የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሺዋስ አሰፋና ሌሎች 2 ተጠርጣሪዎች በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ

በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የቆዩት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)፣ የሰማያዊና የአረና ፓርቲ አመራሮችና ሁለት ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ወሰነ፡፡
የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች በነፃ የተሰናበቱት፣ የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ ተሳትፎአቸውን ማረጋገጥ ባለመቻሉ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አስታውቋል፡፡
በውሳኔው መሠረት አቶ ሀብታሙ የሚጠየቁበት ወይም ሌላ የሚፈለጉበት ጉዳይ ከሌለ በዛሬው ዕለት እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺና አቶ የሺዋስ አሰፋ ከዚህ ቀደም ችሎት በመድፈር የተፈረደባቸውን ቅጣት እንዳጠናቀቁ እንዲፈቱ ወስኗል፡፡
very adimiring
Free the Ethiopian people !!!
We need dedicated and energetic hard working visionary leader’s from kebele all the way to the priminster office just like Dr.arkrbe ekubay……for prime minister,Dr.tewodros adhanom for forign minster,Dr debretsion gebremichael minstry of defence and interagency minister..
የህግ የበላይነት ማለት ይህ ነው ፍርድ ቤቱ ነፃ መሆኑን ማረጋገጫም ጭምር እነዚህ ሰዎች ነፃ ተብለው ለመፈታት የበቁት የህግ የበላይነትም ሊሰፍን የቻለው የውድ የህዝብ ልጆች ሂወትና ኣካል መስዋእትነት ጭምር ነው
ክብርና ሞገስ ለጀግኖች ሰማእታት
Weyane materya seyaterew gena.yemayefetaw yelem erasu eskegebabet maserna mefetatun yeketelale mekenyatum werketu lay hege ale yemetgeberut gen yebaleseletanunun kale enjie hegma befetum ale hgeu yeweyan mekelya new bekoferut guregad erasachew yemegebubet kene eruk ayedelam weyanem yezerawen machedu ayekerm hole eyaserna eyegedele hezeben eyasedede eyezerf yenor meselotal tegelu ayekomeme mejemeryam metaser aneberbachewm ahonem seletefetu berha yewerduten asemelesalw belo asebo kehon weyan ahonem algebawem keze bhala leseken enkan yemkom neger yelm goerfu eyemeta new ager kekefafayoche kasemesayoch keweshetamoch yemetlkekebet ken eyekerb new ensun fetanale belachu endebeftu yemasekeyes sera asebachu kehon atedekemu wetetun bekerbu tayoutalachu…