ተጽፈው ባደሩ ጽሁፎች መንግስት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብትዋል::
ተጽፈው ባደሩ ጽሁፎች መንግስት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብትዋል::
#Ethiopia #Ethiomuslims #Graphics #AddisAbaba #BBN #Miniliksalsawi
መልክቶቹን ህዝብ እንዳያያቸው ለማድረግ ና ለማጥፋት ፖሊሶች በከፍተኛ ቁጥር ተሰማርተዋል
የተጻፈባቸው ባነሮች እየተቀደዱ ነው ቢቢኤን ሰኞ ነሃሴ 11/2007
በዛሬው እለት የሙስሊሙን ኮሚቴዎች ፍርድ ተከትሎ ጠንካራ መልክእት ያላቸው ጽሁፎች በመላው አዲስአበባ ተጽፈው ማደራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በሁኔታው የተደናገጡ ፖሊሶች በቀለም ለማጥፋት እየተጣደፉ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በሳርቤት አደባባይ ፖሊሶች የተጻፈው ጽሁፍ በመክበብ ፎቶ ግራፍ ሲያነሱ እና ሲያጠፉ ተስተውለዋል፡፡ በሌላ በኩል በጎተራ ማሰላጫ ላይ የተጻፈውን ጽሁፍ ለማጥፋት ፖሊሶች መንገዱን ጭምር በመዝጋት አዛርድ በማብራት ሲዋከቡ ተስተውለዋል፡፡ በአዲስአበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተጻፉ ጽሁፎች መልክቶቹ በአግባቡ በህዝብ እየተነበቡ ነው፡፡ ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የኢህአዴግ መፈክር የተጻፈበት ባነር ጭቆናው ይብቃ ትግላችን እስከ ድላችን አምባገነኖች ለፍርድ ይቅረቡ የሚል ጽሁፍ መጻፉን ተከትሎ ፖሊሶች ሙሉ በሙሉ ባነሩን እንደቀደዱት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጸጨማሪ መረጃዎችን እየተከታተልን የምናቀርብ ሲሆን እናንተም በየአካባቢያችሁ የታዘባችሁትን ያያችሁትን ላኩልን ቢቢኤን የህዝብ ድምጽ ነው
