እነ ሃብታሙ አያሌውን ለመፍታት/ከበር መልሶ ለመያዝ/ የደህንነት ቢሮ ትእዛዝ እየተጠበቀ ነው::

እነ ሃብታሙ አያሌውን ለመፍታት/ከበር መልሶ ለመያዝ/ የደህንነት ቢሮ ትእዛዝ እየተጠበቀ ነው::

እነ ሃብታሙ አያሌውን ለመፍታት/ከበር መልሶ ለመያዝ/ የደህንነት ቢሮ ትእዛዝ እየተጠበቀ ነው::

የቀረበባቸው ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ በሽብርተኝነት ላይ ተሳትፎ አላደረጉም በሚል በነጻ እንዲሰናበቱ ከተደረጉት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ለመፍታት የደህንነት ቢሮ ትእዛዝ እየተጠበቀ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በፍርድ ቤት መዳፈር ወንጀል ተለጥፎባቸው እዛው ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጓል::

ለአቶ ሃብታሙ ቤተሰብ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት ፍርድ ቤት በነጻ ተለቀሃል ካለው ጊዜ ጀምሮ ባለቤቱን ጨምሮ ቤተሰቡ ወደ ታሰረበት እስር ቤት ይፈታል በሚል ጉጉት ቀንበቀን እየተመላለሱ መሆኑ ታውቋል::እንደ ምንጮቹ ዘገባ ተፈቱ የተባሉ እስረኞች እስካሁን እንዳልወጡ እና 48 ሰዓት እንዳለፋቸው ፍርድ ቤት ነፃ ያለውን የሚያስረው አካል ማነው ተጠያቂው ታዲያ ሀብታሙ ሄዶ አመራሮቹን እንዳለ ጠይቆአል ግን የሚሰጡት መልስ ቆይ አሁን ትወጣለህ ነው::ቤተሰቦቹ ትላንትና እስከ 1 ሰዓት ድረስ ማታ እዛ ቆየን ግን ምንም የለም ሲሉ ተናግረዋል::

ቤተሰቦቹ ስጋታቸውን እየገለጹ ነው::የእስር ቤት ሃላፊዎቹ የሚጠብቁት የደህንነቶቹን ትእዛዝ ሲሆን የፊታችን ሰኞ ይለቁአቸውና ከዛ እዛው በር ላይ ደህንነቶቹ መልሰው ይይዙአቸውና ከዛ ወደ ፍርድ ቤት ወስደው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዝግ ሊሆን ስለሚችል አራዳ ፍርድ ቤት ወስደው ቀጠሮ ይሰጡአቸዋል ብለን እናስባለን ያሉት ቤተሰቦቹ አቃቢ ህግ በነጻ በተለቀቁት ላይ ይግባኝ እላለሁ የሚል ተባራሪ መረጃ ስላለ ከበር ላይ አፍነው እንዳያስቀሯቸው ያሰጋል::እስካሁን ያልተለቀቁበት እና ታስረው የቆዩበት ጉዳይ ሃላፊነቱን የሚወስድ አካል አለመገኘቱ ሲታወቅ አቃቢ ሕግ ይግባኝ ይበል አይበል የተረጋገጠ ጉዳይ ካለመኖሩም በተጨማሪ የነሃብታሙንም በእስር ማቆየት ተጠያቂው አለመታወቁ ስጋቱን ጨምሯል::