ቀጣዩ ትግል አድዋዎች እና ወላይታዎች መካከል ይጀመራል :: (Daniel Tefera)

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በድጋሜ የኢህዴግ ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ አሉ፡፡ ይህ ማለት ቀጣዩ ጠ/ሚ ናቸው ማለት ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ባስቀመጠው ‹‹መስመር›› መሰረት ግለሰቦች መቀያየራቸው ትርጉም የለውም፡፡

እኔ ግን የአቶ ኃይለማሪያም መመረጥ አንድ ነገር ጫረብኝ፡፡ ከዓመት በፊት ዛሬ በግፍ እስር ላይ ከሚገኘው ዳንኤል ሺበሺ ጋር ወላይታ ሶዶ ሄደን ነበር- ለስራ ጉዳይ፡፡ ወዲያው ግን የሄድንበት ስብሰባ ሲጀመር እንደወንበዴ ታርጋ አልባ በሆኑ ባለሞተሮች ተከበን ወደ እስር ቤት ተወሰድን፡፡ ትልቁ ቁምነገር ወደ እስርቤት መወሰዳችን አልነበረም፡፡ ፈገግ የሚያሰኘው ወደ እስር ቤት የተወሰድንበት ሰበብ ነው፡፡ በአጭሩ ለአንድ ሙሉ ቀን ያሳሰረን ሰበብ ተቃዋሚዎች ወላይታን መርገጣችን ነው፡፡

አሳሪዎቻችን ቃል በቃል እንዲህ አሉን፡-

‹‹ልጃችን ስልጣን ላይ ሆኖ የወላይታን ምድር ተቃዋሚ አይረግጣትም!!!›› በወቅቱ የተሰማኝ ድንጋጤ የለቀቀን በቅርቡ ነው፡፡ ተረኛ ገዥዎች እኛ ነን እያሉን ነበር፡፡ ይሄ በአጠቃላይ ለፍቶ አደሩንና ባለውብ ባህሉን የወላይታ ህዝብ ባይወክልም ገዥነት መንፍስ እያቆጠቆጠ እንደነበር አመላካች ነው፡፡

አድዋችም እንደዚህ አይነት ስሜት ነበራቸው አሉ፡፡ ልጃችን ስልጣን ላይ እያለ ወንድ የሆነ ተቃዋሚ አድዋን ይረግጣል የሚል፡፡ ኃይለማሪያምን በህወሃት መልካም ፈቃድ የሚዘወሩ ናቸው የሚለውን ወላይታዎች የሚቀበሉት አይደለም፡፡ ወላይታዎች እየተነቃቁ ነው፡፡ ልጃችን ስልጣን ላይ ነው እያሉ ነው፡፡ መስፋፋት እየታየባቸው ነው፡፡ ስለዚህ ቀጣዩ ትግል የሚጀምረው በአድዋዎችና ወላታዎች መካከል በሚደረግ የበላይነትን ለመጎናፀፍ የሚደረግ ትግል ይመስለኛል፡፡
ለማንኛውም ሃይሌን ጌታ ይርዳዎት እላለሁ፡፡