቀው ደብረዘየት አካባቢ ቤተ አስርተው ሊኖሩ ሄደዋልም የሚል ወሬም በማህበራዊ ድረ ገጾች ተነቧል።

ታዲያ እንዴት እነዚህ መዘምራን ሁሉም ጉዳዩን አምነውበት ነውን? ብለን የጠየቅናቸው ምንጮቻችን፣ ወጣቶቹ ይህን የተወሳሰበ ተንኮል ከጥቂቶቹ በስተቀር አያቁም። ነገር ግን ስርዓተ አልበኛነት ማሳየታቸው እጅግ የሚያሳፍር ጉዳይ ነው ይላሉ። ቀጥለውም ለእግዚአብሔር አግልግሎት የተሰጠውን የድምፅ ማጉሊያ አጋጣሚ በመጠቀም ላልተፈቀደላቸው አላማ በማዋል ኹከት ፈጣሪ መሆናቸው አሳዛኝ ጉዳይ ነው ብለዋል። በዲያስፖራ የሚከሰተውን የወያኔን የቤተክርስቲያን የማጥፋት ዘመቻ በቅርብ የሚከታተሉት እንደሚሉት ደግሞ በዋሽንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ አሜሪካ ግዛዛት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አባ ፋኑኤል (አባ መላኩ ጌታነህ) የዘመቻው ዋና አቀንቃኝና አተባባሪ እንደሆኑ ይናገራሉ።

አባ ፋኑኤል የወያኔን መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን በተሰጣቸው ትዛዝ መሰረት ህዝበ ክርስቲያኑን የሚከፋፈልበትን ዘዴ የሚረዷቸው የእግር ወታደሮች አሰባስበዋል። የሆኑት በየቦታው (ዳላስ፣ ለንደን፣ሚኖሶታ፣ ናሽቪል፣ ቦስተን፣ ወ.ዘ.ተ.) እንዳየነው ወጣት መዘምራን ቀደም ብለው ያዘጋጁት የአቋም መግለጫ ማንበብ አለብን ማለታቸው ነው። ታቦተ ሕጉ ሳይወጣ በአውደ ምህረት ላይ ቆመው ሁከት ለማስነሳት የሞከሩት ከጩኽትና ግርግር በኋላ ሊቀ ማዕምራን አማረ ፈቅደውላቸው አንብበዋል። ወጣቶቹ ከጠየቋቸው አንዳንድ ጥያቄዎች ውስጥ የቄስ ኃይሉ ከባለአደራ ቦርድ ለምን ተባረሩ፣ ይመለሱ የሚል ይገኝበታል። በመሰረቱ ቄስ ኃይሉ ከባለአደራ ቦርድ መወገዳቸውንና አለመወገዳቸውን ለማጣራት ባደረግነው ሙከራ፣ ቄስ ኃይሉ እንዳልተባረሩ ነው። ይህን ጉዳይ ቄስ ኃይሉ ምናልባት ከጀርባ ሆነው ወጣቶችን የሚገፉ እነ መምህር ተስፋዬ መቆያ ናቸው የሚል አስተያየት ይሰጣሉ ። ስል መምህር ተስፋዬ መቆያ ሌላ ዘገባ እናቀርባለን።

ወጣቶቹ ትርምስ በመፍጠር ቤተክርስቲያኗን በለንደን ደብረጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ችግር ለመፍጠር የታሰበ ይመሰላል የሚሉም አሉ። ባለፈው ሳምንት ስለ አቶ አዲሱ አበበ በዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጋር የገባውን ውጣውረድ ዘግበን ነበር። አቶ አዲሱ የቤተክርስቲያኑን ባለአደራ ቦርድ ለማሳጣትን ብዙ ዘመቻ የሚያደርገው አንዳድ ለሆዳቸው ያደሩ ደፍተራዎችን በመጠቀም ነው። የነዚህን ሆድ አደር ደፍተራዎች ዝርዝር ጉዳይ በሌላ ዘገባ እንመለስበታለን።

ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

በተመሳሳይ መልኩ በሜሪላንድ ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በመምህር ዘበነ ለማ አማካይነት ለረዥም ዓመታት ውስጥ ውስጡን ሲበስል የነበረው ቤተክርስቲያኑን በቀጥታ ወያኔ ቁጥጥር ሥር የማስገባት ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰው መረጃ ያመለክታል። በዚህም መሠረት ባለፈው አስራ አምስት ቀናት በፊት መምህር ዘበነ ለምዕመናን ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሠረት እያንዳንዱ የቤተክርስቲያኑ አባል በሚመደብለት ነፍስ አባት ካህን ስር አንዲመዘገብና ይህንን የሚቃወም ማንኛውም ካህን ለቆ መሄድ አንዲሚችል አስጠንቅቋል። እያንዳንዱ ምዕመን በራሱ ፍቃድና ውሳኔ የፈለገውን ካህን ከፈለገበት ደብር የመያዝ መብቱን የጣሰና ከተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህጋት ውጭ የሆነው የመምህር ዘበነ መመሪያ ብዙ የዲሲን አካባቢ የኦርቶዶስ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በማነጋር ላይ የሚገኝ ጉዳይ ሆኗል።

ከ30 ዓመታት በላይ በቤተክርሲያኑ አባል የሆኑ አንዳንድ ምዕመናን እንደሚናገሩት ከሆነ የመምህር ዘበነ ዕቅድ ቁጥራቸው ከ200 የማይበልጠውን የቤተክርስቲያኑን አባላት ከ10 እስከ 12 ቁጥር ባላቸው ካህናት ሥር በመመደብ፣ ምዕመናኑ በሚመደቡላችው ካህናት የሚተላለፉላቸውን መመሪያዎች መቀበልና በምዕመናን ስብሰባ ላይ ለውሳኔ የሚቀርቡ ሃሳቦችን ከነፍስ አባታቸው በተነገራቸው መሠረት ድምጽ እንዲሰጡ ለማስደረግ መሆኑና እንዲሁም ምዕመናኑ መንፈሳዊና ዕለታዊ ኑሮ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ ነው የሚሉት ይገኙበታል። ይህንንም በአገራችን ላይ በወያኔ አስገዳጅነት እያንዳንዱን ዜጋ “አንድ ለአምስት መጠርነፍ ከተባለው አሰራር ጋር የተያያዘ የእዝ ሰንሰለቱን ጠብቆ ሊካሄድ ዝግጅቱ መጠናቀቁን ተደርሶበታል። ከነዚህም በስውር እየተሰራባቸው ካለው አብይ ጉዳዮች አንዱ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በወያኔ የተሾሙትን አቡነ ፋኑኤል በደብረገነት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ተቀባይነትና እውቅና እንዲያገኙ ለማድረግና ቀጥሎም ቤተክርስቲያኑን በአቡነ ማቲያስ በሚመራው የኢትዮጵያው ሲኖዶስ ስር ለማስገባት ነው።

እስከ አሁን ድረስ ቤተክርስቲያኗ በውጭ ከሚገኘው ሲኖዶስም ሆነ ከአገር ቤቱ ሲኖዶስ ሳትወግን በራስ ገዝ (independent ገለልተኛነት) የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እምነትና ሥርዓቱን ብቻ እየተከተለች ከ30 ዓመታት በላይ የዘለቀች መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም በደረሰን መረጃ መሠረት መምህር ዘበነ ኢትዮጵያ እየተመላለሰ ለማስተማርም ሆነ ለግል ጉዳይ የሚያደርገውን ተደጋጋሚ ጉዞ ከአቡነ ፋኑኤል የመሸኛ ደብዳቤ ካልያዘ በስተቀር እንደማይፈቅድለት በማስጠንቀቂያ መልክ በተነገረው መሠረት ቤተክርስቲያኗን ወደ አገር ቤት ሲኖዶስ ለማስገባት ያቀደው ዘዴ አንደሆነ ይናገራሉ። የቤተክርስቲያኗን ታሪክና ከአቡነ ማትያስ ጋር የነበረውን ግንኙነት ዘርዝረው እንዲያስረዱን የጠየቅናቸው መስራች ምእመናን የሚከተለውን ነግረውናል።

የደብረገነት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ከ20 ዓመታት በፊት አሁን ፓትርያርክ የሆኑት አቡነ ማቲያስ ከወያኔ የተሰጣቸውን የሰሜን አሜሪካ የሊቀ ጵጵስና ሹመት አመዛኙ የደብረ ገነት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አባላት አንደተቃወሙና በዚህም ምክንያት አቡነ ማትያስ በመቶ ሺዎች የሚገመት ገንዘብ ዘርፈው ሄደዋል። ገንዘቡን ሊወስዱ የቻሉት ወ/ሮ ሐረገወይን የምትባል የገንዝብ ያዥ በመሆኗና እርሷ ደግሞ ከአቡነ ማትያስ ጋር ጵጵስናን የማይመጥን ህገወጥ ግንኙነት ስለነበራት በሷ አማካይነት ነበር ይላሉ። በገንዘብ የተነሳ በውጭ አገር ከሚገኙ የኢ/ኦ/ተ/ ቤ/ክ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለማዊ ፍርድ ቤት ድረስ በመሄድ አቡነ ማትያስ ፋና ወጊ ጳጳስ ተብለው ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው ይላሉ። ጉዳዩን የሚያወቁት ምንጮቻችን እንደሚሉት በተካሄደው የፍርድ ቤት ክርክር ከፍተኛ የቤተክርስቲያን ገንዘብ እንዲባክን ሆኗል። በተጨማሪም አቡነ ማትያስ ሲያጠምቁ፣ ሲባርኩና ሲያቆርቡ የኖሩበትን የደብረ ገነት መድኃኔዓለምን ክርስቲያኞችን አውግዘው የተለዩትን ሕዝበ ክርስቲያን እንዴት ሆኖ ነው በአቡነ ማትያስ ስር የምንሆነው? ይሄ እጅግ የሚያሳፍርና የሃይማኖትንም ሕግንም የጣሰ ነው በማለት በቁጭት ይናገራሉ። ከአምስት ዓመት በፊት መምህር ዘበነ የቤተክርስቲያኑ አለቃ አንዲሆን ከፍተኛ እርብርቦሽ ባደረጉና ይህ ሹመት ለመምህምር ዘበነ ለማ “አይገባውም፣ይብሰል፣ ምራቁን ይዋጥ” ባሉ ምዕመናን መካካል ተፈጥሮ ከነበረው ውዝግብ በስተቀር ለረዥም ዓመታት ቤተ ክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንቡን ጠብቆ የአስተዳደር ቦርድ አባላቱን በመምረጥ በሰላምና በፍቅር እንደ ቤተሰብ ሆኖ የቆየ አንጋፋ ደብር እንደሆነ እነዚህ ምዕመናን ይመሰክራሉ።

ሆኖም ከአምስት ዓመት በፊት በመምህር ዘበነ ምክንያት በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው ንትርክና ጭቅጭቅ እንዲሁም አባላት በወሰዱት አቋም ምክንያት ከረዥም ዓመታት ወዳጆቻቸው ጋር አጣልቷቸው የነበረው የአንድ ግለሰብ ጉዳይ አሁንም መልኩን ቀይሮ ተመልሶ መምጣቱ እንዳቆሰላቸው ገለጸውልናል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ለወያኔ ወሬ የሚያመላልሱ ግለሰቦች ከምዕመናኑ ጋር ተቀላቅለው ቤተክርስቲያኑን ለወያኔ ለማስገባት በመህር ዘበነ ለማ የሚሰጠውን ቤተክርስቲያኑ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው ሲኖዶስ ውስጥ ካልገባ በስተቀር ትክክለኛ ቤተክርስቲያን ተብሎ ሊጠራ አይችልም  የሚል በማር የተለወሰ መርዝ በምዕመናን ጭንቅላት ውስጥ እንዲቀረጽ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ይናገራሉ። ቀጥለውም ሲያብራሩ መምህር ዘበነ ለማ በሸረበው አዲሱ እያንዳንዱ ምዕመን በነፍስ አባት ስር የማደራጀትና የመጠርነፍ ተንኮል ያሰበውን ለማሳካት ሙከራዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል። በዚህም ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መመሪያ ከወያኔው ንቡረ ዕድ ኤሊያስ አብርሃ ለመቀበል የእንቁጣጣሽን በዓል ከምዕመናን ጋር ካከበረ በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደሚበርም የደረሰን መርጃ ይጠቁማል። ይህንን በግልጽ የሚደረግ የወያኔን ሴራ በተለይም በነፍስ አባት ስም የሚካሂደውን ጥርነፋ እንዴት ምዕመናን ተቀብለው እንደሚቀጥሉ የሚታይ ይሆናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን ጥርነፋ ጠመንጃ ተደግኖበት፣ ሳንጃ ተወድሮበት በግዳጅ እላዩ ላይ ቢጫንበትም እዚህ የዲሞክራሲ ማዕከል በሆነችው አሜሪካ ውስጥ እየኖሩ በተወናበደና በተጣረሰ ትምህርት በነፍስ አባት ስም እራሳቸውን በፈቃዳቸው ለማስጠርነፍ የሚቀበሉ ካሉ ወያኔ ምን ያህል መሰሪ መርዙን በውጭው ዓለም መርጨት መቻሉን የሚያሳይ ይሆናል።

ከዚህም በተጨማሪ የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ካህናት በመምህር ዘበነ ምክንያት ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው እንደሆነና ብዙዎቹ ከስራና ከደመወዝ እንዳይታገዱ ወይም እንዳይባረሩ ተሳቀው እንደሚያገለግሉ ይናገራሉ። በተለይም በቅርቡ የሊቢያን ሰማዕታት አስመልክቶ በዋሽንግተን ሞኑመንት አጠገብ በተደረገው የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት ላይ በውጭ ከሚገኘው በአቡነ መርቆርዮስ ከሚመራው ከዉጪው ሲኖዶስ የመጡ ጳጳስ ከመገኘታቸው ጋር በተያያዘ ለውጭው ሲኖዶስ ታማኝነታቸውንና አክብሮታቸውን የገለጹ ካህናት ከመምህር ዘበነ ትንኮሳና ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ታውቋል። በተለይም አንዱ አንጋፋ ካህን ለረዥም ዓመታት ከክፍያ ነጻ ማገልገላቸው ሳያንሳቸው እንደ አንድ ምዕመን የአባልነት ክፍያ እየፈጸሙ ቤተክርስቲያኑን በገንዘባቸው፣በጉልበታቸውና በክህነታቸው የሚረዱ ጠንካራ ካህን ቤተክርስቲያኑን በወር $5,000 የሚያስወጣው ካህን ሊገፋቸው መፈለጉና የአስተዳደር ቦርዱ ይህንን ግፍ ለማስወገድና እኝህን ጠንካራ አባት ሊታደጋቸው አለመቻሉ ብዙዎቹን ምዕመናን እንዳሳዘነ ለመረዳት ችለናል። በዚህ ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የደረሱንን ሌሎች መረጃዎችን ትክክለኛነት አጣርተን መረጃዎቹን ለህዝብ ዕይታ እንደምናደርስ ከወዲሁ እናስታውቃለን።

111 Comments on “በዲሲ ትላልቅ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ወያኔ አዲስ ዘመቻ ከፈተ”

  1. በእውነት እይተካሄዱያሉት ችግሮች ቀደም ሲል በአባ መላኩ ጌታነህ የተሸረበ ሴራ እንደሆነ ይታወቃል

  2. በጣም ቀልብ የሚስብ ሪፖርት ነው። ወያኔ በረቀቀ ስልት ለስልጣንና ጥቅም ያደሩ ጥቂት ካህናትን አሰማርቶ የኦርቶዶክስ ቤተክርስያንን የማዳከምና የሱ መገልገያ ለማድረግ የሚያደርገውን ዘመቻ እያንዳንዱ ምእመን መመከትና የወያኔንን ተላላኪዎች ከመሀሉ ነጥሎ ማውጣት አለበት።

  3. Betam yemiysazen neger behayamanotachinina be betekirstiyanachin laye eyetefesem yalewu aremenewun weyane le magelegel bemiruaratu ende Tesfaye Mekoya Zebene Lema Adisu ena lelochin be hodachewu yemigezu aderbayoch newu hezbum min endenekawu bayetawekem sayawukewu lenesu mesariya eyehone endehone eyayen newu beteleye ye senbet temariwochina enat zemariwoch yemibalut nachewu yebasut be Mariyam betekerestiyan yetayewum yehewu newu betam yemigeremewu tabot endayeweta agedewu yerasachewun yemayereba megelecha yaluten kakerebu behuala kiresetiyan kememsel tabot siweta agebewu eyezemeru mehedachewu betam betam asafari newu asemesaye kirestiyanoch engi ewunetegoch bihonuma noro kedemiya le kibrenegsu besetu neber betekirestiyanun lemafres alama balachewu ye weyane telalakiwoch aderaginet yetegemerewu betekirestiyanin ye mafres zemecha mekom yenorebetal manigawum ye orthodox lig yagebagal bilo zeb mekom yenorebetal betam yemidenekewu yanin hulu chuhetena tegel tekakumewu mekom chilewu hizebunyekereta meteyekachewu min yahel le haymanotachewu tegzi mehonachewun be Dr, Amare tihtina masayet tegenzebenal. bewektu bayekeshef noro ende weyanetelelakiwoch eked bihon noro telek erebsha yefeteren bizu sewum ligoda yechel neber Egzeabher yemesegen tegaltewal ahunim bihon be tinikake meketatel yasefelgal Tesefaye Mekoya be Arsema sim yakuakamewu ye mafiya buden sayawukut ye weyane ye gedayu mesariya eyehonu selehone we de libonachu temelesu enelalen bekirebu yehulunim zerezer beye websayetu bemeletefe hizebu endiyawukachewu enaderegalen.

  4. Tirnefa 1 le 10 ye nebs abat ?

    aye weyane kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk

    eshi belo yemeterenef kale

    abarut !!! sayqatel be Qetel !!! kkkkkkkk

  5. Adisu Abebe belo Kahen ! kkkkkk

    Adisu eko,Bandira leqeyer new yetebale Zize

    be and interview lay,,,ye Bandieaw neger aleqelet belo

    yetesaleqeben sew new !!!

    yemettal Qen enitezazebalen !!!

  6. ወደ አንድ ወገን ያደላ በጥላቻ የተሞላ ሀሳብ ነው።እውነት ያሸንፋል።ቤተክርስቲያን የክርስቶስ እንጂ የማንም አይደለችም፡፤

  7. Zebene makes $5,000 a month??? Whomever approves this unjust compensation for this individual should be ashamed of their reckless and irresponsible act. As far as I know, the church has 2 Million Dollars debt. How can they pay him with this much debt hanging on their head?

  8. ፓለቲከኞች እባካችሁ እጆቻችሁን ከቤተ ክርስቲያን ላይ አንሱ ፣ ቤተክርስቲያንን መጠቀሚያ አታድርጓት ። ምን አገናኘው ይሔ ድሕረ ገጽ የፓለቲከኞች ነው ።

  9. Zebene, Zebene I remember when he first came to Washington dc he was wearing a tiny scarf and a dress coat with its pair of pants in a cold March month if I’m not mistaken. From that his arm became firmer and firmer, his voice became louder and louder his arrogance is in abundance. Zebene I’m an die hard and firm Ethiopian Tewahido orthodox church member. I’m sorry we came to this point. Yes I also heard a genuine member of the clergy is being pushed around. First of all Zenebe did chastised Melake Genet Wubu after all his hard work to keep the church for a long time and ended up home bound. I think Melake Genet’s torment by zebene contributed for his ailment, he is in a better place now. And letter on Getahun was kicked out, now this? Zebene is getting paid $5000 which equals to 100 couples $ 50 monthly members payment. Enough is enough.

  10. Why is it always woyane to blame ? ? Its so bulshit ! ! ! Dr. Aklilu Hbte Is a respected Ethiopian of highest caliber so is Adisu Abebe.Hizben min nekaw Agere Ethiopias min bedelech ? ? It ourselves to blame and do not use woyane just to get your ill motives look and sound good.Posting it as “seber zena”because some one has a church education.Egzioooooo Maharene krstos ! !

  11. የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች፤ ልጆቿም ያልቁና እርሷም ትሞታለች ተብሎ የተተረተው ለኛ ለኢትዮጵያውያን ሳይሆን ኣልቀረም መሰለኝ እና ኣንድ ወሬ ተገኘ ተብሎ ምንም ዓይነት ማጣራት ሳናደርግ ይህንን ያህል ኣፋችንን ሞልተን መናገራችን ኣሳፋሪ ነው፤ የኢትዮጵያዊ ጨዋነታችንም የት እንዳደረስነው ራሳችንን መጠየቅ ይገባናል።
    የኣዛኝ ቅቤ ኣንጓች እንዲሉ፤ የቤተ ክርስቲያኗ ተቆርቋሪ መስለው እኛን ኣናቁረው ጠንካራ የቤተ ክርስቲያን ኣባቶቻችንንና መምህራኖቻችንን ለማጥላላት የሚደረገው፤ ከፕሮቴስታንቶች ጭምር እንደሆነ ረጋ ብለን ልንመረምር ይገባናል።
    እነዚህ የተጠቀሱት መምህራኖች፤ የነርሱን መምህራን ባዶነት ራቁቱን ስላውጡባቸው፤ የተጠቀሙበት ስልት መሆኑን እንድናስተዉል እግዚኣብሔር ይርዳን። አሜን።

  12. በጣም ያሳዝናል ! ! ! ኣዲሱ ኣበበ የወያኔ የሞት ፍርደኛ መሆኑን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ማን ነው ? ? ? መንጋ ቆሻሻ ! ! !

  13. ይህ የወያኔና አራጋቢ ፕሮቴሥታንቶች ድምር ውጤት ነው ይህ አዲሥ አይደለም በ አ.አ ያሉ አብያተ ክርሥትያናት ሠበካ ጉባኤ የልማት ኮምቴ ወዘተ የሥርአቱ ካድራዎች በልማት ሥም የቤ.ክ. ንዋይ እየተዘረፈ ይገኛል ከሀገው ውጭ ደግሞ ይህን ነዋይ ለፖለቲካ እርዳታ እንዳይውል በሚል ክትትል የራሡን ቄሥ ካድሬዎችን ይልካል ያደራጃል መረጃም ይቃርማል ገቢውንም ወደ ካዝናው ያሥገባል ይህን መሠል የማተራመሥ ተግባሩን በየ ሀገራቱ ብዙ መረጃዎችን እየሠማን ነው የወያኔ መንግሥት በሀይማኖት ላይ ያለውን ጣልቃ ገብነት ፈፅሞ ያላቋረጠ መሆኑን ያሣያል በተያያዥነት በ ሙሥሊሙ ማህበረሠብም ተመመሣሣይ በ ሀይማኖት ፅንፈኝነት ፍረጃ አሣቦ የፖለቲካ ትርፍ እያገኘ ነው ሥለዚህ ይህን ክፍተት የምንሞላው እኛው ነን በህብረት የወያኔን ሥርአት ከሥሩ እንደአረም ሥን ነቅለው ነውና በጋራ ትብብር ላይ አብረን መሥራት ይኖርብናል።

    ሞት ለወያኔ ዘረኛው ድርጅት

  14. እጅግ በጣም ይሳዝናል። እኔ ዶ/ር አክሊሉ ዝም አሉ? በዉነት የያዘን በሽታ ቀላል አይደለም። ገና ለገናው እንደራሳቸው ለ20 ዓመታት እንደሆቴል ሲያዙባት የነበረችውን ቤተክርስቲያን ከስልጣን ተነጠቅቁ ብለው ነው ይህን ያህል ለወያኔ አሳልፈው ለመስጠት የደረሱት? አሁን በ85 ዓመታቸው ምን ፈልገው ነው? እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ይሉሀል ይሔ ነው።

  15. Christian do not lie የሚለው አልገባኝም። ስለአጋለቷቸው የሚለው ማንን ነው። ደግሞ የፕሮቴስታንት እቅድ የሚባለው ብዙ ጊዜ ለማታቻ የሚቀርብ ነገር ግን ፕሮቴስታንት ቢሆን በወያኔ እቅድ መሰረት እንደሚንቀሳቀስ አንርሳ። ወያኔ መጀመሪያ እስላሞችን፣ ቀጥሎም ፕሮቴስታንትን በማበረታታት በአኦርቶዶክስ ላይ ዘመቻ እንዳደረገ እናውቃለን። ቀጥሎ ክስላሞች ጋር ስለተጣላ አንድ የቀረው ፕሮቴስታንት ብቻ እንደሆነ እናውቃለን። ፕሮቴስታንትም አሁን እየተገለበጠባቸው ነው። የወያኔ ደጋፊዎች በገንዘብ የተገዙ ሰባኪዎችና ሌሎች ጥቅመኞች ናቸው። በአጭሩ ፕሮቴስታንትም በለው የእስላም አክራሪ የወያኔ የእጅ አዙር የጥፋትና የማዳከም ሥራ መሆኑ ከ 25 ዓመት የወያኔ ተንኮል የተረዳነው ስለሆነ በምገባ እያስተዋልን ነው። ግራም ነፈሰ ቀኝ ወያኔ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ኡርቶዶክስን ማጥፋት ዓላማውና ስራው መሆንኑን ለአንዲት ደቂቃ እንዳንዘነጋ።

  16. የወያኔ አቅድና ኣላማ የታወቀ ነው። የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ማውደም ነው። ይህንን የድርጅቱ መስራች የነበሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አረጋግጠውልናል። አቶ ስብሃት ነጋም ኦርቶዶክስና አማራ መጥፋት እንዳለባቸው የድርጅታቸው መመሪያ እንደሆነ ሳይሸሽጉ አስታውቀዋል። ወያኔዎቹ እኮ መመሪያቸው ስለሆነ አያፍሩበትም፣ አይክዱትም። ወያኔ ይህንን ፖሊሲ ስራ ላይ ለማዋል ከሚጠቀምበባቸው ስልቶች ውስጥ አንዱ ምእመናን እምነታቸውን እንዲጠሉና ቤተክርስቲያኑዋን እርግፍ አርገው እንዲተው ለማድረግ የውሸትና በተለያዩ ቤተክርስቲያኑቷ በምትኮንናቸው ድርጊቶች የተበከሉና የተጨማለቁ ካህን ተብየዎችን በየቤተክርስቲያኑ አሰርገው ማስገባት ነው። ከአገር ቤት አንስቶ በተለያዩ የአሜሪካ ስቴቶችና በተለያዩ የአወሮፓ አገሮች ውስጥ ይህ ፖሊሲ ስራ ላይ መዋል ከጀመረ ከ20 አመታት በላይ ሆኗል። ለአብነት ያህል ታደሰ ሲሳይ በዝሙት ተጨማልቆ በተመሳሳይ ህጸጽ ውስጥ ባሉት በአቡነ ማቲያስና በአቡነ ፋኑኤል ድጋፍ እየተደረገለት የወንጅል ስራውን አጠናክሮ ቀትሎበታል። ቤተክርስቲያኒቷ በርካታ ቁጥር ያላቸው እውነተኛ ካህናትና አባቶች ያሏት ቢሆንም የቤተክህነቱን ኣመራር በእጃቸው የያዙት ግን ወያኔዎቹና ወንጀለኞቹ ናቸው። አንዳንድ ከምዕመና ወገን ያሉ ለምሳሌ እንደ አዲሱ አበበ አይነት የመንግስት ጋዜጠኝነት ስራውን በመጠቀም ባገኘው ታዋቂነት በመጠቀም ቤተክርስቲያንን እየታገለ ይገኛል። አዲሱ ወያኔ የፈረደበትን የሞት ፍርድ ለማስፋቅ እንደ ሰለሞን ተካልኝ ግልጥ ያለ ወያኔያዊ ስራውን በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚያደርግ ሁኔታውን በቅርብ የሚንከታተል ሰዎች የምናውቀው ነው። አዲሱ አበበ በምዕመናን ድምጽ ብልጫ በመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተመረጠውን ቦርድ ከውስጥ ሆኖ ሲገዘግዝ ቆይቶ አሁን ግን በግላጭ እንደ ዶ/ር አክሊሉ ዓይነት ቤተክርስቲያኑዋን እንደ ግል እርስትና ንብረት የሚቆጥሩ ሰው ህዝብ ከሥስልጣን ስላወረዳቸው ባደረባቸው ቁጭት በመነሳት ለአዲሱ አበበ አጃቢ በመሆን እራሳቸውን አዋርደዋል። ምናልባት ዶ/ር አክሊሉ ለብዙ አመታት ከተለዩዋት ኢትዮጵያ ለመግባት ከአዲሱ ጋር መሞዳሞድ አስፈስጉዋቸው ይሆናል። በማናቸውም መስፈርት ቢለካ የዶ/ር አክሊሉ ድርጊት ለብዙ ኣመት ሲወስኑና ሲያዙ የነበረው የቤተክርስቲያን ስራ ጉዳይ እንኩዋን ቢተጓጉል ሃላፊነት መውሰድና ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂነታቸውን ማረጋገጥ ሲገባቸው ሾልከው ለማምለጥና ችግሩን በሌሎች ላይ ብቻ ለማላከክ የሚያደርጉት አሳፋሪ አካሄድ እጅግ አሳዝኛና ታሪካቸውንም የሚበክል ነው። የሳቸው ነገር ሲያልቅ አያምር ኣይነት ሆኖባቸዋል። አንዳንዶች ጃዱ ወይ እያሉ የሚጠየቁም አሉ። እሲቶ ዶ/ር አክሊሉ ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ነኝ ካሉ ለምንድነው እንደ ታደሰ ሲሳይና አባ መላኩ ዓይነት ወንጀለኞችን ሲኮንኑ የማይታየው? በዝሙት የተበከለ ካህን አይደለም እንዴ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳው? በእርግጥ አዲሱ እንዲ አይነቱን ቆራጥ እርምጃ ይወስዳል ተብሎ አየጠረተርም። የፕሮቴስታንት ፓስተር ሚኒሶታ ውስጥ በዝሙት ቅሌት ውስጥ ገብተው የነበረውን ዜና በሚዲያ ሲያቀርብ፣ ታደሰ ሲሳይ ትዳሩን ያፈረሰበትን የኦርቶዶክስ አባል ግን ሊያንግረው እንኩዋን አልወደደም። አዲሱ በጣም በአስተሳሰቡ CORRUPT የሆነ ለጋዜጠኝነት የማይመጥን ገላባ ሰው ነው። በነገራችን ላይ የሚኒሶታውን የዝሙት ቅሌት የሪዲዮ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ከፓስተሩ ጋር የተኛቸውን ሴት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግላት በዝሙቱ ድርጊት እሱም የጎመጀና የፍትወት ፍላጎቱ የተቀሰቀበት ይመስል ነበር። ለምሳሌ ሴትየዋን ምን በላችሁ? የት ሄዳችሁ? የሚጠይቀው ጥያቄ በሙሉ እሱም ሴትየዋን እንደፈለጋት ያስመስል ነበር። ታዲያ አዲሱ በዝሙት ቅሌት ስልጣነ ክህነቱን የተገፈፈውን ታደሰ ሲሳይን ቢደግፍ ምን ያስገርማል። ዘመድ ከዘዱ አህያ ካመዱ አይደለም እንዴ?

  17. Good question do you think they/he care about the Church as long as he gets what he want. Even most of the board members are his supporters, don’t forget what Abine Mathias did to the church before he took all the money by the help of his girlfriend Haregwoine. this is the fact.

  18. Can you tell us the clear information if this is not true? you must be jocking who is a strong preacher the woyane telalakis? please think twice before you talk everybody knows who is who do you think those are a true Christian so sad.

  19. The main purpose of this article is just to destruct the orthodox church and create chaos and suspicion among the followers. The author of this article has never contribute a penny to the church but he /she may got a big cash from people who do not want to see the strength of the church. Problem or misunderstanding may exist any where or in any system but the solution finders are the members who devoted to the particular group or system only not the outsider who patches unrelated gossips news to tabloid news outlet.
    God gives strength and unity to our church!

  20. Yezeh report azegajoch, Egziabhern yemetamenu kehonachhu, yeneseha edmie endisetachhu entselyalen. Ebakachhu, Ye tekedesechwun Bete Chrestianen, Tewahido Emenetachenen ke poletica gar eyekelakelachhu sewun atawonabedut. Egziabher lebona Yistachhu.

  21. የሚገርም ነው ፖለቲካና ሐይማኖትን በአንድ ላይ በፍፁም አይሄድም በርግጥ የዲሲ ማርያም ቦርድ አባላት አብዛኞቹ ፖለቲከኞች ናቸው ወያኔ ስልጣን ካለቀቀ እያሉም ይነግሩናል ወያኔ አስቂኝ ድራማ ሰረቷል 100% ምርጫ አሸነፈ ሀሀሀሀሀሀሀሀ የእሱ መንትዮች በተመሳሳይ ሀኔታ ለሶስተኛ ግዜ በመንፈሳዊ ካባ ተሸፍነው በዲሲ ማርያም ቦረዱ 100% አሸነፈ ዛሬ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በመንፈሳውያን እንመራ ብለው ሲጠይቁ ነገሩን ገልበጥ አደረጉና ከወያኔ ጋር አገናኙት ፖለቲከኞቹን?(ቦርዱን) ነፃ ለማድረግ እናንተ ይህን ፅሁፍ አወጣቹ በጣም ያሳፍራል እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው አንድ ቀን ፍርዱን መስጠቱ አይቀርም ግን ቤ/ክ ተጀምሮ ለአላስፈላጊ ወጪ የዳረገው ማነው??? አጠቃላይ ጉባኤው ና መላው ሕዝብ ጋዝ ስቴሽኑ (ማደያው)እንዲገዛ ወስኖ እነዳይገዛና አሁን ግርግዳው ላይ በደረሰው መሰንጠቅ ለእሱ ድጋፍ አድርገው ፍርድ ቤት በክርክር ላይ ገንዘቧን ለብክነት የዳረገው ማነው ? አሁንስ ግንባታው በመቆሙ ለኮንትራክተሩ በየወሩ ከ$40,000 ዶላር በላይ ቤ/ክ እንድትከፍል እዳ ውስጥ የጨመራት ማነው ??? ቤ/ክኗ እራሷን ችላ እንዳትንቀሳቀስ ነቀረሳ የሆናት ይህ በፖለቲከኞች የሚመራው ቦርድ ብቻ ነው ። ባጭሩ ከሰንበት ት/ቤቱ ና ወጣቶቹ ላይ እጃችሁን አንሱ ።

  22. ከላይ Anonymous በሚል ይህን የጻፉት ” …….የሚገርም ነው ፖለቲካና ሐይማኖትን በአንድ ላይ በፍፁም አይሄድም…….” ያሉት ይህንን መልስ ለመጻፍ አስገድዶኛል። እንዴ በጣም የሚገርም ነው እኮ። ፖለቲካ አይደለም የሚሉ ደደቦች እራሳቸው ደደበው ሌላውን ለማደደብ የሚፈልጉ ናቸው። ፖለቲካውን ቤተክርስቲያን ውስጥ ያስገባው ወያኔ አይደለም እንዴ? ህጋዊውን ፓትርያርክ ከመንበራቸው አውርዶ ጎሰኛውን የወያኔ ጆሮ ጠቢ በምትካቸው ያስቀመጠው የኢትዮጵያን ፖለትካ በጠመንጃው የሚቆጣጠረው ወያኔ አየደለምን? አባ መላኩ በዝሙት የጨቀየውን ታደሰ ሲሳይ ኢትዪጵያ ልከው አሹመው ከነ ወንጀሉ ነፃ ሰያወጡት የታደሰን የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ተከታይት አረጋግጠው ነው። አዲሱስ ከአባ መካኩና ከታደሰ ሲሳይ ጋር አብሮ ሲቆም ፖለቲካቸውንና መዋቅራቸውን ተቀብሎ ነው። በዋሽንግተን ሞኑመንት ላይ የተደረገው ዝግጅት ላይ መምህር ዘበነና መምህር ተስፋዬ መቆያ ያልተገኙት በፖለቲካ ምክንያት ወያኔ በሚወቀስበት መድረክ ላይ ላለመታየት ብለው እንደሆነ እራሳቸው አምነዋል። ስልሆነም በሁሉም ቤተክርስተያኖች ውስጥ ያለው አይነተኛ ጉዳይ ፖለቲካው ነው። ሎሎቸ ጉዳዮች የፖለቲካው ተቅጥላና ማጣፈጫ ቅመመሞች ናቸው።

  23. የነ አዲሱ የቤተ ክርስቲያን አድማና መፈንቅለ-ቦርድ አይሳካም። ከወያኔ ጋር ለመታረቂያ ቤተክርስቲያናችን እንደ ጭዳ ለማቅረብ የተወጠነው ሴራ ይከሽፋል። አንዳንድ ስነ ምግባር የጎደላቸው ካህናት ለምሳሌ ቄስ ኃይሉ የተቸገሩ በተለይም ሴቶችን ጸሎት ኢትዮጵያ ድረስ ተደዋውዬ አጸልይላቸኋለሁ እያሉ አለደረሰኝ ገንዘብ እንደሚቀረጭጩ የማናውቅ መስሏቸው ከሆነ በጣም ተሞኝተዋል። እንደነዚህ ዓይነት እንከን ያለባቸው ናቸው ለወያኔ መጠቀሚያ ለመሆን በቀላሉ የሚሸነፉ። የዕሁዱ ግርግር አዲሱና ካምፓኒው የአባላትን ጠቅላላ ጉባዔ ለማስጠራት የሚፈለገውን ያህል ቁጥር ለማስፈረም ስላልቻሉና አብላጫው የደብሩ አባላት ስለተቃወሟቸው እረብሻ አስነስተው የምዕመናኑን ትኩረት ለመሳብና ከረብሻው ተጠቃሚ ለመሆን ሙከራ እያደረጉ ነው። አዲሱ ከራሱ አልፎ በደብሩ የተከበሩ ሰዎችን አብሮ ከእድፉ ሊለቀልቅ መሞከሩ በጣም ያሳዝናል።

  24. Anonymos you are a big liar everybody knows the truth you are talking nonsense we all knows what you said on Sunday. you all are a bunch of looser you better disciplined yourself before serving the church.

  25. ፖለቲካ ጥሩም ሆነ መጥፎ የራሱ የጉዞ ሂደት አለው ነገር ግን ቤተክርስቲያን አቅሞ በፈቀደ ልጆቻዋን ይዛ በሃይማኖት አምነቱን አንዲጠብቁ ታደርጋለች፤ ቤተክርስቲያን በተላያየ ጊዜ በተላያየ የፖለቲካ ሥርዓት ተፈትናለች ይህን ለማወቅ ብዙ ወደኃላ የታሪክ ጉዞ መሄድ አያስፈልግም፥ የማገነዘብ አእምሮ ብቻ ነው የሚያስፈልገው አውነተኛ አማኝ ልጆቿ የቤተክርስቲያንን አንድነትና ጥንካሬ ነው የሚያንገበግባቸውም በገንዘባቸውም ሆነ በጉልበታቸወ ሌት ተቀን የሚለፉትና የሚጥሩት:: ነገር ግን ጥቂት የበግ ለምድ የለበሱ እምነቱ የሌላቸው ቤተክርስቲያን በመምጣት ወይንም አሉባልታ በመቃረም ቤተክርስቲያንን ሰላም ሲነሷት ይታያል፥ ስህተት ሊፈፀም ይችላል ሰዎች ናቸውና ይህ ስህተት ይፍፀም የነበረ ኣሁንም ያለ ወደፊትም የሚኖር ክስተት ነው:: ስህተቶች በረጋ መንፈስ መተራረም የሚኖርው በቀና መንፈስ አማኙና ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆርው ምዕመን ቁጭ ብሎ ሲነጋገር ብቻ ነው፥ የቤቱን የጨቀየ ጉድፍ ለጓደኛው የማይናገር ግን አሉባልታ በተሞላ ወሬ የቤተክርስቲያን ሰም ማጥፋት አና ሰላምን መንሳት የወሬውን ኣቡኪና ፈትፋች ማንነት ይገልፃል::

  26. ዮሐንስ 8 (John)
    44፤ እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። በውኑ በደብረ ሰላም በሰንበት ትምህርትቤቱ ለምእመኑ የቀረበው የጹሁፍ ሪፖት አሁን ከወያኔ ከተባለው ጋር ምን ያገናኘዋል?????? ወያኔ ነው እንዲ በዲሲ ማርያም ተተክሎ የህዝቡን ገንዘብ እንክት እያደረገ ያለው ለ18 ዓመት ሂሳብ ሹም ሆኖ አለቅም ብሎ ተተክሎ ያለው ማነው??? ቤተክርስትያኒቱን የግል ሀብት ማከማቻ የፖለቲካ ድርጅት መፈንጫ ያደረጋት ያለው ማነው????እንግዲህ ህዝብ እንዲፈርድ የእሁዱን ጥያቄ በተመለከተ በእጃችን ያለውን ቪዲዮ እንለቃለን ።ከላይ የተጻፈውን ውሸት እና ቪድዮውን እዮና አንባቢ ይፍረድ ቪዲዮ ያለቀቅነው የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ጠባቂ ሊቀ ካህናት ወርቅነህ የቤተክርስቲያናችንን ገዳይ እዚሁ እንፈታለን ምንም አይነት ቪዲዮ እንዳትለቁ ስላሉ አክብረን ነው ።እነዚህ በወደቀ ፖለቲካ አማካኝነት ልባቸውን ዲያብሎስ የትቆጣጠረው ሀዋርያው እንደተናገረው መጨረሻቸው ጥፋት ነው ።ሆዳቸው አምላካቸው ነው።ክብራቸው በነውራቸው ነው ።ሀሳባቸው ምድራዊ ነው።ፊል -:3:-19

  27. Rubbish no time for Derg bandits. Your oppressive era is long gone. Any church which is not governed by kenan low is not a church.

  28. ወገን ሆይ አሁንም እናሥተውል የወያኔ መንግሥት በይፋ በተልይ የገደል ሟሚቶው ሀይለማርያም ደሣለኝ የተፃፈውን መፅሀፍ ተግባራዊ አድርጉ የሚል መመሪያና ማሥጠንቀቅያ አዘር ንግግር ለአባቶች ማድረጋቸውን አንዘንጋ ይህን መፅሀፍ ምን እንደሆነ መረጃው ያለው ያጋልጥ።

    ወያኔ አሁንም እጁን ከሀይማኖት ላይ ያንሣልን ጥሪውን ይቀበል !!!

  29. Hana ; for the sake of church unity please stick by the decision you made first and do not be provoked by a few anti orthodox people gossips . Do not release any video or a sensitive material which perturb the church unity. Christians do not follow the wake of the other spectrum of people. The motive of the writing is to trigger the distraction of genuine Christian on its belief and to bring them to their camp for their ultimate target of disintegration of the church. It does not need to be an expert to know the true nature of the making this kind of news; they always scribed for disintegration but never used their pen for the growth of church. These people do not have a slight concern or sympathy about the church on the contrary increased number of people going to the church and devoted to its religion makes them to pump up their envy rate to infinity. Church is for its followers and believers only not to infiltrators. Any misunderstanding or wrong doing must be corrected by throwing away self-ego attitude and praying together first to discuss on issue of resolving problem which favors church integrity and unity. After all we are all human and make mistake but if we have love, humility, and strong belief in our heart all problems will be solved smoothly by the Almighty God.

  30. Hana if you release the video or not doesn’t make any difference sooner or later the truth will come out, off course what was read by the youth group is nonsense they should have respect the Tabot and finish the ceremony instead of announcing their rubbish and pretending to cover their evilness by singing, that is not christianity.

  31. Betame yemgarmawe nagare telko chiger yalewe bordo lay new
    Be 5 amate weste abatochine mabarare hezbone enda eyehadig mekfafele ye betkersteyanone birr yale agebabe mebelate ye bordo sera new enjey kelay endatbalew ayedalme
    Polticana berkersteyane yeleyayale eyandandcho firdone kelay tekbelalchu
    Ye ha new ewnatu

  32. Where did you get this nonsense information? are you the supporter of Amare kassaye first and most you need to research and get the whole information before you post this untruth biased thing…Dr Aklilu Kesis Tesfaye Kesis Metenu Addisu Abebe KesE Abreham Diacon Elias Kes Wondwosen why qwould this stupid board member will terminate their
    God chosen service? because the church is lead by EPRP (ehapa) even the so called Kese amare who have no doctorate degree who lied three times to the people by saying he studied teology gthen he studied law then he said he studied poletical science… A typical EPRP member with its board memebers and a few old ladies who have no relevant to the situation….They are the one to blame not those innocent pristes and choirs I am baffeled by the whole situations I was there I saw the whole thing I video recorded soon everyone will see he whole truth and the person who post this should be ashamed…get the fact before you bark on the wrong tree

  33. Selame mejamerya mahbera kidusan bendanchy ayenato menme yemayaweke sew yemtara ayedalme
    Majemrya alamawen ewakey ke mawratshe bafit ok.

  34. Well, if i have to blame i blame myself for not knowing how to react for any wrong doing in my church then i pray to God to guide me through it: please let’s stop being prejudice.

  35. tazabi do you really know what you are talking about you rude words express who you are, most people you named are committed adultery everybody knows that. The board are working hard and stop the peoples from stealing the church money that’s why your God given priests are not happy about them. the woyane agents like Tesfaye Mekoya and Adisu are trying to destroy the Church, you like it or not the truth will come out soon, about the video a lot of people has it, it is not a problem to post it if it is necessary but I don’t think it is. you better think twice before you are talking, Lets wait and see, you will be ashamed of not Dr. Keses Amare or the board.

  36. Tazabi, do you think that people are this foolish? This is the wrong theory blaming the non- existing EPRP? You might think some of the board members might be EPRP generation. I am next to the EPRP generation. I do not see any issue on regarding this.

  37. I do not want say it but sometimes it has to call a spade a spade. Some of you are Sunday morning Christian and you go to church for chatting with friends in topics that make your human flesh happy than listening the words of gospel. These kinds of people always fantasy to change the church to their own world. They do character assassination to individual or group who has positive contribution to the church while antagonize the church dogma & doctrine to satisfy the need of their material world. Some of the clergy member innocently or lack of analysis or with some other reasons cooperate with these damage causing pseudo Christians to divide and rule the confused with true or true seeking Christians. Our Church has already a well framed dogma & doctrine and we all go to church by accepting these rules to worship God from the bottom of our heart not to implement our confused idea & system that did not work from our previous association.

  38. አላርፍ ያለች ጣት __ ጠንቁላ ትወጣለች።

    በዲሲ ማርያም ቤተ ክርስትያን ለተፈጠረው አለመግባባት ምክንያቱ ከላይ የተጠቀሰው የወያኔ ጣልቃ ገብነት ሳይሆን፣ በቤተክርስትያኗ ውስጥ ከአስተዳዳሪዋ ጀርባ ስውር እጅ ያለው ኢሕአፓ በቀሲስ ተስፋዬ መቆያ አማካይነት በመጋለጡና ይህንን ተከትሎ መምህራችንን በፍልሰታ ጾም ወቅት በማባረራቸው፤ እንዲሁም ቤተ ክርስትያኗን የሚያምሱትን ሴቶች ቀሲስ ኃይሉ “ለምን መቅደስ ውስ ጥ ገብታችሁ አትቀድሱም” በማለታቸው “ሥራዎን በፈቃድዎ
    ይልቀቁ” የሚል ደብዳቤ በአስተዳዳሪው ስለደረሳቸው ነው። ነገሩ ተጋንኖ እዚህ ደረጃ ከመድረሱ በፊት መፍትሔ ለማፈላለግ የተደረገው ሙከራ በሙሉ አልተሳካም። ሰንበት ት/ቤቱ የወሰደው እርምጃ አማራጭ ስለጠፋና ማህበረ ምዕመናኑ እንዲያውቀው ስለተፈለገ ነው።

    እሁድ ዕለት በተፈጠረው ችግር በስተጀርባ የማንም ሰው
    ፣ ጳጳስም ሆነ ድርጅት እጅ የለበትም። የኢሕአፓ ጉልበቱ ምላስና ብዕር ብቻ ነው። ለርሱ ያልተስማማውን ሰውም ሆነ
    ድርጅት ሰም መለጠፍ የተለመደ ተግባሩ ነውና አይደንቀኝም። ስውር ዕቅዱን የሚያሳየውን ቪዲዮ እንለቀዋለን፤ ቤተ ክርስትያኗንለማዳን ከማሰብ የተነሳ።

    ቀሲስ ኃይሉ የቦርድ አባል አይደሉም። ፖሊስ የጠሩት የቄስ
    አማረ ወዳጆች ናቸው። ፖሊሶቹ ሲመጡ “ይኼ የአባቶች
    የልጆች ችግር ስለሆነ ራሳችን እንፈታዋለን” ብሎ የመለሳቸው አንድ ምዕመን ነው። ቄስ አማረ ፖሊስ መምጣቱን ሲሰሙ “እየታሠራችሁ ትሄዳላችሁ” ብለው በመናገራቸው የሰው መሳቂያ ሆነዋል።

  39. Amha igezabhare yesethe this is the truth.
    Dr amarma police. Semta eyandandcwen wesadlge new yalote aye menfesawi abate.
    Enay yemgarmage iko dr eya felsatane be kolo new yemthomote yebalale men waga alewe sew eyabdalo felsata letfeta 2 ken sekarewe kahene mabarere dinkame thome.
    Dr eye eko yebeako nachewe yebalelgale mebekate polaticaga mahone new enday
    Esachewe mene yawekalo yebalale angate dafe agare atfey alo abatochachen.
    yehanen lele yansasage weshate mararge lza new
    Betakerstyanachenne yembatabetote 8 amate mulu birrowne sebalo sebazabzo yenorote 7 sewochena yena dr amara aragabey ye wate bet setoche nachewe ewenato yehaye new.

  40. ከላይ አምኃ ብሎ የጻፈው ሰው በጣም መደዴና ደደብ መሆኑ ከቃላቶቹ መረዳት አያዳግትም። ለምሳሌ ይህንን መናገር ምን ማለት ነው”እንዲሁም ቤተ ክርስትያኗን የሚያምሱትን ሴቶች “ ይህ ደደብነትህና ለሴቶችና እናቶች ክብር የለሌህ መሃይም መሆንህን በዚህ አረጋግጠሃል። በሌላ በኩል እኔ እስከማውቀው ድረስ ኢህአፓ በመማቅሩም ሆነ በአሰራሩ ከደብረ ሰላም ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። እንደው በድርጅቱ ላይ ጥላቻ ካለህ በቀጥታ ማለት የምትፈልገውን ከማንም ጋር ሳታያይዝ መናገር ትችላለህ። ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ በሊቢያ የተሰውት ሰማዕታት እውነቱን ተናገረው ለማተባቸው መሆኑን የዘነጋው ይመስለኛል። እሱ ለማተቡ ሳይሆን የሚናገረው ወያኔን ላለማስቀየም ምክንያቱም ኢትዮጵያ ከመሄድ ላለመከልከል። በሊቢያ የተሰውት ወገኖቻችን ግን ማንንም ለማስቀየም ወይም ለማስደሰት ሳይሆን አምላካቸውን የሞተላቸውን ጌታችንንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማራቸው “እውነቱን እውነት፣ ሀሰቱን ደግሞ ሀሰት ብለው መራራውን የመጨረሻውን የሃይማኖት መገለጫ የሆነውን መስዋዕትነትን በኩራትና በክብር ተቀበሉ። በጣም የሚያሳዝነው ግን ለነዚህ ሰማዕታት በዋሽንግትን ሞኑመት የተደረገው መታሰቢያ ጸሎት ላይ እውነቱን ሳይፈሩ የሚመሰክሩ አባቶች ማለትም አቡነ መቃሪዮስ፣ እንዲሁም ቀሲስ አስተርአየ ጽጌና ሊቀ ማዕምራን ቀሲስ አማረ ካሳዬ እንደሚገኙ አስቀድሞ ስለታወቀ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያና ባልደረባው መምህር ዘበነ ለማ ላለመሳተፍ ከስፍራው ሸሹ። መምህር ዘበነ ለማ ይባሱኑ ስለመታሰቢያው ጸሎት አልሰማሁም ብሎ ካደ። እንደነዚህ ዓይነት ቀላማጆች ናቸው ቤተክርስቲያናችንን አሽመድምደው ያዋረዷት። በእርግጥ ከነዚህ ጀርባ አዲሱ አበበ የጋዜጠኝነት ስራውን ለፖለቲካ ሽፋን የሚጠቀም ወራዳ ግለሰብ አለ። ቀሲሲ ኃይሉም ቢሆኑ የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ እንደሚባለው በጸሎት ማጸለይ ስም ከምዕመናን እየተቀበሉወደ ኪሳቸው የሚከቱት ገንዘብ አስክሯቸው ካልሆነ በስተቀር ይህችን ቤተክርስቲያን የሚፈታተኑባት ሌላ ምክንያት የላቸውም።

  41. ወይዘንድሮ ምነው እግዛብሔርን ብትፈሩ ፖለቲካና ሐይማኖት አብሮ አይሔድም ከፍቅር ሕብረት ሰንበት ትምሕርትቤት ተማሪዎች ላይ ዕጃችሑን አንሱ ምንም የሐይማኖት ዕፀፅ የለባቸውም ዛሬ በምትሰርቁት የህዝብገንዘብ እና የቤተክርስትያን ብር ልባችሑ ተደፍኖ እውነት ሲወጣ ወዴት ጠጋ ጠጋ ቦርዱ ፖለቲከኛ ነው ምንም ጥርጥር የለውም አስተዳዳሪውም ዶክትሬታቸው በፖለቲካ ነው የገኙት ቤተክርስቲያኗ ፩ኢሐፓ ፪ ኢድዩ ፫ደርግ ፬አነዮዲት ጉዲት የሚመሯት ካህን የሚሰድቡ የሚያዋርዱ እንዲሑም ለ፱ አመት በዝብዘው ለግል ሕይወታቸው የተጠቀሙ መዝብረው ካዝናውን ባዶ አድርገው አሑንም ያልበቃቸው ኦዺት እንዳይደረግ የሚከለክሉ ታዺያ ማነው የቤተክርስትያን ጠላት ዲያብሎስ ብዙ መረጃ በማስረጃ የተደገፈ ህዝብ ፊት እና አለም እንዲያቀው እናወጣለን ።

  42. ሰርግ የሚደገስበት ሙሉክፍያ ያለቀቤት ለልጆቻቸው ሰው ያልነዳው መኪና ከአንድም ሑለት የሱቅ መክፈቺያ የሖነብር የሕዝብ ገንዘብ እንጂ የዶክተር አማረ አይደለም የእኔ ያንቺ የአንተ የእርሶ ነው ዝም አትበሉ እንዲሑም ለ19 ዐመት በዘበዙ ይልቀቁ ግን ልጆትን ድረው እስከዛሬ ከጠፋው ገንዘብ አይብስም ፩ ሚሊዮን ፬፻፻ ሺ ብሩ የትሔደ አሳ ጎርጐሪ ዘንዶ ያወጣል እረዱኝ ቁረጡኝ አሑን ነው ምነው ፈሩ

  43. አምሀ እግዚአብሔር ይስጥልን እውነቱ ይህ እና ይህን የመሰለ ነው አንተ ባልከው ላይ የሰንበት ትምህርትቤቱ ይህችን ቤተክርስትያን ለመስራት እራሳቸውን ዝቅ አድርገው የህዝብ ጫማ እየጠረጉ መኪና እያጠቡ ያጠራቀሙት ገንዘብ በፖለቲከኞች እያለቀ በመሆኑ ለህዝበ ክርስቲያኑ መግለጽ ስለነበረባቸው ገለጹ ።የቤተክርስትያኒቱን አስተዳዳሪ ደጋግመው አናግረዋል ጠይቀዋል ነገር ግን ይሰጡቸው የነበረው መልስ ከፉከራ ጋር ማስፈራርያ ከዛቻ ጋር ነው ይህም የምለው በአይኔ በፀሎተ ፍልሰታ በአስተዳደሩ ይሰጥ የነበረውን መንፈሳዊነት የጎደለው መልስ በማየቴና በመስማቴ ነው። እንዲሁም በእለተ ሰንበት 2000ሺ ህዝብ በተገኙበት ላይ ምን ያህል አንባ ገነን ሆነው ያለእፍረት የሰንበት ትምህርትቤት ያዘጋጁት እንዳይነበብ እንዳውም እንደገመትነው አንድ ወንድም የንስሀ ልጃቸው ይመስለናል ንስሀውን ስለነገራቸው ከአንድ መንፈሳዊ አባት የማይጠበቅ ስሙን እየጠሩ አንተ ጉድህን አውቃለው ቆይ እያሉ እውነትን እንዳይናገር ሲያስፈራሩት ታይተዋል ። በውኑ ንስሀን መናገር እውነትን እንዳንመሰክር ማስፈራርያ ማድረግ ይገባልን???? እንዴት ነው ንስሀን ለካህን የምንነግረው????

  44. ደግሞ ቄስስ ተስፋዬማ እውነተኛክርስትያን ነው ቄስስ አስተራይ እና ዶክተር አማረ አንድናቸው ገና ጉድ አለ ለካ ዶክተር ድንግልማርያም መንበር ላይ ቆመው ድንግል ማርያም ጥንተ ተሐብሶ አለባት ካለ ከሐዲጋር አብረዋል ደግሞ በቄስ ተስፋዬ ልትተኩት ያመጣችሑት ቄስስ ሳሙኤል ማለት የመናፍቅ አዳራሽ ሲጨፍር የነበረ ለካ ለዚህነው መንገዱን የምታፀዱት አሑን ግልፅ ነው ሰንበት ትምሕርትቤቱን ዘማርያን መወንጀል አትነግሩንም የሐይማኖት ልዩነትም አለብና ?

  45. በሀሳባችን ብንለያይም ተጨባብጠን እንለያያለን:

  46. ሐና ቃለሕይወት ያሰማልን እማናቅ ስለሚመስላቸው ነው የሊቢያው መሪ እኮ በሴት ነው የሚመራ የነበረው አባገነን የደብረሰላም አስተዳዳሪም እኮ እሱን ሆኑ ሊቀሊቃውንትን እንኳን እኮ አልፈሩም ምናል የተቀረፀው ይለቀቅ እኛም መረጃ እናውጣ ሕዝቡይወቅ

  47. Egzeabher yeker yebelachu enante Hana ena medhanit belachehu yemiteteru yedabilos meleketegoch tinsh enkuan eferet yemayesemachu balegewoch gudegochs enante likun Keses Asteraye lemezelef yetegawu bekatachu newu Tesfaye Mekoya yetaweke ye weyane telalaki mehonu gelete newu yenanten kaleakebayenet yemiyasefelgewu ayemeselegem serawun selemiyawuk abet geta hiye sentu laye tenteletelacheu minewu biberdelachu Keses Samuelem hone Dr. Amare enante endemitawerut aynet selalhonu bekentu afachehun tekefetalachu yehenin yemetasferarubeten video ena maserega eyalachu yemitikebateruten lemin atelekutem yesenbet temarewochem honachu ye enat mezemiran tebelachu yebalege tirekimoch bemin melekiya yehon enante kirestiyan yemetebalut tabot agedachu yenenten yehaset were kalasekedemin belachu setebetebetu ya hulu miemen gud yalachu beweyane telalakiwochu Tesefayena Adisu eyetemerachu mehonu yetaweke newu minale bibekachu betekiresetiyan batebetebtu yedureye menga betekirestiyanuan wero lemaferes makedu tedersobetal kes Hailum lela ye diyabilos telelaki selot laseleyelachu eyalu kesentochachin genzeb atalewu siwesdu zare degmo ke weyane telalakiwoche gare honewu lela zerefiya liyakahedu tenesu hulachehum ye metafrubet ken eruk ayedelem Egzeabher hulunim yayal.

  48. ወይዘሮ ስፍራሽ ለመሆኑ እንዴት ነው አስተረአያ ፅጌ ድንግል ማርያምን ጥንተ ተሀብሶ አለባት ብሎ በኢትዮጵያ አባቶች ከተወገዘ ግለሰብ ጋር ህብረት ያሳየሽው???? የሀይማኖት እጸጽ ካለበት ጋር እረ እባካችሁ ፖለቲካ ያልፋል እግዚአብሔር ግን ህያው ነው ። ሌላው ደግሞ ስለሴቶች ተቆርቁረሽ ተናግረሻል ጥሩ ነው የእግዚአብሔር ቃል ሴት በቤተክርስትያን እንዴት መሆን እንዳለባት ቃሉ ይነግረናል 1ኞ ጢሞቲዎስን 11-15
    ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር ….. በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድላትም …. ሙሉውን አንብቡት እና በደብረ ሰላም ያሉ በአስተዳደር ክፍልም ይሁን በቦርድ ያሉ እንደቃሉ እየኖሩ ነውን??? አበው ካህናትን ወንድሞች ዲያቆናትን እየሰደቡ እያዋረዱ ቤተመቅደስ ገብተው መቀደስ የቀራቸው አይደሉምን?????በሌላ በኩል ቃሉ እንዲህ ይለናል ለቤተክርስትያን ሴት ለማገልገል ምን አይነት መሆን አለባት 1 ጢሞቴዎስ 5 (1 Timothy)
    9፤ ባልቴት በመዝገብ ብትጻፍ ዕድሜዋ ከስድሳ ዓመት እንዳያንስ፥ የአንድም ባል ሚስት የነበረች እንድትሆን ያስፈልጋል፤
    10፤ ልጆችን በማሳደግ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል። በደብረሰላም ለአገልግሎት የተመረጡ ይህን ቃል ያሟሉ ናቸውን??????
    13፤ ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፥ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም። እንግዲህ እህቴ እውነትን እውነት ሀሰትን ሀሰት ልን ይገባናል ምክንያቱም ማቴዎስ 12-:36 እንዲህ ይለናል እኔ እላችኋለሁ ሰዎች ስለሚናገሩት ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል። 37: ከቃልህ የተነሳ ትፀድቃለህ ከቃልህ የተነሳ ትኮነናለህ። ለሚጠፋ ለሚያልፍ ከንቱ ነገር ቤተክርስትያንን አንለውጥ መቼ እንደምንጠራ አናቀውም።

  49. ጆሮ ለመሳብ ደጋገማችሑት

    ፩ ወያኔ

    ፪ አባ መላኩ

    ፫ ቄስ ታደሰ

    ሰማን ሰማን ዶክተር አማረ ለምን እነዚህን ፫ስሞች ፈሯቸው እኔግን እምጠረጥረው ነገር አለኝ እድል አግኝቼ ቄስ አማረን ልጠይቅ ለምንድነው አቡነፋኑኤልን እና ቄስታደሰን የሚፈሩት እነሱን ትተው የራሳቸውን ስራ የማይሰሩት ማውገዝ ስለነሱ ክፉስራ መጠቆም የራሶትን እዩ

  50. ትዝብት
    ማን እንደሖንሽ እናውቃለን ከዲያብሎስጋር ዝምንድና የለኝም እንደናንተም በሰው ላብ አልተዳደርም ገና ለተቀረፀው ነው ስለገንዘቡም እናጋልጣለን አትድከሚ

  51. ትዝብት ብላችሁ እራሳችሁን የጠራችሁ እስቲ አዳምጡን እንዴት ይሆን የአስተራእያ ጽጌ ሊቅነት ድንግል ማርያምን የጌታ ኢየሱስን እናት ጥንተ ተሀብሶ አለባት ብለው ከቅድስት ቤተክርስትያን አስተምሮ ወተው የዲያብሎስን እንክርዳድ ስለዘሩ ????? ህብረታቸውን ከመናፍቃን ጋር ስላደረጉ ሊቅ ያልዋቸው ????ማቴዎስ 10 (Matthew)
    26፤ እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና።
    27፤ በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።
    28፤ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። እንግዲህ አስፈላጊ ከሆነ ድንግል ማርያምን ጥንተ ተሀብሦ አለባት ብለው የጻፉት ፁሁፍ አለኝ post ማድረግ እችላለሁ። እንዴት ኢሳያስ በትንቢት መነፅር የድንግል ማርያምን ንፅሀ ዘር ሆና የቀረችልን መሆንዋን ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ ብሎ የተናገረሉትን እንደሶዶም በጠፋን ነበር…ት/ኢሳ 1:-9 ቅዱስ ገብርኤል ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች መሆንዋን የመሰከረላትን ። እንግዲህ ማን ይሆን ባለጌው???

  52. በሐሳብ አልተለያየንም እውነቱ ይወጣል ካህናትን እናባርራለን እያሉ ማስፈራራት እኮ እውነቱ ከማጋለጥ አያስቆምም አማረ ካሳዬ እኮ የፈሩትን ፈርተው ነው እኮ አይነበብም ያሉት የቄስስ ተስፋዬን በደል ለምን እናዳይናገር ፈለጋችሑ እውነት ዶክተር እውነተኛ ከሆኑ ምንም ሳይፈሩ ይፍቀዱለት እድል ስጡት ይናገር ። ምንም አያስፈራም እኮ ግን እንደ ከዚበፊት እንደተባረሩት ዝም አንልም በሚድያም ቢሖን እንለቀዋለን

  53. መድሐኒትና ሀና

    ምንም የተደበቀ ነገር የለም ቀሲስ አስተርአየ የሚያዉቅትን ፅፈዋል። ዮኦረንታል ኦርቶዶክስ መስክሯል። ምናልባት ስለ ጥንተ ሀብሶ ጉዳይ

    “ስለ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በተሳሳተ መንገድ የሚጠቀሱ ጥቅሶች” በሚል ርስ የተፃፈውን ተመለከቺ። ገፅ 8ና ገፅ 9 ታገኙታላችሁ። ታድያ ለምን ቀሲስ አስተአየ አልተወገዙም? አቡነ ማትያስን ስንት ስቀተቅቷቸው ለምን ጭጭ ብለው ይጠጣሉ?
    ምናልባት ቀሲስ አስተአየ ተወግዘዋል ብለሽ እንዳትተቅሺ። ምክንያቱም አባ ማትያስ le ወር ጊዜአዊ እገዳ እንጂ አላወገዙም። አንድ ሰው ብቻውን ማዑገዝም አይችልም። የተወገዙበት ካለ እንየው?

    http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2009/10/mary_mother.pdf

  54. ምነው አዲሱ ዛሬ በአቢሲኒያ ሬድዮ ላይ ልትሰጠን የነበረው የመፈንቅለ-ቤተክርስቲያን ዜና ሳይተላለፍ ቀረ? ይኼ ማለቂያ የሌለው ዱለታና አድማ መፈናፈኛ አሳጣችሁ እንዴ?

  55. Paying him 5k is not that an issue. I even make more than that. If he is working some where else he can make more. The main thing to me is, is he leading the church based on the word of God or not?i meant based on what we learn from a Holy Bible,

  56. Hana, Medhanit enanten yeyazachehu diyabilos minim yemiberdelet ayedelem setasedabiwoch nachu sele Keses Astreayem hone Dr, Amare yemenager bikat yekachehum yeyazachehu seyetan ke menfesawiyanu gar eyagachahehu newu yekeryebelachu esti aleg yalshewun sehuf letfiwuna yetay tafrebetashalesh enem tikikilegawu merega aleg be gizeyawinet yagedutem Abune matiyas neberu esachewum lik alemehonachewun awukewu afachewun zegetewu kuch belewal anchi sewun lemadenager bememoker yaltebale betaweri kekeletesh besteker minim yemitamechewu neger yelem boardu tenkero sera selesera tekatelachu sem lematefat mekerachihun tayalachu Egzeabher meferedu ayekerem Tabot agedachu yenate trkimrki were kaltesema belachu yemitibetebtu enante nachu kirsetiyanoc ere eferu ebakachu bered belu eferet yenurachu betekiresetiyanin lemaferes yehe hulu erucha betam yasaznal

  57. ስለ ውግዘት ከተነሳ እዚሁ እመሀላችን ተቀምጦ ከመወገዝም በላይ ስልጣነ ክህነቱን ተተገፈፈውን ታደሰ ሲሳይን እስከመቼ ነው ተሸክመን የምንኖረው? ከዚህ የበለጠ ውድቀት ለቤተክርስቲያችን የለም።

  58. የወብዳር ብለሽ የምትጠሪ

    ዶክተር እና አስተሪይ የማውገዝ ስልጣን ማ ሰጣቸው የደብረሰላም አስተዳዳሪ እነዮዲት ጉዲት አርፋችሑ ቁጭ በሉ እናንተ እኮ የቀራችሑ ገብቶ መቀደስ ነው እንግዲሕ ካሕናቱን አስወጡና ግቡ ያን ያህል ነው አማረ ካሳዬ ቤተክርስትያኗን ያበላሿት እናንተ በበላችሑበት ጩሑ ለሐይማኖታችሑ ምንም ግድ የላችሑም እናቃለን ቤተክርስትያኗ ካዝናዋን ባዶ አረጋችኋት ምን ቀራችሑ

  59. በመሰረቱ እነ አስተራያ ጽጌ እና መሰሉቻቸው እነሱ ማን ሆነው ነው ሌላውን ማውግዘዝ የሚችሉት ካህናትን ዲያቆናት ከመቅደሱ እያባረሩ እንዳውም ስናስባቸ በዙሪያቸው ያሉ የከበብዋቸውን ሴቶች መቅደስ ሊያስገብዋቸው እቅድ ያላቸው ይመስላሉ እባካችሁ እናተ በጥቅም የታሰራችሁ ህዝቡን አታውኩት በተለይ ከ17 አመት በላይ ሒሳብ ሹምነቱን አስተዳደሩን የያሽ ወይዘሮ እረ በቃሽ ውረጂ ትንሽ ይዘግንንሽ።

  60. መክሊት በሚል ስም ከላይ የጻፍሽ በጣም የቦዘብሽና ናላሽ የዞረብሽ እንደሆንሽ እንደሆነ ለመረዳት አያዳግትም። (እኔ አንኳ የታደሰ ደጋፊዎች እነ አዱሱ አበበ የጻፉት መስሎኛል)። ታደሰ ሲሳይ እኮ አይኑ የገባችን ሴት በሙሉ ለመዳራት የሚፈልግና ብዙዎችንም በዝሙት ያጨቀየ ወንጀለኛ ነው። ስለሆነም እንችም ከዚህ እንደ ዶሮ ያያት ሁሉ ላይ ልውጣ ከሚል ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንዳለሽ ብታስረጅን ለምን ለታደሰ ጥብቅና እንደቆምሽ ለመረዳት እንችላለን። ታደሰ መውገዙና ከክህነት አገልግሎት መከልከሉ በጣም አስፈላጊ ነበር። እሱን ያወገዙ ካህናት ጀግኖቻችን ናቸው፣እውነተኛ አባትነታቸውን አረጋግጥውልናል። የማወገዝ ስልጣን የላቸውም የምትይው እንኳን የሶስት ካህናት ጉባኤ ይቅርና እንደኔ አየነት ተራ ምእመን እንኳ እንደ ታደሰ አየነቱን በተደጋጋሚ በማስረጃ የተረጋገጠበትን ዜማዊ በመሀይም ቃል ማወገዝና ይችላል። because Taddese is a habitual and repeat offender.

  61. Meklit engdeyawu anchi awugzewa enesu bekat kelelachewu tinishe alemaferesh yemigerem newu megemeriya yehenin ye baltete timiheretena were titesh hayemanoteshin lematenat mokere ewuketu bedenb binor noro eko yehe Kideset Mariyam wusete yetesebesebe serafet set hulu bechifen baltemera neber kedase yekumina Tabot yetagedena yegan terkimrki were ademitun yemitelu gudoch yesenbet temehert bete teblewu betenkol temoltewu yetederagut ye Tesfayen ye Adisu metekemiya mehonachewu alegebachewum betam yemiyasaznu feteretoch nachew hisab yazewa yemitelut lelebnet selaltemeche newu enatewu weregochu gebtachu lemekedes felgachu endewu engi astedadariwuma betekirestiyanua be weyane menga atewererm belewu le ewunet komewal kitel belu engi tenkarawuna ye miserawu bored ayelekim ende ene Tesfaye ena Adisu ayenetu ye weyane telalaki mewaredu ayekerem ke gerba honewu yemiyafagut endene Martha ayenetu zerafi arogitem megaletachewu ayekerem.

  62. አይ hana እባክሽ አንቺ ከቦርዱ ጋር የምትካፈይው ስላለሽ በከንቱ ቀባጥሪ የሰንበት ትምህርት ቤት ይህችን ቤተክርስትያንዝቅ ብለው ጫማ እየጠረጉ መኪና እያጠቡ ገቢ የሚገኝበትን ነገር ሁሉ እያደረጉ እውነትን ሲሰሩ የነበሩ ያሉ ናቸው እናተ ደግሞ ከስር ስር እየቦጠበጣችሁ ቤተክርስቲያኒቱን ባዶ ያስቀራችሁ አይምሯችህ በኢሀፖ በተባለ ሴጣን የተደፈነ ናችሁ።

  63. እኔ የሚገርመኝ ሰው ካልፈለጋችሁ ጥቅም ካልቀረባችሁ ለ18 ዓመት ስልጣን አለቅም የሚያስብ ነገር ምንድን ነው????? ደግሞ አለማፈራችሁ ዛሬ ደግሞ የሰማሁት ሳሙኤል የተባለ በመናፍቃን አዳራሽ ምን ሊያረግ ሄዶ ነው ከመናፍቃን ጋር አንድነት እንዳለው በመድረካቸው ሲገልጽ ማስረጃ ያላቸው ሲናገሩ ሰማን እናተ የማሪያም ቤተክርስትያን ቦርዶች ወዴት ወዴት ነው አካሂያዳችሁ ከመናፍቃን ጋር አንድነት አለኝ ከሚል ሰው እንዴት ነው እንዲሰብክ እንዲዘምር መድረክ የሚሰጠው?????? አይ ከዚህ የከፋ ምንፍቅና አለ እንዴ መቅደስ መግባት በቀራቸው ሴቶች በነስማይጠሬ ብዙ ይሰማል።

  64. What is going on with the Tewahido children? Why do you think weyane took the rightful patriarch Abune Merkorios and put Poulos who was aTigre and when Poulos died again weyane put Matios who is a Tigre . Now that is politics ok! Why do you keep saying politicians, politicians and EPRP. Unless you guys are weyane you shouldn’t mention it, weyane is the culprits period. Addisu Abebe is working hard to present this church to Matios as እጅ መንሻ to get the land he is killing himself for the church in Akaki. He is doing any thing for his retirement.

  65. Thank you so much to expose the whole situation in our orthodox church. The Atlanta Mariam church was so good and peaceful. The so called priests are creating problems. They are paid by the people. The board and including the participants should be strong. Who ever creates problem should be fired. And move on. Please, do not wait until the problem is chronic.

  66. መጀመሪያአውጋዦቹ ብታቂ አማረካሳዬም የተወገዙ ናቸው ምናለ ወሮ ሐና ነኝ ባይዋ ከአንድ ክርስትያን የማይጠበቅ ከአንደበትሽ የሚወጣው እኔ ቄስ ታደሰን አላቃቸውም ባቃቸው አንቺ ያልሽውን ለመድገም አልፈልግም እኔ ወላጆቼ በምግባር በሐይማኖት ኮትትኩተው ነው ያሳደጉኝ እንዳቺ ዋልጌ አልወለደኝም አላሳደገኝም ጉግ ማንጉግም አይደለሑም ንፁሕ ኢትዮጵያዊት እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይኝ እኔ ኢሐፓም ቦርድም አይደለሑም እምነቴምን እንደሚጠብቅብኝ አቃለሑኝ ይብላኝ ለወለደሽ እና እናት ከሖንሽ ለልጆችሽ

  67. መክሊት እህቴ እራሷን hana ብላ የጠራች ምግባረ ብልሹ አንድ እውነት የሌላት የቤተክርስትያናችንን ካህናቶች ላይ ግፍ እየሰሩ ሌላ ለማውገዝ ሲሄዱ እነሱ ለሚሰሩት ግፍ ማን ያውግዛቸው??????

  68. እነ ስምአይጠሬ እኮ በጨካኙ ስም ለመስጠት አስቸጋራ በሖነብን የቤተክርስትያኑ አስተዳደር ቄስ አማረ ካሳዬ እና ግብራበሮቻቸው ቄስ ኤልያስ እንዲሑም ዲያቆን ጥበብ ዲያቆን የኋለዕሸት ማይክራፎን አብሪ አጥፊው እና ለጥቅም መሐል መንገድ ላይ የቆሙ ለሐይማኖት ግድ የሌላቸው እነ ዮዲት ጉዲት ትጓደድ እና ወሰኔ እነ ውልታ እንዲሑም በቤተክርስትያን በአዛውንቶች ጥቅም ተጋሪ ወሮ ሐረገወይን እና ሌሎቹሞ ዋናው ዶክተርነኝ ባዩ የቦርዱ ሊቀመንበር ህዝብ ይወቃችሑ

  69. እህቴ መክሊት

    አንጀቴን አራስሽው ቃለህይወት ያሰማልን እውነት እውነት ነው

  70. እውነት ይሔን በሱባኤ እናወጣዋለን እናምናል እግዛብሔር ይረዳናልአባቶቻችን እና ፍቅር ሕብረትን ይጠብቅልን ።

  71. menew Eresachehut Ye Hizab Ayazena Astedader AtO Tadessens Eresachehut Wanaw Esum New Lelam Semachewen Yaltekesu Abew AbaToch Kahenat Ena Daykonat Endaymselachehu Yehe Hulu Yemtaut Derama Enatenm Kenu Aytawekem Yedersal Le Kerachehu Ena Lewenet Kumu

  72. እንክርዳዱ ከስንዴው ይለያል ወደ እሳት ይጣላል። ኢሀፖ እና በህዝቡ ላም የሚቀልዱ ከበተክርስቲያናችን ይለያሉ ። እግዚአብሔር የዘገየ ቢመስልም የሚቀድመው የለም ።ድንግል ቤትዋን ታፀዳለች ።እግዚአብሔር ለንስሀ ግዜ ቢሰጣቸው መቅደስ መግባት ቀራቸው።

  73. እግዛብሔር እረ በጣም ዝም ቢላቸው እኮ የለም ብለው ተዳፈሩ መቅደስም ይገባሉ እውነት ሴቶቹ እረ ገብተዋል በምስራቅ በር አይፈሩም ለዚህ እኮ ነው ቄስ አማረ የሴት ጋርድ ያላቸው እና አቶ ፍሬው ደግሞ የቅዳሴ ስርአት የማያቅ በቅዳሴ ሰአት መልአክቶችን እየረገጠ ሙሉ ቤቱን ሶሞሶማ የሚሮጥበት የዶክተር በትረሙሴ ያዥ

  74. እውነት ፃድቁ አባቴ የደብረአፅቦ የኢትሳ አንበሳ ተክልሐይማኖት ይሔ አልበገር ያለው አንድሰው እስኪቀር እዋጋለሑኝ የሚለውን እልሕ አይሉት ድርቀት ዲያብሎስ ከአፀደ ቤተክርስትያን አውጡልን ።

  75. የአሜሪካንን መንግስት አታለውና ቀላምደው ስደተኛ ነኝ ብለው የፖለቲካ ጥገኝነት ያገኙትና አውግዘዋቸው የነበሩትን አቡነ ጳውሎስ እንደገና ጉቦ ከፍለው ጫማ ስመው የታረቁትና የማይመጥናቸውን የጵጵስና ማእረግ ያገኙት አባ መላኩ ናቸው በደብረ ሰላም ደብር ውስጥና በሌሎችም ቤተክርስትያኖች ውስጥ ብጥብጥ እያካሄዱ ያሉት። እሳቸው ከወያኔው ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ሁለት ተግባሮችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ። 1) ከተቻለ በውጭ የሚገኙትን ቤተከስቱያኖች በሙሉ በርሳቸው አስተዳደር ስር ማዋል 2) ካልተቻለ ደግሞ በውጭ የሚገኙ ቤተክርስቲያኖችን
    ማበጣበጥና ቅዳሴውንና አገልግሎቱን ማስተጓጎልና ወይንምማዘጋት ናቸው። እነዚህን መሰሪ ተልእኮ የተሰጣቸውና የተለያየ ጥቅሞች ማባበያ ቃል የተገባላቸውን ምእመናንና የሰበካ ጉባኤ አባላትን በየደብሩ ያጠመዱ ሲሆን አብዥኛው ከእነሱ ጋር የሚሰለፈው ግን ሚስጥሩ ያልገባው የዋሁም ምእመን ነው። በደብረ ሰላም ደብር ውስጥ ከምእመናን መካከል አዲሱ አበበ ካህናት ወገን ደግሞ መምህር ተስፋዬ መቆያ ይገኙበታል። ሌሎች የራሳቸው የሆነ ኩርፊያ ያለባቸው እንደ ዶክተር አክሊሉ ሃብቴ በእለት ብስጭት ተነስተው ተደራጅተው በአባ መላኩ በሚመራው የቤተክርስቲያን አፋኝ ቡድን ውስጥ ሳያውቁት ተጠልፈው ገብተዋል። አሁንም ካፈርኩ አይመልሰኝ ማለታቸውን ትተው በአድማና በብጥበጣ ተግባር ውስጥ በስተት የገቡ ምእመናኖች ቤተክርስቲያናቸውን ማፍረሳቸውን ትተው ወደ ህሊናቸው በህዝብ ከተመረጠው የቤተክርስተያኑ ቦርድ ጋር አብረው ገንቢ አስተዋፆ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል።

  76. አይ menber በመጀመሪያ አንቺ ምንም የማታቂ ጋጠወጥ መሆንሽን ለመረዳት የጻፍሽው ይገልፅሻል። በመቀጠል ይቅርታ መጠየቅ አንዱ የቅድስና ምልክት መሆንሽ ያሳዝናል ይቅርታ መጠየቅና ይቅርታ ማድረግ መፅሀፍ ቅዱሳዊ መሆኑን ለመረዳፍ አፍሽን አይንሽን አይምሮሽን ተጠቅመሽ መፅሀፍ ቅዱስ አንብቢ ። ውሻ በበላበት ይጮሀልና አዩስደንቅም አፍሽ እግዚአብሔር በአከበራቸው ላይ ብታላቅቂ እግዚአብሔር ፊት ስትቀርቢ ይዘጋል ሺ ዓመት አትኖሪም ። ይልቁን እስካሁን የዘረፈችሁት ይበቃችኋል የተጠየቃችሁት ሌላ የምትቀባጥሩት ሌላ ይደብረሰላም ህዝበ ክርስቲያን ሰልችቷችሀል ።

  77. መንበረ ብለሽ ስምን መልአክ Yያወጠዋል አሉ ያንቺን ግን ዲያብሎስ ነው በአቋራጭ ያወጣልሽ

    ስድብ የዳቢሎስ ነው እኛ የደብረሰላም ምእመን እኮ እውነቱን አወቅን አንቺ ዶር አክሊሉ የደረሱበት እድሜ ሳትደርሺ አፍሽ ነቀርሳ ይተክልብሻል ምክንያቱን ታቂዋለሽ

    ደግሞ መጋቢ ተስፋዬ መቆያ ምን ያድርጋችሑ የሱ ፋይል ሕዝብፊት የቀረበለትማ መልሱን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እመነት ተከታይ ለሖኑት በሙሉ እተዋለሑኝ ኢሐፓ ፡ኢድዩ እና ኢሰፓ እና እነዮዲት ጉዲት ተነው ይጠፋሉ አምናለሑኝ ።

  78. እውነት፡የምናውቀው፡ነው፡ይምንናገረው፡የምንጸፈው?
    መጀመሪያ ከምን አሳብ፡ተነስተክ፡ነው፡የጻፈክው?እውነቱ፡ለማንንም፡የተደበቀ፡አይደለም?
    ምክንያቱም፡እኛ፡የድንግል፡ማሪያም፡ለጆች፡እንታገሳለን፡እናስተውላለን፡ዛሪን፡ግን፡ለእምነታችን፡ለእውነት፡መስዋት፡እንከፈላልን
    እውነቱን፡ከድንግል፡ጋረ፡ሆነን፡ጅመርነው።
    *የስንበት፡ትምህርት፡በት፡አገልጋዮች፡ምንድነው፡ያጠፉት?
    *አባታቶቻችንስ፡ምንድነው፡ያጠፉት?
    መልስክ፡በርግጠኝነት፡ሃይማኖታዊ፡መልስ፡የለክም?ምክንያቱም፡አንተ፡የፈጣሪ፡ክብር፡ስለጎደለክ፡በማታውቀው፡ነገር፡ነው፡የአባቶችን፡የአገልጋዮችን፡ስም፡የምታጠፋው?
    አንተ፡ምን፡ያህል፡ብታውቅ፡ነው፡ሰለነሱ፡የምታውራው?መረጃ፡አለክ?
    የቦርዱን፡ስህተቶች፡ለመሽፈን፡ዛሪ፡በናንተ፡መንገድ፡መጡ፡ወደ፡ፖለቲካ፡ለማዞር፡አገልጋዩ፡/ህዝቡ/ አያውቅም፡ተብሎ፡ነው?
    መልሱ፡ግን፡እናውቃለን!ዛሪም፡አባታችን፡ሰለ፡ስላም፣ፍቅር፣እርቅ፡ነው፡የሚያሰተምሩን።እሳችውም፡ፈጣሪን፡አክብርው፡የሚኖሩ፡አባት
    ናችው። ትንሽ፡አሳብ፡ልስጥክ
    በድንግል፡ማሪያም፡ስም፡ንግድ፡የሚነግዱ፡እነማን፡ናችው?
    ዘመናዊ፡መኪና፡የሚቀያይሩት፡እነማን፡ናችው?
    የገዳመ፡ተ/ሃይማኖት፡ብር፡እነማን፡ጋር፡ነው?……መልሱን፡ካንተው፡ልጠብቅ፡ካለሆነ፡መለሱን፡በስፊው፡አቅርባለው

  79. ካሉ

    ቃለህይወት ያሰማልን

    እውነት መሰዋትነት ታስከፍላለች እንከፍላለን ።

  80. Hana, Meklit, Kalu lelochim meselochahehu yemitawerut hulu beseyetan temertachehuna seyetan aderobachehu selehone betam tasaznalachu lemehonu yetegawu papas newu egzeabher yemeretewu be 30 shih dollar yegezawun diyabilos Fanuelen newu maferiyawoch nachu minale sewu laye batenteletelu eneman endehonachunyemitesefut yemayetawek yemeselachuhal gizewu yeseletene newu bedenbe eyetemezegebachu newu legizewu kebateru gedelem endekebet letenedutena letatalelut yemitimokerut hizeb eyaywekachu newu boardu lemine tenkero sera lega lelebnet altemechenim belewu behayemanot sem linegdu yetenesutem bihon Egzeabher eyagaletachewu newu betekiresetiyanun lemaferes yetenesachu hulu ayasakalachehum ewunetega kirestiyanoch betehonuma noro kidase yeker asekertach yenanten trkimrki were lemawurat awudemheret atewetum neber tabot agedachu setechohu atewulum neber ye Egzeabhern hayalinet bitawuk noro senesereat yenorachu neber betekiresetiyanuan legel tikem magega lemadereg alemech selalachu lemasebetebet be diyabilos telkachu memtatachihun eyasayachu newu Egzeabher libona ysetachu mechem lib yelachu enante kehadiwoch nachuna.

  81. አይ tarike እንዴ እንዴት እና እንዴት ነው ነገሩ የምን መሸፋፈን ነው ወዲህ ወዲያ እያላችሁ አታምታቱን የደብረ ሰላም ቤተክርስትያን ምእመናን እና የሰንበት ትምህርትቤቱ ጥያቄ ፖለቲከኞች ቤተክርስቲያናችንን ለግል ጥቅማቸው አላማቸው ማስፈፀሚዩ አደረጓት ስለዚህ ይውረዱ እነስማይጠሬ እነዮዲት ጉዲት መቅደስ ሊገቡ የተዘጋጁ አሁን ደግሞ ጵጵስናውንም ለመረከብ የተዘጋጃቹህ ትመስላሉችሁ ።አለማወቅ።

  82. ደግነቱ የዶክተር ጋሻጃግሬዎች ሚስታቸው እግዜር ይስጣት ወ/ሮ ነገደ ባታገቢያቸው እኮ አለም ትጠፋ ነበር ደግሞ ጳጳስ ሖነው ቤተክርስትያን እምነታችንን ያጠፉልን ነበር ለእግዛብሔር የሚሳነው ነገር ምንም የለም አሑንም ዝናሽን እንሰማለን ይሰሙሻል ስለዚ በድንግል 18 አመት በልታችኋል ይበቃችኋል ሕፃን የሰጡትን ይቀበላል እንዺሉ አስለቂቅልን

  83. All these hostility is directed againist Dr. Kesis Amare because of the fact that he rejected TPLF spy Abba Melaku. Addis is Abba Melaku’s point person to take over our church. Please Ethiopians wake up and know your enemy, Woyane + Abba Melaku + Addisu.

  84. mehabere seyetanoch yemetsedbachew abatoch memanane betekerstiane meserto tebekach enanete tenanet metachu megelgele fanta tsadaby,asadaje seme awchy yewayane tellakiy honachu

  85. ይቅር ይበልህ/ሽ እኛ አባታችን ቀሲስ ኅይሉን ስናውቃቸው እንኳንስ እንዲህ ያለውን ነገር ሊያደርጉ ይቅርና የራሳቸውን ገንዘብ ሳይቀር ጨምረው ነዳያንን የሚመግቡ ፤ቤተክርስቲያንን የሚረዱ፣ ቅዱሳንን የሚዘክሩ፣ ችግረኞችን የሚረዱ፣ ካህናትን የሚመግቡ፣ የፍቅር፣የትህትና እንዲሁም የትእግስት መምህር የሆኑ ሰለቸኝ ደከመኝ የማያውቁ በቤተክርስቲያን ጉዳይ ሲመጡባቸው ደግሞ ወደኋላ የማይሉ ቆራጥ የሃይማኖት አባት መሆናቸውን ነዉ ።ለዚህም በኢትዮጵያ የደብረ አሚን ተከለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በዚህም ሀገር በርካታ ምእመናን ምስክራቸው ነን። የዛሬን አያርገውና የዛሬ ሁለት አመት ዶ/ር አማረ የሰጡት ምስክርነት በራሱ በቂ ነው። በርግጥ ቀድሞ በጌታችን ላይ እንዲሁም በቅዱሳን ላይ ሀሰትን ሲያሰራጭ የነበረ የሀሰት አባት ዲያቢሎስ ዛሬም በአባታችን ላይ መነሳቱ ባይገርምም፣ ለእንደዚ አይነቱም መልስ መስጠት ባያስፈልግም ፤ የዋሀን የቤተክርስቲያን ልጆች እውነተኛ መረጃ ይኖራቸው ዘንድ ይህንን ፅፈናል።

  86. አባታችን ቀሲስ ኀይሉ ጠላት ቢያወራ እኞ አባታችን ማን እንደሆኑ ስለምናቅ አይደንቀንም ጠላት ዲያብሎስ በፆም በፀሎት የሚያሳድደውን ከመዋጋት ድንግልን መከታ ያደረገን ራእይ 12 (Revelation)
    17፤ ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ። ስለዚህ ቃሉ ቀድሞ ስለነገረን ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ግድ ነው ። እነርሱ ግን ዛሬም ነገም ከአባታቸው ከዲያብሎስ ናቸው ቃሉም እንዲህ ይላቸዋል ዮሐንስ 8 (John)
    44፤ እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።።

  87. Meri geta deabilos Workneh is the liar and non god believer as well. He only cares to get his hand on the church money.He opened a church in Woodbridge, VA to make money unfortunately it never happened.

  88. ማንነህ ማንነሽ በቀሲስ ሀይሉ(kess Hailu) ስም የምትጠቀም[የምትጠቀሜ] አቁሙ!

    ሀስት ነገር ነው የምታስተላልፍት እና አቁሙ!

    ቀሲስ ሀይሉ መልካም የፍቅር..የሃይማኖት አባት ናቸው!

    ስለእውነት የምታውቀ ነገር ካለ እራሳቹን ሆናቹ ተናገሩ,የንፀህ አባቶችን ስም ለማጥፉት የተነሱትን እናውቅቃቹዋለን ህሌና ጎዳሎዎች

  89. Ya you have ugly mind & tekure lebe (heart)
    Kess hailu tebak melaeket alhew,ante gen yesetane (dablose)mehweha nak (nashe)

  90. kesis hailu\ብለሽ\ክ፡የምትፅፌ\ፍ እንዳተ\ቺ፡የቆሸሽ፡\የበስበስ\ስዉ፡ከምሆን፡እራሴን፡አጠፉ፡ነበር፡የአንተ\ቺ፡አባት፡ሌባ፡እናትክ\ሽ፡ሴተኛ፡አዳሪ፡ከሆነ፡ቤተስብ፡የተፈጠ፡ቆሻሻ፡ሠውእንዴት መልካም የሆ ነነገር ይወጣዋል፡አዉንም ቦርዱ ሌባ ነዉ፣ሌባ፣ሌባ፣ሌባ,,,የደፈረሰዉይጠራል!ልብያለዉ፡እንደ፡አባታችን፡አልስርቅም፡ማለት፡ነው።

  91. ይቅር ይበልሽ ይበልሕ

    የአባታችንን ስም በአደፈ እጅሽ ወይም እጅህ አትጠቀሚ አትጠቀም ለነገሩ ከዲያቢሎስ እና አሳዳጊ ከበደለው ምንም አንጠብቅ ም

  92. እሩቅ አትሒዱ በቄስስ ሐይሉ ስም የሚፅፈው ማን እንደሆነ ይታወቃል ከዝንብ ማር አይጠበቅም አየናቸው የፊታችን እሑድ እኛ እንዳንገባተከልክለን በፖሊስ ከመለሱን ውስጥ ውልታ ትኋደድ በቅዳሴላይ የሚሮጠው የቦርድ ተመራጭ አቶ ፍሬው እንዲሁም የቄስ አማረልጅ በምን ምግባር እንዳሳደጓት አየን እኮ ትልቅሰው የማያከብሩት አባቷ ፍሬ አዋቂ ስታዋርድ አየን አንደ እዚህ አገር መንገድ አዳሪ ነው የምትሳደበው ታዲያ ምነው ከዝንብ ማር ጠበቅን

  93. Meklit, anchi sid adeg yesetgna adari lij. Ene kanchi gara seme kemigengne erasen batefa yeshalegnal. You are that half lady loser.

  94. አይ እነ ዮዲት ጉዲት እረ ትንሽ እፈሩ ደንግጡ እግዚአብሔርን ለንስሀ ግዜ ቢሰጣችሁ እንደፈርኦን ደነደነ ልባችሁ ማን ያውቃል ነገ መቅደስ ገብታችሁ እንቀድስ የምትሉ አይነት ነው አያያዛችሁ ። የእግዚአብሔርን ትእግስት ንቃችሁ በፍርድ ወንበር እንቀመጥ አላችሁ ።እናተ እረክሳችሁ መቅደሱን በጫማ አስረገጣችሁ ።እረ ይህ ልትሞቱለት የተነሳችሁለት ዶላር ስንት አመት ያኖራችሁ ይሆን ??? ምነው ስንት ገንዘብ ያላቸው ያችን ሞት ዶላሩ አላስጣላቸው መጠራት አለ ምን ይሆን መልሳችሁ?? ሶፎንያስ 3 (Zephaniah)
    2፤ ድምፅን አልሰማችም፥ ተግሣጽንም አልተቀበለችም፤ በእግዚአብሔርም አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።
    3፤ በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፤ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው። እባካችሁ የትንቢት መፈፀሚያ ሆናችሁ በውስጥዋ የተመሸጋችሁ እንደ መምሬ አማረ ካሳዬ እና አስተራዩ ጽጌ የመሰላችሁ ሶፎንያስ 3 (Zephaniah)
    4፤ ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፤ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል።
    5፤ እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፤ ክፋትን አያደርግም፤ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።።

  95. እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ። ኦሪት ዘፍጥረት: ምዕራፍ 6 ቁጥር 5-6
    እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ። ኦሪት ዘፍጥረት: ምዕራፍ 6 ቁጥር 5-6
    እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ። ኦሪት ዘፍጥረት: ምዕራፍ 6 ቁጥር 5-6
    ጆሮ ያለው ይስማ!!!!!!!!

  96. ዉይይይ… ምነው ማክሰኞ አልደርስ አለች
    ትንቢት!!!
    ከሳሽ ተዋርዶ ይሸኛል ፍሬው ፀጉር ያበቅላል ቀሲስ አማረ ካሣዬ ከነቦርዴ ቤተክርስቲያንን ይናፍቃሉ አዳሜ እዚህ የምትንጫጪ ሁላ በቂጥሽ ቁጭ ትያለሽ ሌላ ምንም የምለው የለኝም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*