አርቲስት ደበበ እሸቱ የተረጎመው መፅሐፍ በጣይቱ የትምህርትና የባህል ማዕከል ተመረቀ::

አርቲስት ደበበ እሸቱ የተረጎመው መፅሐፍ በጣይቱ የትምህርትና የባህል ማዕከል ተመረቀ::

አርቲስት ደበበ እሸቱ ተረጎመው መፅሐፍ በጣይቱ የትምህርትና የባህል ማዕከል ተመረቀ::

“የአማራ ገዢ መደብ” የሚለውን የፈበረከው ማነው?
የጎሳ ጥላቻን የፈጠረው ማነው?
ኢትዮጵያ እንድትጠፋ አሁን የሚያምሳትን ችግር የጠነሰሰው ማነው?
…………………………………………………………….
የነዚህን ጥያቄዎችን መልስ አርቲስት ደበበ እሸቱ ከተረጎመው መፅሐፍ ታገኙታላችሁ:: መፅሐፉ በዕለተ አርብ 28/08/2015 Maryland በሚገኘው ጣይቱ የትምህርትና የባህል ማዕከል ተመረቀ::

– አርቲስት አለምፀሐይ ወዳጆ ከአንጋፋው የሙያ ባልደረባዋ ደበበ እሸቱ ጋር የነበራትን ትውስታዎች እያካፈለችን በሳቅ ስታስፈንድቀን ሌሎችም አንጋፋ አርቲስቶች እንዲሁ ብዙ የሚገርሙና የሚያስቁ ትዝታዎቻቸውን አካፍለውናል::


– እንዲሁም የመፅሐፉ አሳታሚ;- የፀሐይ አሳታሚ ድርጅት ባለቤት አቶ ኤልያስ ወንድሙ ስለመፅሐፉ አጠር ያለ መግለጫ ሰጥቷል :: ከዚህም ንግግሩ ውስጥ የማይረሳው የአሁኑን የሀገራችንን ችግር መሰረቱን ለማወቅ ትውልዱ ይህን መፅሐፍ እንዲያነብ እንደሚያስፈልግና እሱም የርሱን ድርሻ ለማበርከት የተወሰኑ ቁጥር ያለውን የመፅፉን ኮፒ በነፃ ኢትዮጵያ እንዲገባ እንደሚያደርግ ተናግሯል :: ይህውም ትውልዱ የችግሩን ስር አውቆ መፍትሄ ለመፈለግና ሀገሪቱን ካለችበት ከችግር ለማውጣት እንደሚረዳ አክገንዝቧል ::


– መፅሐፉ ሃምሳ አራት ገፆች ያለው ዋጋውም ዝቅተኛ ነው;; ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ እንድትጠፋ የጥላቻ ባሩድ የቀበሩትና ቅመሙን የቀመሙበትን መርዝ በዚሁ አነስተኛ ገፆች አዝሏል ስለዚህ እኔም ገዝታችሁ እንድታነቡ እመክራለሁ::

ጣይቱ ብጡል