በኢትዮዺያ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃቸው በዲስክ የተቀረፀው የምኒሊክና የጣይቱ ነው::
( የአባ ዳኘውን ድምፅ ከታች ያገኙታል)
በሸክላ (ዲስክ) እየተቀረፀ የሚጫወተው መሣሪያ ( ግራሞፎን) ወደ ኢትዮዺያ የገባው በምኒልክ ዘመነ ምንግስት ነው:: የመጀመሪያው ግራማፎን በ1889 ዓ.ም ሄንሪ ደ ኦርሊንስ እና ኒኮላስ ሊዎንቲቭ ለምኒልክ አመጡላቸው::
ይህም እነሊዎንቲቭ ያመጡት ግራማፎን መጫወት ብቻ እንጂ ድምፅ የማይቀዳ ነበረ:: በኃላ በአመቱ በ1890 ዓ.ም ከንግስት ቪክቶሪያ የተላኩ የእንግሊዝ መልክተኞች በመጡ ግዜ ግራማፎኑንና ድምፅ መቅጃውን ይዘውላቸው መጡ:: እነኚህ መልክተኞች የእንግሉዝን ንግስት የንግስት ቪክቶሪያን ሰላምታ በዲስክ ቀርፀው አምጥተው ስለነበር ምኒልክና ጣይቱ ባሉበት መልክተኞቹ ዲስኩን አሰሙ:: ጣይቱም ስማቸውን ዲስኩ ውስጥ ሲሰሙ ‘እረ የኔንም ስም ትናገራለች’ አሉ::
በኃላም የምኒልክና የጣይቱ ድምፃቸው (ሰላምታቸው) ተቀድቶ ለንግስት ቪክቶሪያ ተላከ::
እንግዲህ በኢትዮዺያ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃቸው በዲስክ የተቀረፀው የምኒሊክና የጣይቱ ነው::
*ዻውሎስ ኞኞ – አጤ ምኒልክ ገፅ 340
[youtube http://www.youtube.com/watch?v=7qV27-OT5IE&w=650&h=355]
@tencolu ትክክል ነህ ሀሳቤ የታመነ ነው:ያንተ ሀሳብ ደግሞ ቻይና እንደሰራው ጫማ የተወላገደ ነው:ያንተ ሀሳቦች ጣራና ግድግዳው ጥላቻ ነው:
ደሥ የሚል የታሪክ ትውሥታ ነው ግን የመጅመሪያውን መኪና የዘወሩትንም ቢካተት ያሥደሥታል አሁን ላለንበት ደረጃ ድልድይ ናቸውና።
ሚንይልክ የኢትዮጵያ አይን ነበሩ:ሩቅአሳቢ ስለነበሩም ቴክኖሎጅን ከኢትዮጵያ ጋር አጋብተዋል:ዘመናዊ ወመንፈሳዊ ንጉስ ነበሩ:አንዳንድ ጥራዝ ነጠቆች ምንይልክን ሂትለር ይሉታል:በተዘዋዋሪ እነዚህ ትንሾች በጣሊያን ቀኝ በተገዛን ማለታቸው ነው:ከነፃነት ባርነትን መምረጥ ደግሞ ያው ከወሮበላነት የሚመነጭ ነው:ምንይልክ ባይኖሩ ኢትዮጵያ የዝንብ መጫወቻ ነበረች:ምንይልክን መጥላት ኢትዮጵያንና የራስን ማንነት መጠየፍ ነው:
@ከዘንድሮ…..ጦማሪው
የአመለካከትና የፖለቲካ ንፅህና የሌለው ሁሉ የዝንብ ማረፊያ ይሆናል ይሸታል ይጣላል።
@dc ማን ሙቶ ማን ነፃ ይወጣል?አሜሪካ ተቀምጠህ ሰወችን ተፋጁ,አምፁ ትላለህ:ስጋ ከሚበላበት ሀገር እየኖርክ ሽሮ የሚበላን ሰው ማዘዝ አትችልም:ዲሲ-ቅድሚያ ልበስ የዉቀት ካልሲ
@ከዘንድሮ…….
እኛ የዚህ አይነት ህሊና የለንም ግን እንደ ድንጋይ ወፍጮ ሁሌ አንተን ሥንወቅር ሥንመክር እንገኛለን እንጂ።
ባክህ አይንህን አታፍዝ ህዝቡ ተለውጣል የዚህን ምላሽ ደግሞ በኢቲቪ እንደለመድከው አሠማን