ከደቡብ ወሎ ዩንቨርስቲ የታፈሱ ወጣቶች ወደ ደሴ እስር ቤት ተወሰዱ::

በደ/ወሎ ለጋንቦ ወረዳ የመቅደላ አንባ ዩንቨርስቲ የመሰረት ድንጋይ ወደ ቦረና በመዛወሩ የተነሳዉን ሰላማዊ ስልፍ ምክናየት በማድረግ ከጊባ ከተማ፣ጭሮ ከተማናአቅስታ ከተማ በፌደራል ፖሊስ እየታፈሱ ብዙ ወጣቶች መታሰራቸዉ ይታወቃል።

በደ/ወሎ ለጋቦ ወረዳ መንግስት በፈጠረዉ በመቅደላ አባ ዩንቨርስቲ ችግር ምክናየት ሲታፈሱ የከረሙት ቁጥራቸዉ በርካታ ወጣቶች ወደ ደሴ እስር ቤት መዛወራቸዉ ታዉቆል።ይሁንና ዛሬም ብዙ ወጣቶች ከየቦታዉ እየተለቀሙ ለጋቦ ፖሊስ ጣቢያ መታጎራቸዉ የሚታወቅ ሲሆን እስራቱ እንዳለ ሁኖ በጎን የወረዳዋን ሰዉ ለማሳመን የሚደረገዉ ጥረት እንደቀጠለ ነዉ::;

ዛሬ ጁመአ በጊባ ከተማ የዞኑ የፍትህ መምሪያ ሃላፊ በመገኘት ህዝቡን ሰብስበዉ ለማሳመን የሞከሩ ቢሆኑ መንግስት እስካሁን ምንም ነገር እንደለለ ቢያወራም ዛሬ በጊባ ከተማ የመጡት ባለስልጣን ኮሌጅ ነዉጅ ዩኒቨርስቲዉ አልሂደም የሚል ንግግር በመናገራቸዉ ለማህበረሰቡ እንቆቅልሽ ንግግር ሁኖበታል።በጊባ ከተማ በእነአቶ ደመቀ አማካኝነት የተጣለዉ የመሰረት ድንጋይ ዩንቨርስቲ እንጅ ተጨማሪ ኮሌጅ እንደለለ እየታወቀ ይህንን ቃላት ለምን እደተናገሩት አልታወቀም።

በተጨማሪም በዛሬዉ እለት በአቅስታ ከተማ በአቶ አበባዉ አማካኝነት የከተማዉን ህዝብ ሰብስበዉ ምንም ነገር እንደለለ ለማሳመን ሲሞክሩ ዉለዋል።ይሁንና እስካሁን ወረዳዋን እየጠበቀ ያለዉናማደሪያዉ በወረዳዉ አስተዳደር ግቢ ያደረገዉና በወረዳዉ በጀትና የወረዳዉን የደሃ ንብረት የሚያከስረዉ የሚያየፌደራል ፖሊስ ቁጥሩ ከ130 በላይ መሆኑ ይታወቃል።