ካለማስረጃ የተጠረጠረ ሁሉ የሚንገላታበት ጉዳይ ሊወገድ የሚችለው በኛ ትግል ብቻ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ላለፉት ጊዜያት በተለያዩ እስር ቤቶች ሲንገላቱ ሲገረፉ ሲሰቃዩ ከርመው ካለወንጀላቸው ወንጀለኛ ነን ብለው ፈርመው ከማእከላዊ ማሰቃያ ወደ ቃሊቲ ማጎሪያ ከተዘዋወሩ በኋላ በካቴና ከርመው በካንጋሮው ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ ተሳትፎአቸውን ማረጋገጥ አልተቻለም በማለት የለቀቃቸው መሆኑ ታውቋል::መጀመሪያም የታሰሩት ወያኔ ራሱ በጠራው ምርጫ ላይ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቀባይነት ያገኛሉ ብሎ ብመገመቱ እና ያለውን የወጣት ሕብረተሰብ ቀልብ ይገዛሉ ብሎ ስላሰበ በፍራቻ እንዳሰራቸው በወቅቱ የታወቀ ነው::እያኔ 100 በ100 አሸነፍኩ የሚለው ምርጫው ሕዝባዊ ተቃውሞ እንደማያስከትል የተቃዋሚዎችን አፍ በጉልበት ዘግቶ ካረጋገጠ በኋላ ሰላማዊ ትግል አፈር ገብቷል ተብሎ እስኪደመደም ድረስ ካሸ በኋላ እንደ ጠንካራ ፓርቲ የሆነውን አንድነት ካፈረሰ በኋላ አስፍላጊዉን ስራ ሰርቶ እስረኞችን ፈታ::ይህ መጀመሪያም ካለወንጀላቸው የታሰሩ ንጹሃን መሆናቸው የታወቀ ነው አሁን ደሞ ያሰራው አካል ራሱ በፍርሃት የሚርድ ወንጀለኛ መሆኑን በይፋ ደጋግሞ እያሳየን ነው:;
ንጹሃን ዜጎችን እያንገላቱ ነጻ ነው ማለት ነገ ከተጠያቂነት አያድንም ንጽሃንን አስሮ እየፈቱ የፖለቲካ ተሃድሶ ነው ማለት ሕዝብን ማጭበርበር ነው:;የነጮቹን ጫና እየጠበቁ መሾር ያለው አገዛዝ ምን ያህል አጣብቂኝ ላይ እንዳለ ያሳያል::በነጮች ሳምባ እንደሚተነፍስም ያሳብቅበታል::አሁንም ከተፈቱት በተጨማሪ በወህኒ የሚገኙ ዜጎች ሁሉ የሕሊና እስረኞች ስለሆኑ በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል::ዋስትና የሌለው አገዛዝ ነገም እንደሚያስከትል አናውቅም::ማንም እንዳሻው እያሰረ የሚፈታበት የአፈና ስርዓት ማክተም አለበት::ለዚህ ደሞ የለውጥ ሃይሎች በጋራ ቆመው ይህንን አስከፊ ስርአት መታገል ይገባቸዋል::ካለማስረጃ የተጠረጠረ ሁሉ የሚንገላታበት ጉዳይ ሊወገድ የሚችለው በኛ ትግል ብቻ ነው::