ቀጣዩ ትግል አድዋዎች እና ወላይታዎች መካከል ይጀመራል :: (Daniel Tefera)
አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በድጋሜ የኢህዴግ ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ አሉ፡፡ ይህ ማለት ቀጣዩ ጠ/ሚ ናቸው ማለት ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ባስቀመጠው ‹‹መስመር›› መሰረት ግለሰቦች መቀያየራቸው ትርጉም የለውም፡፡
እኔ ግን የአቶ ኃይለማሪያም መመረጥ አንድ ነገር ጫረብኝ፡፡ ከዓመት በፊት ዛሬ በግፍ እስር ላይ ከሚገኘው ዳንኤል ሺበሺ ጋር ወላይታ ሶዶ ሄደን ነበር- ለስራ ጉዳይ፡፡ ወዲያው ግን የሄድንበት ስብሰባ ሲጀመር እንደወንበዴ ታርጋ አልባ በሆኑ ባለሞተሮች ተከበን ወደ እስር ቤት ተወሰድን፡፡ ትልቁ ቁምነገር ወደ እስርቤት መወሰዳችን አልነበረም፡፡ ፈገግ የሚያሰኘው ወደ እስር ቤት የተወሰድንበት ሰበብ ነው፡፡ በአጭሩ ለአንድ ሙሉ ቀን ያሳሰረን ሰበብ ተቃዋሚዎች ወላይታን መርገጣችን ነው፡፡
አሳሪዎቻችን ቃል በቃል እንዲህ አሉን፡-
‹‹ልጃችን ስልጣን ላይ ሆኖ የወላይታን ምድር ተቃዋሚ አይረግጣትም!!!›› በወቅቱ የተሰማኝ ድንጋጤ የለቀቀን በቅርቡ ነው፡፡ ተረኛ ገዥዎች እኛ ነን እያሉን ነበር፡፡ ይሄ በአጠቃላይ ለፍቶ አደሩንና ባለውብ ባህሉን የወላይታ ህዝብ ባይወክልም ገዥነት መንፍስ እያቆጠቆጠ እንደነበር አመላካች ነው፡፡
አድዋችም እንደዚህ አይነት ስሜት ነበራቸው አሉ፡፡ ልጃችን ስልጣን ላይ እያለ ወንድ የሆነ ተቃዋሚ አድዋን ይረግጣል የሚል፡፡ ኃይለማሪያምን በህወሃት መልካም ፈቃድ የሚዘወሩ ናቸው የሚለውን ወላይታዎች የሚቀበሉት አይደለም፡፡ ወላይታዎች እየተነቃቁ ነው፡፡ ልጃችን ስልጣን ላይ ነው እያሉ ነው፡፡ መስፋፋት እየታየባቸው ነው፡፡ ስለዚህ ቀጣዩ ትግል የሚጀምረው በአድዋዎችና ወላታዎች መካከል በሚደረግ የበላይነትን ለመጎናፀፍ የሚደረግ ትግል ይመስለኛል፡፡
ለማንኛውም ሃይሌን ጌታ ይርዳዎት እላለሁ፡፡
Funny ወላይታና አድዋ ለስልጣን ሲጋጬ አማራ ዳኛ ሊሆን…..
ኣንዳንዴ የምንለውንም ማወቅ ተገቢ ነዉ እላለሁ።
ትርጉም የማይሰጥ ኣነጋገር፤ ያስተዛዝባል።
ልክ ነህ የደደብ ወያኔ መገለጫው ጎጥ ነው
ትግራይ ሊያሥገነጥል የሚያሥችላት ደረጃ ደርሣለች ለምሣሌ የተከዜ ሀይል ማመንጫ ፤ ከጅቡቲ መቀሌ የመኪና መንገድ ፤ መሠቦ ሥሚንቶ ፤ አልመዳ ጨርቃጨርቅ ፤ መቀሌ ጅቡቲ የባቡር መሥመር ዝርጋታዎች በጥቂቱ ለግንዛቤ ማሥጨበጫነት ይሆን ዘንዳ ብዬ ነው ይህ ነው ነፃ ማውጣት የጫካው አጀንዳ ሌላው ለም የሚባለው ክልል ጡት እንደተነፈገ ጥጃ ቀጭጮ የሚታየው ይህ ኢፍትሀዊ ዘረኛ ድርጅት ሥርአት መገለጫ ነውና ቀጣይ የሥርአቱን ችቦ ከነደሙ ሣይታጠቡ ተረከቡ ፌሽትያ ነው ለወያኔ እሣቸው የሙሥናውን መረብ ለመበጣጠሥ ተዘጋጅቻለው ብለዋል የማንን ትኩረት ለማግኘት ነው ንብረት አሽሽተው ጨርሠዋል የሦዶውም ሊሥትሮ ተሥፋውን ለወላይታው አሥረክቧል።
ኢትዬጵያ ሆነሻል ኦሮማይ።
ውጤቱም 11 ፥ 0 ነው
ይህ ሥልታዊ ማፈግፈግ በ9 የወያኔ ደቀመዛሙርት ምሪት ወደ ወላይታ አምርቷል ይህ የወያኔን መዳከም ያሣያል ወይም ይህን 20 ቀን የፈጀ ሁሉም ኮፍያቸውን ሢያነሡ ግንባራቸው እንደ ብር የሚያንፀባርቁ ሆነዋል እናም በመጨረሻ ሠአት” ሠብ የለን እዩ ” ሠው የለንም… አይናቸው ፈጦ የግድ ለወላይታ ተሠጠ በሙታኑ ኑዛዜ መሠረት ቻው…. የትግራይ ሙታን ሠማእታት መንፈሥ የሚመራው ፈረሥ የጋሞ ገደል ገብቷምል ኦሮማይ።
የኢትዬጵያ ጉዳይ እሥካሁን አሸንዳይ ….ዳይ ዳይ ….!!!
እየተባለ ሢጨፈር 24 አመታት እንደ ከበሮ ተደልቀናል ግን ምን አተረፍን ….?
አሁንም ህዝብ ወገን ተርቦ ሰለሜ …..ሠለሜ ሊጨፈር ነው ከሠለሜ መሥመር ያፈነገጠን በቀበቶ ተገርፎ ይታለፍ ይሆን? እንዳሉት ከሆነ አቶ ሀይለማርያም ይህን ልክፍት በፀሎት ማላቀቅ አለብኝ ብለዋል ጌታ የሡሥ ይርዳኝም ብለዋልለፖሥተሩ።
ኢትዬጵያ እንደኮሦ የተጣባት የወያኔ ዘረኝነት ፖለቲካ የጫሞን ወንዝ ይሻገር
ይሆን ወይሥ አቶ ሀይለማርያም መድሀኒቱን ከጫካው ቆርጠው ይሽሩ ይሆን?
gondere recist nazi.son of minelik the killer of brave oromo.